.

ከመላው አለም በሶሻል ሚዲያ ተሰባስበው “ኩራት በኢትዮጵያ ” በሚል ስያሜ አገራቸው ውስጥ በአቅማቸው ለመስራት የተሰባሰቡ ሀገር ወዳድ ዜጎች የቦርድ አመራሮች በፈጠሩት ችግር ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውን ዘግበን ነበር። ኢትዮጵያ ፕሮስፐረስ ይህ በሶሻል ሚዲያ ከፍተኛ ትኩረት ያገኘው አጀንዳ ዙርያ ተጨማሪ መረጃ እንደምናቀርብ በገባነው ቃል መሰረት ከሚመለከታቸው አካላት አንዱ የሆነው የንግድ ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎችን አነጋግረን ቀጣዩን ዘገባ ይዘን ቀርበናል ። “ኩራት በኢትዮጵያ ” ኑሮአቸውን በውጭ ያደረጉ 200 ዳያስፖራዎች በአግሮ እንዱስትሪ ለመሰማራት የመሰረቱት ማህበር ነው። ይህ ማህበር ከተመሰረት አንድ አመት የምላው ቢሆንም በአባላቱና በቦርድ አመራሮች መካካል በተፈጠረ አለመግባባት በአሁኑ ወቅት ስራ ላይ አይደለም። ~ይህ አክስዮን ማህበር የሚመሰርቱት አባላት ቁጥር 200 ቢሆኑም መስራች በሚል የተመዘገቡት አስራ አንድ የቦርድ አመራሮች ብቻ ናቸው። ~እነዚህ 11 ግለሰቦች ለአክስዮን የከፈሉት ገንዘብ በእያንዳንዳቸው ስም 50,000 ብር ሲሆን ውልና ማስረጃ አስገብተው ባፀደቁት የመመስረቻ ፅሁፍ ላይ ግን እያንዳንዳቸው 500,000.00 ብር እንደከፈሉ ተመዝግቧል ።ይህም በንግድ ሚንስቴር ኤክስፐርቶች ተጣርቶ የተደረሰበት ችግርና እነዚህን የቦርድ አመራሮች በህግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ከንግድ ሚንስቴር የአክስዮንና የንግድ ዘርፍ ማህበራት ክትትልና ድጋፍ አመራሮችን አነጋግረን በሰጡን ማብራሪያ ባለ አክስዮኖቹ በከፈሉት ገንዘብ ልክ አክስዮኑ ተተክሎ 200 አባላት ባለ አክስዮን ለማድረግ ብቸኛው አማራጭ በውልና ማስረጃ የፀደቀው የመመስረቻ ፅሁፍ በድጋሚ በማዘጋጀት ሁሉም አባላት ማስፈረም እና መስራች ማድረግ ብቻ ነው ብለዋል። ይህን የሰሙ የቦርድ አመራሮች ግን ከዚህ ሀሳብ ይልቅ በምንም ውስጥ ላልተካተቱ ነገር ግን በባእድ ሀገር ለፍተው ያካበተትን ጥሪት ሀገራችንን እናልማ ላሉ ሀገር ወዳድ ዜጎች በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው ማዋል ቢሆንም ይህ አካሔድ በወንጀል ላይ ተጨማሪ ወንጀል መፈፀም መሆኑ ተረጋግጦ ማህበሩ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ታግዷል በማህበሩ ስም የተቀመጠ ገንዘብ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል። ከቦርድ አመራሮችና ተበዳዮች ጋር የሚነሱትን ሀሳቦች በቀጣይ ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

NB. It was copied and pasted from the source website before it was deleted.

http://www.ethiopiantodye.com/00123-2/#prettyPhoto

Leave a Reply