11 ጁላይ 2019

ግመሎች

ላውረን ብሪስቤን ኪውካሜል የተባለ የግመል ወተት ማቀነባበሪያ አላት። በአውስትራሊያ ብቸዋኛው ፈቃድ ያለው ማቀነባበሪያ ነው።

የአውስትራሊያ የግመል ወተት ንግድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎመራ መጥቷል። በአገሪቱና በዓለም አቀፍ ደረጃም የግመል ወተት ፍላጎት እየጨመረ ነው።

ላውረንና ቤተሰቦቿ በግመል ወተት ንግድ የተሰማሩት ትርፋማ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፤ ሥራውን ስለሚወዱት ጭምርም ነው። ግመሎቹን ከቤተሰቡ አባላት ለይተው እንደማያዩዋቸው ትናገራለች።

የዱቄት ወተት እና የእናት ጡት ወተት ምንና ምን ናቸው?

“እንደ ሰው የተለያየ ባህሪ አላቸው። አጠገባቸው ሆነሽ ስለ ምንም ጉዳይ ብታወሪ ይረዱሻል” ትላለች።

ብዙ የአውስታራሊያ አርሶ አደሮች ከሌሎች እንስሳት ይልቅ ግመልን ይመርጣሉ። ግመሎች ወደ አገሪቱ የገቡት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1840 ሲሆን፤ አሁን 1.2 ሚሊየን ግመሎች በመላው አውስትራሊያ ይገኛሉ።

አውስራሊያ ውስጥ የመጀመሪያው የወተት ማቀነባበሪያ የተከፈተው 2014 ላይ ነበር። ዛሬ ግን ንግዱ በአገሪቱ እያንዳንዱ ጥግ ተስፋፍቷል።

ከአዕዋፍ እስከ አንበሳ ያሉ እንስሳት በግለሰቦች እጅ ለስቃይና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው።

ዓለም ላይ ቀዳሚ የግመል ወተት አምራቾች የምሥራቅና ሰሜን አፍሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ናቸው። የአውስትራሊያ መንግሥት በቀጣይ አምስት ዓመታት የግመል ወተት ንግድን እንደሚያሳድግ ይናገራል።

በአገሪቱ 2016 ላይ ይመረት የነበረው 50,000 ሊትር ወተት ወደ 180,000 ሊትር አድጓል።

የወተት ማቀነባበሪያ ካላቸው ቤተሰቦች መካከል ሜጋን ዊልያምስና ባለቤቷ ይገኙበታል። 2014 ላይ በሦስት ግመሎች ንግዱን ጀምረው አሁን የ300 ግመሎች ባለቤት ሆነዋል።

በቀን ከአንድ ግመል ስድስት ሊትር ወተት እያለቡ ወደ ሲንጋፓር፣ ታይላንድና ማሌዥያ ይልካሉ። ንግዳቸውን ወደ ቻይናና አሜሪካ የማስፋፋት እቅድም አላቸው።

“የአውስታራሊያ ግመሎች ጤናማ መሆናቸው የወተት ንግዱ እንዲያድግ ይረዳል” ትላለች ሜጋን።

በመካከለኛው ምሥራቅ በተደጋጋሚ የሚከሰተው የግመል በሽታ የመካከለኛው ምሥራቅን የወተት ንግድ ይፈታተናል።

በእርግጥ የሰው ልጅ የግመል ወተት መጠጣት ከጀመረ ከ6,000 ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። የግመል ወተት ውድ ቢሆንም፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የሰዎች ፍላጎት እየናረ መጥቷል።

ከሺዎች እስከ ኳትሪሊየን እንስሳት በአንድ ቀን የሚወለዱባት ምድር

የግመል ወተት ለጤና ጠቃሚ እንደሆነ በተደጋጋሚ መገለጹን ተከትሎ፤ ብዙዎች አጥብቀው ይፈልጉት ጀምረዋል። የግመል ወተት ቫይታሚን ሲ፣ ቢ፣ አይረን፣ ካልሽየም፣ ማግኒዥየምና ፖታሽየም ንጥረ ነገሮች አለው።

የግመል ወተት ከአውስትራሊያ ወደ ሲንጋፓር የምታስገባው ረቤካ ፎርውድ፤ “እጅግ ጠቃሚ ከሆኑ ምግቦች አንዱ ነው” ትላለች።

የሥነ ምግብ ባለሙያዋ ቻርሊን ግሮስ፤ የግመል ወተት የንጥረ ነገር ክምችት ጠቃሚ መሆኑን ታስረዳለች።

“የኮሌስትሮልና ስኳር መጠኑ አነስተኛ ነው። የላም ወተትንም ሊተካ ይችላል። በእርግጥ ስለ ግመል ወተት የሚባሉ ነገሮች በአጠቃላይ በጥናት የተደገፉ አይደሉም” ትላለች።

የግመል ወተት ቺዝ (አይብ) እንዲሁም የቆዳ መንከባከቢያ ቅባቶች ለመሥራትም እየዋለ ነው።