May 14, 2019

Source: https://ethiothinkthank.com

የሚዲያ መግለጫ

ጀኔቫ/ግንቦት 9 ፣2019 (እ.አ.አ)-በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወቅታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ጉባኤ አማካኝነት በሚካሄደው ሶስተኛው ዙር አለም አቀፍ መደበኛ የሀገራት የሰብአዊ መብት አያያዝ ግምገማ እና የምክክር መርሃ ግብር ግንቦት 14 ቀን 2019 ይካሄዳል፡፡ የመርሀ ግብሩ ጠቅላላ ሂደት በwebcast live ድህረገጽ ላይ በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

ኢትዮጵያ ከግንቦት 6 እስከ 17 ቀን 2019 ድረስ ለሦሥተኛ ጊዜ ለግምገማ ከሚቀርቡ 14 ሀገሮች መካካል ስትሆን፤ ከዚህ በፊት ለመጀመሪያ ጊዜ በ2009 እንዲሁም ለሁለተኛ ጊዜ በ2014 በተካሂዱት ሁለት የአለም አቀፉ ወቅታዊ የሀገራት የሰብአዊ መብት ግምገማ(UPR) ዙሮች ላይ መገምግሟ ይታወሳል፡፡ የመጀመሪያና ሁለተኛ የግምገማ ውጤቶችን ለማግኘት ቀጥሎ ያለውን መረብ ይጫኑ first and second UPR reviews.

አለም አቀፉ መደበኛ የሀገራት የሰብአዊ መብት ግምገማና የምክክር መድረክ (UPR) ከሦስት አቅጣጫ በተገኘ መረጃ ላይ ተመርኩዞ ይፈፀማል፡፡ እነዚህም ሀ) ከተገምጋሚው ሀገር በሚቀርብ ሪፖርት፤ ለ)ከተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ጉባኤ ልዩና ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ኤክስፐርቶችና ቡድኖች እነዲሁም ሌሎች የተባበሩት መንግስታት አካላት( Special procedures, human right treaty bodies, and other UN entities) የሚቀርቡ ሪፖርቶች፤ (ሐ)ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ለምሳሌ ከሰብአዊ መብት ተቋማት፣አህጉራዊ ድርጅቶች፣ እንዲሁም ሲቪክ ማህበራት የሚያቀርቧቸው ሪፖርቶች ናቸው፡፡

ከሦስቱ ምንጮች የተገኙ ሪፖርቶችን ለማግኘት እዚህ here ይጫኑ፡፡

ቦታ፡ የስብሰባ አዳራሽ ቁጥር 20 palais des Nationes,Geneva

ጊዜና ሰዓት 09.00-12.30, (ማክሰኞ ግንቦት 6)፤ Tuesday 14 May (Geneva time, GMT+1 hour)

አለም አቀፉ ወቅታዊ የሀገራት የሰብአዊ መብት ግምገማና የምክከር መድረክ (UPR) ፤ አጠቃላይ መቶ ዘጠና ሦስቱ የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት የሰብአዊ መብት አጠባበቅና አያያዝ በየአራት አመት ከግማሽ ጊዜ ውስጥ የሚገመገምበት ሂደት ነው፡፡መቶ ዘጠና ሦስቱ አባል ሀገራት የመጀመሪያው መድረክ ከተፈፀመበት ከ ሚያዝያ 2008 ጀምሮ ሁለት ጊዜ ተገምግመዋል፡፡በዚህ በሦስተኛው ዙር ተገምጋሚ ሀገራት ከዚህ ቀደም በሁለተኛው ግምገማ ወቅት የተሰጣቸውን ምክረ ሀሳቦች/አስተያየቶች/ ለመተግበር የወሰዷቸውን እርምጃዎች እንዲሁም በሀገራቸው ውስጥ ያለውን ወቅታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሁኔታ ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል፡፡

መርሀ ግብሩን በቀጥታ በ http;//webtv.un.org መከታተል ይቻላል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የሚቀርቡ ፅሁፎችንና አቅራቢዎችን ማንነት ለመረዳትና ለማግኘት UPR Extranet [username: hrc extranet (with space); password: 1session] ይጎብኙ

ገምጋሚ ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ የሚሠጡ ምክረ ሀሳቦች (አስተያየቶችን) ለማጽደቅ ለግንቦት 16 ፣2019 ከሰዓቱ 17፡ 30 ቀጠሮ ይዟል፡፡ በዚህ ሂደት ላይ የሀገሪቱ መንግስት የተሰነዘሩትን አስተያየቶች በተመለከተ አቋሙን የመግለፅና የማሳወቅ ሙሉ ፈቃድ አለው፡፡በግምገማው ሂደት ኢትዮጵያ ላይ የተሠነዘሩ አስተያየቶች በተመሳሳይ ቀን ለመገናኛ ብዙሃን ይጋራሉ፡፡