አንዳንድ አገራት ፍልስጤምን እንደ አገር ዕውቅና የማይሰጧት ለምንድነው?

ከ 5 ሰአት በፊት ባለፈው ሳምንት የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ፍልስጤም የድርጅቱ ሙሉ አባል ለመሆን ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ድምፅ ሰጥቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣኗን ተጠቅማ ይህን ጥያቄ ውድቅ ብታደርገውም 12 የምክር ቤቱ አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል የአሜሪካ አጋር የሆኑት ፈረንሳይ፣ ጃፓን እና ኮሪያ ይገኙበታል። ዩናይትድ ኪንግደም እና ሰዊትዘርላንድ ድምፀ ተዐቅቦ […]

በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ቀጣይ ሥጋቶች

ፖለቲካ በሲሳይ ሳህሉ April 24, 2024 የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽሕፈት ቤት በጋራ ያቀረቡትን ምክረ ሐሳብ ተከትሎ፣ የሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ለመዘርጋት ታምኖበት ወደ ሥራ ከተገባ ከአንድ ዓመት በላይ ተቆጥሯል፡፡ የሽግግር ፍትሕ በአገሪቱ ለዘመናት የተፈጸሙና አሁንም የቀጠሉ ያልጠሩ ትርክቶች፣ ቁርሾዎች፣ አለመተማመኖች፣ የእርስ በርስ ግጭቶችና የሰላም ዕጦቶች፣ […]

ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገራዊ ምክክር ላይ በአጀንዳነት የሚቀርቡ ጉዳዮችን እንዲያዘጋጁ ተጠየቁ – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

April 24, 2024 በናሆም አየለ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በሀገራዊ ምክክር ላይ “አጀንዳ ሊሆኑ ይገባሉ” የሚሏቸውን ጉዳዮች እንዲያዘጋጁ  ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በደብዳቤ ጥሪ አቀረበ። የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በሚያቀርቧቸው አጀንዳዎች ላይ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት የሚያካሄዱበትን ሁኔታ እንደሚመቻች ኮሚሽኑ አስታውቋል።  “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው እና ባለፈው ሳምንት ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተላከው ደብዳቤ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር […]

HRC55 – Joint Statement on the importance of transitional justice and accountability in Ethiopia – European External Action Service 11:06 

Delegation of the European Union to the UN and other international organisations in Geneva  03.04.2024   Geneva  Press and information team of the Delegation to the UN in Geneva UNITED NATIONS HUMAN RIGHTS COUNCIL 55th session Joint Statement Mr President, I am making this statement on behalf of a group of 44 countries. During the 54th session of the Council, […]

አቶ ጌታቸው ረዳ ከብልፅግና ጋር ስለመዋሃድ፣ ስለሰሞኑ ግጭት እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ስላላቸው ግንኙነት ምን አሉ?

24 ሚያዚያ 2024, 07:14 EAT የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ፓርቲያቸው ህወሓት ከገዢው ብልፅግና ጋር በሚያደርገው ንግግር ወቅት የውህደት ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ እንደማያውቅ ለቢቢሲ ተናገሩ። ህወሓት ዋነኛው መሥራች እና አስኳል የነበረበት የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባርን (ኢሕአዴግ) በመተካት የገዢነት መንበሩን ከተረከበው ብልፅግና ጋር ከተለያየ በኋላ ነበር በሁለቱ ወገኖች መካከል ደም አፋሳሽ ጦርነት የተከሰተው። […]

የቡድን ሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች ከሰሜን ኢትዮጵያ የሚወጡት ዘገባዎች እንዳሳሰባቸው ገለጹ

April 24, 2024 – VOA Amharic  ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑት የቡድን ሰባት አባል ሀገራት ኤምባሲዎች “አከራካሪ” ከተባሉት ከሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚወጡት የግጭት ዘገባዎች እንዳሳሰቧቸው ገለፁ። ኤምባሲዎቹ ቅዳሜ ዕለት በጋራ ባወጡት አጭር መግለጫ፣ ውስብስብ ፖለቲካዊ እና የደኅንነት ቀውስን ለመፍታት እንዲሁም በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ ሁሉንም ያካተተ ውይይት ማድረግ ብቸኛ መንገድ መሆኑን ገልፀዋል። … … ሙሉውን ለማየት ወይም ለማንበብ […]

ዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የምትልክበት ሕግ ምንድን ነው? ተፈጻሚነቱስ በማን ላይ ነው?

ከ 5 ሰአት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ […]