በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረውና በደርዘን ለሚ
ቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው
እንቅስቃሴ አሁን ባለው አዲስ ሁኔታ በአጀንዳውም በተሳትፎውም እየሰፋ ሲሄድ እየታ
ዘብን ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ
ንቅናቄ በወያኔ /ኢህአዴግ ግፈኛ አገዛዝ በተሰጠው የጭፍጨፋ ምላሽ የተነሳ ንቅናቄ
ው በአጠቃላይ ቁጣን በተላበሰ መልክ
ለዴሞክራሲ ወደሚለው ጥያቄ እየተቀየረ ነው፡፡ እንደዚህ በመሆኑም በአንድ በኩል በ
ዚያው በኦሮምያ ክልል ከተማሪዎቹ ባሻገር
ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከትግሉ እየተቀላቀሉ ሲሄ
ዱ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን
ከኦሮሞ ወጣቶች አንድነት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ፍትህና ዴሞክራሲ ለሚለው ለዚህ የ
ጋራ የሆነ አጀንዳ የመንቀሳቀስ አዝማሚያ
እያሳዩ ነው፡፡
ይህ በጎ ሂደት ቀጥሎ ለዚህ ፍትህና ዴሞክራሲ ለተጠማ ህዝባችን በጎ ውጤት እንዲያ
መጣ ዛሬ የሃገር ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ሃይሎች
መክረው አንደኛ ንቅናቄው ሰፍቶ መላውን ህብረተሰብ የሚያካትትበትንና በእርግጥም የ
ማይበገር ህዝባዊ የትግል ማእበል
የሚሆንበትን፤ ሁለተኛ ደግሞ ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ምን እናድርግ በሚሉት ጥያቄዎች
ዙሪያ ተወያይተው አስቸኳይ መልስና የጋራ
የትግል ስትራቴጂ መንደፍ ይኖርባቸዋል፡፡
አንደኛ ትግሉ ሁሉን አቀፍ፣ ሁሉን አንቀሳቃሽ ህዝባዊ የትግል ማእበል እንዲሆን ም
ን ይደረግ
?
በትግል አጀንዳውም ሆነ በተሳታፊው
እየሰፋ የሄደው ትግል በዚህ እንዲቀጥል ዛሬ በዚህ ግፈኛ አገዛዝ የመብት ብቻ ሳይ
ሆን የህልውና ቀውስ ውስጥ የገቡ የተለያዩ
የህብረተሰብ ክፍሎች በሙሉ ሁሉም ብሶታቸውን እያነገቡ እንዲንቀሳቀሱ ማበረታታትና
ጥሪ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት
ስራ አጡ ወጣት ለስራ፣ ገበሬው ለህልውናው ወሳኝ ለሆነው ለመሬት ይዞታ ዋስትና፣
ነጋዴውና ኢንቬስተሩ ከሙስናና ከአድልዎ
ለተላቀቀ አሰራር፣ ሰራተኛው ለመብትና የጥቅም ጥያቄዎቹ፣ ምእመናን መንግስት በሃይ
ማኖቶች አስተዳደር ጣልቃ ገብነቱን እንዲያቆም
ወዘተ እየጠየቁ ትግላቸውን ማቀጣጠል ይኖርባቸዋል ማለት ነው፡፡
ሁለተኛ በዚህ መልክ ብሶታቸውን እያነገቡነና መፍትሄ እየጠየቁ የሚንቀሳቀሱ የተለያ
ዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉም ተራ በተራና
በየፊናቸው የሚንቀሳቀሱ ከሆነ ሁሉም ተራ በተራ የሚመቱበት አደገኛ ሁኔታ እንደሚከ
ሰት መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ይልቅ
የሚያዋጣው አካሄድ ላይ ላዩን ሲታዩ የተሰበጣጠሩ የሚመስሉት የህብረተሰቡ ጥያቄዎች
ምንጫቸው የተዛባና ጸረ ዴሞክራሲያዊው
የወያኔ ኢህአዴግ ፖለቲካ መሆኑን ተገንዝበው ብሶትህ ብሶቴ በሚል አርማ በአንድነት
ለአንድ አላማ በመቆም ሂደቱ ወደ ተባበረና
በአንድ አቅጣጫ ወደሚገፋ ህዝባዊ ትግል እንዲቀየር መሞከር የግድ ይሆናል፡፡
ሶስተኛ በዚህ መልክ የሚቀሰቀሰው ትግል ደግሞ ከእነዚህ የተሰበጣጠሩ የመብትና የጥ
ቅም ጥያቄዎች አልፎ መሄድ የኖርበታል፡፡
ለነዚህ ሁሉ ህዝባዊ ጥያቄዎች ዘላቂ የሆነ መፍትሄ የሚገኘው በሃገራችን ዴሞክራሲና
ተጠያቂነት ሲሰፍኑ ብቻ ስለሆነ የዚህ ህዝባዊ
ትግል የፖለቲካ ገጽታ ከእለት እለት እየጎላ ሄዶ የስርአት ለውጥ በሚለው አጀንዳ
ዙሪያ እየጎለበተ መሄድ ይኖርበታል፡፡
የሃገራችን ዴሞክራሲያዊ ሃይሎች ይህንን የተቀነባበረና የተባበረ ህዝባዊ ትግል ለመ
ቀስቀስ ግልጽ የሆነ ስትራቴጂ ነድፈው
መንቀሳቀሳቸው አስቸጋሪም ቢሆን ቁልፍ የጊዜው ተግባር የመሆኑን ያህል ከዚህ የትግ
ል መቀስቀስ ባሻገር ሌላም ታሪካዊ ተልእኮ
ይጠብቃቸዋል፡፡ ይኸውም የዚህን ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ ዘላቂነትና ለድል መብቃት ለማ
ረጋገጥ መወሰድ የሚገባቸውን እርምጃዎች
ይመለከታል፡፡ ይህም አንደኛ ኢህአዴግ ይህንን ህዝባዊ እንቅስቃሴ በከፋፍለህ ግዛ
ፖለሲ ካስፈለገ ደግሞ በደም ባህር ለማክሸፍ
ሊጠቀም የሚችላቸውን አካሄዶች ከወዲሁ አጢኖ ለነዚህ የሚመጥን አጸፋ ማዘጋጀት ያስ
ፈልጋል፡፡ ሁለተኛ ለዚህ ትግል አመራር
ሊሰጡ በሚችሉ ሃይሎች (በግንባር ቀደምነት የሚንቀሳቀሱ ወጣቶች፣ የፖለቲካና የሲቪ
ክ ማህበራት መሪዎች ወዘተ ላይ) አይቀሬው
የአፈና እርምጃ ሲወሰድ ትግሉን እንዳያዝረከርከውና አመራር አልባ በማድረግ እንዳያ
ከስመው ምን ስትራቴጂ እንከተል የሚለውን
ጥያቄ ከወዲሁ መመለስ ያስፈልጋል፡፡
የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲውን ለማክሸፍ አሁን በኦሮሞ ወጣቶች እንቅስቃሴ ዙሪያ የተከሰ
ተው አንድነት በጣም ተስፋ የሚጣልበት
ቢሆንም ይህ የአንድነትና የትብብር መንፈስ ዘላቂ እንዲሆንና እንዲጎለብት አንደኛ
የኢህአዴግ መንግስት ይህንን ለመሰበር በራሱ
ካድሬዎችም ሆነ በአንዳንድ ኦሮሞ አክራሪዎች የሚወሰዱና ህዝብን ከህዝብ ለማቃቃር
የሚደረጉ ሙከራዎችን ነቅቶ መጠበቅና
   (.. . .)
ALL ETHIOPIA SOCIALIST MOVEMENT (ME’ISONE )
P.O.Box 14 01 17 . D-53056 Bonn . E-M
a
il:
meisone@t-online.de
www.meison.info
___________________________________________
__________________________________________
___________________________________________________
___________________________________________________
________________________
Account Nr. 3603457585 . BLZ (Bank code number) 3
7050198
BIC COLSDE33 IBAN DE27 3705 0198 3603 4575
85
እንዳመጣጣቸው እየተከታተሉ ማክሸፍ ያስፈልጋል፡፡ ይህንን ለማድረግ በኦሮምያ በአሁ
ኑ ወቅት በአማራው ብሄረሰብ አባላት ላይ
የሚፈጸሙትን ግፎች ሁሉም ወገን – በተለይም እንዲህ አይነት ግፎች የሚፈጸሙት በኦ
ሮሞ ህዝብ ስም በመሆኑ – የኦሮሞ ዴሞክራቶች
በይፋ አውግዘው መውጣታቸውና ከዚህም ጋር ተያይዞ በአማራው ስም የተደራጁ ዴሞክራቶ
ች በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚፈጸሙትን
ግፎች በይፋ መቃወማቸው የአክራሪዎቹን ቅስም ለመስበርም ሆነ ለምንመኘው የህዝቦች
