በኬንያ ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ ቢያንስ 32 ሰዎች ሞቱ

ከ 3 ሰአት በፊት በኬንያ መዲና ናይሮቢ በተከሰተ ከባድ ጎርፍ መንገዶች በውሃ ተጥለቅልቀው የታዩ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣን የጎርፉ መጠን “እጅግ በከፋ ደረጃ እየጨመረ ነው” ብለዋል። ባለፉት ቀናት በኬንያ የጣለው ከፍተኛ ዝናብ መጠነ ሰፊ ውድመት እያስከተለ ነው። የመንግስታቱ ድርጅት ቢያንስ 32 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ እና ከ40 ሺህ የሚበልጡት ደግሞ በዝናቡ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው […]

የኢራን መንግሥትን የተቃወመው ራፐር ሞት እንደተፈረደበት ጠበቃው ተናገረ

ከ 4 ሰአት በፊት መንግሥትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የታሰረው ኢራናዊ ራፐር በሞት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን ጠበቃው ገለጸ። ቱማጂ ሳሊህ የተባለው ሙዚቀኛ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢራን የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ በመደገፍ የራፕ ሙዚቃ አውጥቶ ነበር። በወቅቱ በመላው ሀገሪቱ ማሻ አሚኒ የተባለች ሴት ሂጃብ በአግባቡ አልለበሽም በሚል በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች ህይወቷ ማለፉን ተከትሎ አገሪቷን ያናወጠ ከፍተኛ […]

ለዩኔስኮ የማስመረጫ ሰነድ ዝግጅት እየተደረገለት ያለው ‹‹ፊላ››

ዲራሼዎች በፊላ ሲጫወቱ ኪንና ባህል ለዩኔስኮ የማስመረጫ ሰነድ ዝግጅት እየተደረገለት ያለው ‹‹ፊላ›› በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: April 24, 2024 ቀደምትና ታሪክ ጠገብ እንደሆነ በሚወሳለት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋርዱላ የሚገኘው የዲራሼ ብሔረሰብ፣ ልዩ በሆኑት ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎቹና ጨዋታዎቹ ታዋቂ ነው፡፡ በቀዳሚነት የሚወሳው ከአገር አልፎ ባህር ማዶ ድረስ ዕውቅናን ያገኘው ‹‹ፊላ›› የሚባለው ባህላዊ የሙዚቃ መሣሪያ ነው፡፡ ‹‹ፊላ እና ሌሎች […]

አዲስ ሪከርድ ያስመዘገበው ዓለም አቀፉ የአገር መከላከያ ወጪ

የዓለም የወታደራዊ ወጪ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል (ሻተርሰቶክ) ዓለም አዲስ ሪከርድ ያስመዘገበው ዓለም አቀፉ የአገር መከላከያ ወጪ ምሕረት ሞገስ ቀን: April 24, 2024 በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.ኤ.አ. በ2023 ለመከላከያ ኃይል የዋለው ወጪ 2.4 ትሪሊዮን ዶላር መሆኑን የስቶኮልም ዓለም አቀፍ የሰላም ጥናት ተቋም አስታውቋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1949 የተቋቋመውና በየዓመቱ ለውትድርና የዋለውን ወጪ የሚቃኘው ተቋም፣ ሰኞ ሚያዝያ 14 ቀን […]

በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገለጸ

ማኅበራዊ በሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የተነሳውን ሰደድ እሳት መቆጣጠር አለመቻሉ ተገለጸ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: April 24, 2024 በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገበውና በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን  በሚገኘው የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ ከሰባት ቀናት በፊት ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የመነሻው ምክንያት ሳይታወቅ የተነሳውን ሰደድ እሳት በቁጥጥር ሥር ማዋል አለመቻል በአካባቢው ነዋሪዎች ሥጋት መፍጠሩ ተገለጸ፡፡ በርካታ […]

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ተዘግተው ተማሪዎች እንዲሸጋሸጉ ተደረገ

ዜና የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ተዘግተው ተማሪዎች እንዲሸጋሸጉ ተደረገ ተመስገን ተጋፋው ቀን: April 24, 2024 በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሥር የሚገኙ የዘንዘልማና የሰባታሚት ካምፓሶች በፀጥታ ችግር ምክንያት በመዘጋታቸው የግብርና፣ የጤና፣ የጂኦሎጂና የዲዛስተር ማኔጅመንት ተማሪዎች የፀጥታው ችግር እስኪቀረፍ፣ ከተማ ውስጥ ባሉ ካምፓሶች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድረጉን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ፡፡ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት […]

ከተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በሚንቀሳቀሱ የፀጥታ አካላት ላይ ዕርምጃ መውሰድ ተጀመረ

ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ዜና ከተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በሚንቀሳቀሱ የፀጥታ አካላት ላይ ዕርምጃ መውሰድ ተጀመረ ፅዮን ታደሰ ቀን: April 24, 2024 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ፣ ከተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት ውጪ በሚንቀሳቀሱ በርካታ የፀጥታ አካላት ላይ ሕጋዊ ዕርምጃ መውሰዱን ትናንት ሚያዝያ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን […]

የአውሮፓ ኅብረት ተግባራዊ ሊያደርግ ያቀደው ሕግ ለአርሶ አደሮችና ለላኪዎች ፈታኝ ይሆናል ተባለ

የአግሪቴክ ሲምፖዚየም የተገኙ ተወካዮች ዜና የአውሮፓ ኅብረት ተግባራዊ ሊያደርግ ያቀደው ሕግ ለአርሶ አደሮችና ለላኪዎች ፈታኝ ይሆናል ተባለ ሰላማዊት መንገሻ ቀን: April 24, 2024 የአውሮፓ ኅብረት ቡናን ጨምሮ ወደ አባል አገሮቹ የሚላኩ ሰባት የምርት ዓይነቶች ከደን ጭፍጨፋና መመናመን ነፃ መሆናቸው ሳይረጋገጥ፣ ለግብይት እንዳይቀርቡ የሚከለክል ሕግ አውጥቶ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ማቀዱ፣ ለገበሬዎችና  በወጪ ንግድ ለተሰማሩ […]

ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የበጀት እጥረትና የሠራተኞች ፍልሰት ፈተና ሆነውበታል

ዜና ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የበጀት እጥረትና የሠራተኞች ፍልሰት ፈተና ሆነውበታል ናርዶስ ዮሴፍ ቀን: April 24, 2024 የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ሪፖርት 722 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ቢያሳይም፣ የበጀት እጥረት የታቀዱ ግዥዎችን ለመፈጸም አዳጋች እንዳደረገበትና የሠራተኞች ፍልሰት ተግዳሮቶች እንደገጠሙት ታወቀ።  ባለሥልጣኑ ለሠራተኞቹ አቅርቦ ውይይት የተደረገበት ሪፖርት፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለማሰባሰብ ከታቀደው 300 ሚሊዮን […]

ከራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ50 ሺሕ በላይ መድረሱ ተገለጸ

ዜና ከራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ50 ሺሕ በላይ መድረሱ ተገለጸ በጋዜጣዉ ሪፓርተር ቀን: April 24, 2024 በቅርቡ ግጭት ከነበረባቸው የራያ ዞን አካባቢዎች ማለትም ከአላማጣ ከተማ፣ ከራያ አላማጣ፣ ከዛታና ከኦፍላ ወረዳዎች የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከ50 ሺሕ በላይ መድረሱ ታወቀ፡፡ ከአካባቢው አስተዳደር ኃላፊዎች መረጃ አግኝቻለሁ ያለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት፣ 42 […]