በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል ግጭት አገረሸ

March 29, 2024 – Konjit Sitotaw በአፋር ክልል፣ በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል በድጋሚ በተያዘው ሳምንት ግጭት ማገርሸቱን ዋዜማ ሰምታለች። ግጭቱ የተከሰተው፣ በገቢ ረሱ ዞን (ዞን ሦስት) አሚባራ ወረዳ ውስጥ አፋርና ሱማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት ገዳማይቱ ቀበሌ እንደኾነ ታውቋል። በግጭቱ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ሳይገደሉና ሳይቆሰሉ እንዳልቀሩ ተነግሯል።

በሕገ ወጥ መንገድ ዜጎችን ማሰር እና ማንገላታት የገዢውን ፓርቲ እንባገነናዊ ፈላጭቆራጭነት ያመለክታል- ኢሕአፓ

March 29, 2024 በሕገ ወጥ መንገድ ዜጎችን ማሰር እና ማንገላታት የገዢውን ፓርቲ እንባገነናዊ ፈላጭቆራጭነት ያመለክታል- ኢሕአፓ (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ”በሕገወጥ መንገድ ዜጎችን ማሰር እና ማንገላታት የሚያመለክተው የገዢውን ፓርቲ እየሄደበት ያለውን አንባገነናዊ ፈላጭ ቆራጭነት ባህሪ ነው ሲል አወገዘ። የኢሕአፓ ሊቀ መንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ከትላንት ወዲያ በፓርቲው ጽህፈት ቤት በስራ ላይ እንዳሉ […]

የኢሕአፓ ምክትል ሊቀ መንበር ተፈቱ ፣ ሊቀ መንበሩ ታሰሩ

March 29, 2024 – DW Amharic  የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሊቀ መንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ መታሰራቸው ተገለፀ። የፓርቲው ሊቀ መንበር ማክሰኞ ዕለት በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ሲውሉ «የእርስ በእርስ ጦርነት ይብቃ» በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ለማዘጋጀት ሲንቀሳቀሱ ተይዘው አዋሽ አርባ ለወራት በእሥር ላይ የቆዩት የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር ሰሞኑን ተፈተዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ […]

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና ሰሜን ሸዋ አዋሳኝ ግጭት

March 29, 2024 – DW Amharic  በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞን አዋሳኝ አካባቢ ለተከታታይ ሁለት ሳምንታት የቀጠለው ግጭት ባለፉት ሁለት ቀናት ጋብ ማለቱን የየዞኖቹ ነዋሪዎች አስታወቁ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በጦርነት የተጎዱት የትግራይ ክልል የጤና ተቋማት

March 29, 2024 – DW Amharic  በትግራይ ክልል በጦርነቱ የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት እና አዳዲስ የጤና ፕሮጀክቶች ለመጀመር እየሠራ መሆኑ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በክልሉ በተለይም በከተሞች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች፣ በወጣቶች ደግሞ ሱስ አሳሳቢ እንደሆነ የትግራይ ጤና ቢሮ ይገልፃል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

በጋምቤላ ክልል በላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት

March 29, 2024 – DW Amharic  ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ይንቀሳቀስ ነበር በተባለው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው ጥቃት የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼቨለ ተናግረዋል። ጥቃቱ የደረሰው ትናንት ረቡዕ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢ ነው። ጥቃቱን ያደረሱ ሐይሎች ግን አለመያዛቸውን ነው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹት።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ከተማና ከተሜነትን ለዓመታት አዋዳ የኖረችው ፒያሳ

March 29, 2024 – DW Amharic  ከተማ እያደገ፣ እየተዋበ፣ የላቀ እየዘመነ፣ የፍሳሽና እና ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱ እየተሳለጠ፣ መንገዶች እየሰፉ መሄዱ የማይቀር ነው። ሰሞነኛው ለልማት በሚል ፒያሳን የማፍረሱ የመንግሥት ርምጃ ብዙ ድንጋጤ፣ ከተለያየ አቅጣጫ አግራሞት፣ ቁጭት፣ ብስጭት፣ ሐዘን እና ለምን የሚሉ ጥያቄዎችንም ከብዙዎች አስነስቷል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የኩላሊታችንን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዙ 6 ቀላል መንገዶች

ከ 5 ሰአት በፊት በደም ውስጥ ያለን ቆሻሻ እያጣራ በሽንት መልክ የሚያስወጣው ኩላሊት በጣም አስፈላጊ ከሆኑ የሰውነት ክፍሎች አንዱ ነው። እንደ ዓለም አቀፉ ኒፍሮሎጂ ማኅበር ደግሞ የደም ግፊትን ከመቆጣጠር ባለፈ በሰውነት ውስጥ ያለን የኬሚካል ሚዛን ለመጠበቅ ያግዛል። በጣም ወሳኝ ሆነው አገልግሎቱ ደግሞ ቀይ ደም ህዋስ እንዲዘጋጅ ድጋፍ ማድረጉ ነው። ስለዚህም ኩላሊት ሲጎዳ መዘዙም ብዙ ነው። […]

እስራኤል በሶሪያ ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማ 40 ሰዎች ተገደሉ

ከ 1 ሰአት በፊት እስራኤል በሶሪያ ላይ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 36 ሰዎች መገደላቸው የሶሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ገለጸ። ከአሌፖ ከተማ በቅርብ ርቀት በሚገኘው አካባቢ በአገሪቱ ሰዓታት አቆጣጠር ሐሙስ መጋቢት 19/2016 ዓ.ም. እኩለ ሌሊት ላይ በርካታ የአየር ጥቃቶች መፈጸማቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ሶሪያ ኦብዘርቫቶሪ ፎር ሂዩማን ራይትስ የተባለ ቡድን የጥቃቱ ዒላማ የነበሩት በሶሪያ […]