የጤና አገልግሎት አቅርቦት ይዞታ በኢትዮጵያ

April 10, 2024 – DW Amharic  ከዓለም ሕዝብ ቁጥር ከግማሽ በላይ የሚሆነው መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ማግኘት አለመቻሉን የዓለም የጤና ድርጅት ይፋ አድርጓል። ባሳለፍነው ሳምንት እሑድ በመላው ዓለም የታሰበውን የዓለም የጤና ቀን መነሻ በማድረግ በአካባቢያችሁ አገልግሎቱ እንዴት ነው? ያልናቸው ወገኖች የመድኃኒት አቅርቦት ዋነኛው ችግር መሆኑን ይገልጻሉ።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የብለክለት ሥጋት ያጠላበት የሀዋሳ ሐይቅ

April 9, 2024 – DW Amharic  በደለል እና በፕላስቲክ ቆሻሻ ብክለት ሥጋት ላይ የወደቀውን የሀዋሳ ሀይቅ ለመታደግ ማህበረሰብ አቀፍ ዘመቻ እያካሄደ እንደሚገኝ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ መምሪያ አስታወቀ። በሀይቁ ዙሪያ የሚገኙ የጎርፍ መግቢያዎች ልኬት መካሄዱን የጠቀሱት የመምሪያው ባለሙያ ውጤቱ ህልውናውን ለመጠበቅ አንቂ ሆኖ እንዳገኙት ለዶቼ ቬለ ተናግረዋል።… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

የዓለም ባንክ ጥናት ‘የሙቀት መጨመር’ በኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት ላይ ተጽእኖ አለው አለ

9 ሚያዚያ 2024 የዓለም ባንክ በአየር ንብረት ለውጥ የተነሳ በሚከሰት የሙቀት መጨመር ምክንያት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ውጤት ምን ያህል ተጽዕኖ ደርሶበታል በሚል ጥናት አጥንቶ በቅርቡ ይፋ አድርጓል። በዚህ ጥናቱም በትምህርት ዓመቱ በተለይ ደግሞ በፈተና ወቅት ለከፍተኛ ሙቀት ተጋላጭ የሆኑ ተማሪዎች ከሌሎች በተለየ ዝቅተኛ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል። ዓለም ባንክ ለዚህ ጥናቱ ከአውሮፓውያኑ ከ2003 እስከ 2019 ድረስ […]

ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት

April 8, 2024 – DW Amharic  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሙከርም ሚፍታህ፣ ከጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት ለመሆኑ ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል… … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ

ሕይወቱን ለመቀየር መላ አፍሪካን ያካለለ ርቀት የሮጠው ግለሰብ

ከ 3 ሰአት በፊት የማይታሰብ የሚመስለውን ፈተና ለመጋፈጥ እራሱን ሲያዘጋጅ፤ “ቆም ብዬ ሕይወቴን ተመለከትኩት” ይላል የ27 ዓመቱ ወጣት። ወጣቱ በአእምሮ ጤና ይሰቃያል። የመጠጥ እና የቁማር ሱሶች ሕይወቱን አመሰቃቅለውታል። “ምንም ባጣ የሚቆጨኝ ነገር የለም” ብሎ በማመኑ ከባዱን ፈተና በመጋፈጥ በሕይወቴ ለውጥ ማምጣት አለብኝ ብሎ ተነሳ። ራስል ኮክ የተባለው እንግሊዛዊ ሕይወቱን የሚቀይረው አፍሪካን የሚያካልል ርቀት በመሮጥ መሆኑን […]

‹‹በሌሎች ክልሎች ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከትግራይ አንፃር አነስተኛ ነው ብዬ ለመግለጽ አልችልም›› ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ 

ሳሙኤል ቦጋለ April 7, 2024 ቆይታ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ዕርዳታ የሚያቀርቡ ዓለም አቀፍ የረድዔት ድርጅቶችና ሠራተኞች በአገሪቱ በሚከሰቱ የበሽታ ወረርሽኞች፣ ድርቅ፣ ጎርፍና ጦርነት ምክንያት ባለፉት ጥቂት ዓመታት በእጅጉ ተፈትነው ነበር። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ፣ በዩክሬንና በጋዛ ግጭቶችና እየተካረረ በመጣው የዓለም ጂኦ ፖለቲካዊ ፉክክር፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት እየተስተዋለ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አገሮች ሊያገኙ የሚችሉት ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀነሰና ፈተና ውስጥ እየገባ ነው። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ2023 ሰብዓዊ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወደ 20 ሚሊዮን ለሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ምላሽ ለመስጠት ከሚያስፈልገው 3.9 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው አንድ ሦስተኛው ብቻ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት አጠቃላይ ሁኔታ፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የነበሩ ፈታኝ እክሎችና የወደፊት ተግዳሮቶችን በተመለከተ የሚሉት አላቸው። በፖሊሲ አወጣጥና በሰብዓዊ ምላሽ የሥራ መስክ የሦስት አሠርት ዓመታት ልምድ ያካባቱት አላክባሮቭ (ዶ/ር) ወደ እዚህ መስክ ከመቀላቀላቸው በፊት በአገራቸው አዘርባጃን ሐኪም ነበሩ። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ ኤጀንሲዎች በተለያዩ ኃላፊነቶች ያገለገሉ ሲሆን፣ ለአብነትም በሱዳንና በሶማሊያ የዩኤንኤፍፒኤ ፕሮግራም ኦፊሰር፣ በአፍጋኒስታንና ፍልስጤም የሰብዓዊ ዕርዳታ ኦፊሰር በመሆን አገልግለዋል። ባለፈው ነሐሴ ወር ደግሞ በተመድ የኢትዮጵያ ጽሕፈት ቤት ዋና ተወካይ ሆነው ተሹመዋል። በኢትዮጵያ ስላሉ የሰብዓዊ ምላሽ ጥረቶች፣ ስለሰብዓዊ ዕርዳታ ፕሮግራሞችና የገንዘብ ድጋፎች፣ እንዲሁም የወደፊት የሰብዓዊ ዕርዳታ ዕጣ ፈንታን በተመለከተ ሳሙኤል ቦጋለ ከእሳቸው ጋር ያደረገው ቆይታ እንደሚከተለው ተሰናድቷል። ሪፖርተር፡– ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ለሰብዓዊ ዕርዳታ ኤጀንሲዎች ከባድ ይመስለኛል። የእርስዎ ምልከታ ምንድነው? አላክባሮቭ፡- እዚህ አገር በጣም የተደባለቁ ሁኔታዎች መኖራቸውን ተረድቻለሁ። በግጭት፣ በተራዘመ ድርቅ፣ ጎርፍና በአየር ንብረት አደጋዎች የተጎዱ አካባቢዎች አሉ። የእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ጥምረትና የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ የተፈጠረው ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ ሲታከልበት ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሸክም ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ። በዚህ ላይ ደግሞ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ […]