November 2, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/165945

Sheger FM : ትዕግስትና ሆደ ሰፊነት ከማያባራ የጭካኔ ድርጊት ጋር እንዴት ይታረቃል? ኢትዮጵያውያን የአብሮ መኖር ልኬታቸውን ረጅም ዘመን ይቆጥሩበታል ግድያና ክፉ ስራዎችን አጥብቀው በሚከለክሉ እምነቶች ተከታዮች መሆናቸውም ለረጅም ጊዜ ይጠቀሳል፡፡ግን አሁን የሚታየውና የሚሰማው ይፈፀማል ተብሎ የማይታሰብ የማይገመትም ነበር አብሮ የኖሩ፣ ክፉ ደግ ያሳለፉ ዜጎች በድንጋይ እየተወገሩ፣ በበትር እየተቀጠቀጡ መሞታቸውን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡ግጭቶች ከመፈጠራቸው ይባስ አፈፃፀማቸው አስደንጋጭ ሆኗል፡፡ ይኽን መሰል አሰቃቂ ድርጊት ሲፈፀም ሃይ የሚል አካል ቶሎ አለመድረሱ የወደፊቱንም ጊዜ አስጊ አድርጎታል፡፡ ስለዚህ ህዝቡ መንግስትንም እየጠየቀ ነው፡፡