ይህ የኤርትራ ተዋጊ ጀት ቆየት ብሎ የተነሳና ከኤርትራ ድረገጽ የተገኘ ነው:: ለዜናው ከፋይል ተጠቀምንበት እንጂ መቀሌ የገባው ጀት ይሄኛው ላይሆን ይችላል::
ይህ የኤርትራ ተዋጊ ጀት ቆየት ብሎ የተነሳና ከኤርትራ ድረገጽ የተገኘ ነው:: ለዜናው ከፋይል ተጠቀምንበት እንጂ መቀሌ የገባው ጀት ይሄኛው ላይሆን ይችላል::
|

(ዘ-ሐበሻ) ሁለት የኤርትራ የጀት አብራሪዎች ከነጀታቸው ትናንት መቀሌ መግባታቸውን እና ጥገኝነት መጠየቃቸውን የትግራዩ መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች ዘገቡ::
እንደዜናው ከሆነ መብራህቱ ተስፋማርያምና ኣፈወርቂ ፍሰሃየ የተባሉ አብራሪዎች ጀታቸውን በመያዝ መቀሌ ኤርፖርት ከገቡ በኋላ ጥገኝነት ጠይቀዋል::
ዲሴምበር 2014 ልምምድ ላይ የነበረ የኢትዮጵያ ሄሊኮፕተር በዋና አብራሪው አስገዳጅነት ኤርትራ ማረፉ የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ የኤርትራ ወታደሮች ጀት ይዘው መቀሌ ገብተዋል:: በተለያዩ ጊዜያትም የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ኤርትራ እየገቡ ጥገኝነት መጠየቃቸው አይዘነጋም:
:

Leave a Reply