የትግግዝና የወንድማማችነት መንፈስ
መስፈንና ለትግሉ መሳካት ይህ ነው የማይባል አወንታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡ ሁ
ለተኛ ደግሞ ዛሬ ትግሉ እየሰፋ በጎንደር. በጎጃምና
በሌሎች የሃገራችን ክፍሎች እየተከሰተ በመሆኑ በነዚህም አካባቢዎች እየተፈጸሙ ያሉ
ትን አስከፊ የግድያ፣ የእስራትና የወከባ
ዘመቻዎች ሁሉም በአንድ ድምጽ ሊያወግዛቸው ይገባል፡፡
ሌላው የተባበረ የህዝብ ትግልን ለማክሸፍ የኢህአዴግ መሪዎች የሚጠቀሙበት እኩይ ዘ
ዴ በዚህ ለፍትህና መላ ህብረተሰቡን ወደ
ዴሞክራሲ ለማሸጋገር በሚደረግ ትግል ፖሊሱ፣ ሰራዊቱና የደህንነቱ አባላት ብቻ ሳይ
ሆኑ የኢህአዴግ አባላትም ሳያመነቱ በነሱ ጎን
እስከመጨረሻው እንዲቆሙ በይፋም ሆነ በስውር የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ ጠንቅቆ ማወቅና
መዋጋት
ያስፈልጋል፡፡ የቅስቀሳው ዋና
አላማ ለዚህ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ያልሆነ አጀንዳ በመስጠት ትግሉ በእነሱም ህልውና
ላይ የተቃጣ አድርገው በማቅረብ እነዚህ ወገኖች
በአልሞት ባይ ተጋዳይነት መንፈስ ተንቀሳቅሰው ይህንን ትግል እንዲወጉ ማድረግ ነው
፡፡ ይህንን አካሄድ ለመዋጋትና ለማክሸፍ
ከፈለግን በማያቋርጥ ቅስቀሳ ትግሉ ዴሞክራሲና ብሄራዊ እርቅ የሰፈነባት ኢትዮጵያ
ለመመስረት ስልጣን ላይ ተንሰራፍተው በአገርና
በህዝብ ኪሳራ የግል ጥቅማቸውን ከሚንከባከቡ ጥቂት ሙሰኞችና ጸረ ህዝቦች ጋር እን
ደሆነና በሰራዊቱም ሆነ በኢህአዴግ አባላት ላይ
የተቃጣ እንዳልሆነ፣ እነዚህ ሃይሎች በነገይቱ ዴሞክራሲያዊት ሃገራችን ቦታ እንደሚ
ኖራቸው እያበሰሩ ትግሉን እንዲደባለቁ መወትወት
ያስፈልጋል፡፡
እንቅስቃሴውን ለማዝረክረክ በአመራሮች ወይም በግንባር ቀደምነት በትግሉ የሚሳተፉ
ዜጎች ላይ የሚያነጣጥር የአፈና ውርጅብኝ
በእርግጥም የኢህአዴግ መሪዎች እንደሚመኙት (ከዚህ በፊትም በደንብ እንደታየው) የ
እንቅስቃሴውን መክሰም ወይም ህዝብ ለህዝብ
የሚጋጭበት ትርምስ መልክ መያዝ እንዳያስከትል ያለን አንድ አማራጭ፤ ተነስ ታገል
ለምንለው ህዝብ የዚህን ትግል ዘላቂ አላማ
ምንነት ብቻ ሳይሆን፤ ወደዚህ በሚወስደው መንገድ በየደረጃው የምንታገልበትን የትግ
ል አጀንዳና አካሄድ ከወዲሁ በግልጽ
ማስጨበጥና ይህ አጀንዳና አካሄድ ምንም አይነት አፈና ሊደመስሰው በማይችል ሁኔታ
በሚልዮኖች አእምሮ እንዲሰርጽ ማድረግ
ይሆናል፡፡
ለዚህ ታሪካዊና አገራዊ ተልእኮ ብቁ ለመሆን ከዴሞክራቶችና አገር ወዳድ ሃይሎች የ
ሚጠበቀው የጊዜው አንገብጋቢ ተግባር በትግል
ላይ ላለው ህዝባችን የምናሰጨብጠው ግልጽ የሆነ የትግል አጀንዳ ምንነት ላይ መምከ
ርና ለህዝቡ ይፋ ማድረግ ይሆናል፡፡ አሁን
እንደሚታየው ሁሉም በየፊናው ህዝባችንን ተነስ ታገል እያለ በሚያሰራጨው መግለጫ የ
ትም የሚደረስ አይመስለንም፡፡ በታጋዩ
ህዝባችን ፊት ታአማኒነት እንዲኖረን ከፈለግን አመራር ማለት ምሳሌነትም ስለሆነ በ
አንድነት ተነስቶ እንዲታገልና እንዲሰዋ ጥሪ
በምናደርግለት ህዝብ ፊት እኛም በአንድነት ቆመን በአንድ አቅጣጫ ለመታገል የተነሳ
ን መሆናችንን ማሳየት ይጠበቅብናል፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ የተባበር ትግል ያሸንፋል!!
ታሕሳሥ 19. 2008 ዓ.ም. (29.12.2015)

 

Leave a Reply