February 20, 2017

ቤት የለለው ትግራዋይ ሁሉ የቤት ባለቤት ለማድረግ ፓርቲያችን ህወሐትና ዲሞክራሲያዊ መንግስታችን በቁርጠኝነት ወስኗል” – አባይ ወልዱ

የህወሐት አመራር በህዝብ የተጠላው ስርአቱ እድሜ ለመራዘም ታሳቢ በማድረግ ትናንትና የመኖርያ ቤት ከሊዝ ኪራይ ውጭ ፣ በማህበር ፣በግለ ሰው ሊሰጥ ከሆነ በህወሐት መቃብር ነው የሚደረግ ሲል ቆይቶ አሁን የትግራይ ህዝብ ብሎም የመላው ሀገራችን ህዝቦች የመኖርያ ቤት እጦት የወለደው ብሶት ለስልጣኑ ወይ የአፋኝ አገዛዙ እድሜ ለመራዘም በማይችልበት ደረጃ ስለደረሰና ስለሰጋ ተገድዶ እንደ የሽግሩ ቁልፍ መፍትሄ በሀገራችን ያለው የመጠልያ ቤት እጦት መሆኑ ተረድቶ ለጊዜው እንደ ማስታገሻ ወይ የእሳት አደጋ ማጥፍያ ስልት ለመጠቀም እንሆ 70 ሜትር ካሪ መሬት እንሰጣለን በማለት ዋናው አላማው ደግሞ የፖለቲካ ስልጣኑን እድሜ ለማራዘም በማድረግ እንሆ በትግራይ ክልል በ. 12 ትላልቅ ከተሞችና በ104 ታዳጊ ከተሞች 48 ሸ መተማመኛ በህወሐት አመራር ቁጥጥር በሚገኝ ደደቢት በንክ በዝግ በንክ እንዲ ቀመጥ በማድረግ እንዲሁም ለአርሶ አደሮች የመሬት ከሳ 5000 በር በድምር 53 000 ብር እያንዳንዱ ቤት ሰሪ ለመጀመሪያ እንዲ ከፍል ተገደዋል ።

በሌላ በኩል 187 000 ብር በ 12% ወለድ ለደደቢት በድርና ቁጠባ ባንክ ሊከፍሉ ውል እንዲገቡ ተገደዋል ። ይህ ብድር ከመንግስት ባንክ በ3% ይበልጣል ። ስለየባንክ እዳ ልዩነቱ በሚመለከት ካሁን በፊትም ገልጨው ነበር ።
የተከበራችሁ የኢትዮጱያ ህዝቦች አንድ አንድ ወገኖች ቀደም ሲል ዜጎች በሀገራቸው ቤት ሰርተው የሚጠለሉባት መሬት ማግኜት አለባቸው ስትል ነበርክ ፣ አሁን ደግሞ መንግስት መሬት ሲሰጠን ተቃውሞ ታነሳለህ በማለት ብዙ ወቀሳ ሰንዝሯቹሁብኛል ፣ በበኩሌ ግን ይቅርና 70 ሜትር ካሪ መሬት ከዛ ያነሰ ስፋት መሬት ቢሆን አልቃወምም ሁሉም ዜጋ ድንኳን ዘርግቶ የሚኖርባት ብትሆንም መሬት ማግኜት አለበት የሚል እምነት አለኝ ። እኔ እምቃወመው

1. የሚታደለው የቤት መስርያ መሬት ዜጎች ዜጎች በመሆናቸው የማግኜት መብታቸው የተጠበቀ መሆን እያለ የህወሐት መሪዎች እነ አባይ ወልዱና አዲስ አለም ባሌማ ግን በህዝብ እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ባደረጉት ትግል ተጽእኖ ፈጥሮባቸው ሳይወዱ በግድ እሬት እየጣማቸው መሬት ሰጥተውት እያሉ እነዚ እንደቸሩላቸው ከአምላክ በላይ ሆነው ለመታየት ለፖለቲካ ፍጆታ ሊጠቀሙበት መሞከራቸው ነው የሚያናድድ ። መቸ ይብቻ ለፓለቲካ ድጋፍ ማግኛ ዘዴ መጠቀማቸው አልበቃም ቡሎዋቸው የነሱ ዲሞክራሲ ባህሪ እንዳላቸው የውሸት ፕሮፕጋንዳቸው መጠቀምያ ማድረጋቸው ነው ።

2. ያቺ 70 ሜትር ካሪ መሬት ለመኖሪያ ቤት በቂ አይደለችም ። እነዚህ የሀገራችን ሆዳሞች ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው ግን ከአዲስ አበባ እስከ ክልሎች ያሉ ምርጥ ከተሞች ከ500 እስከ 1200 ከዛ በላይ መትር ካሬ ስፋት መሬት በመያዝ ሰማይ ጠቀስ ህንጻዎችና ቪሏዎች እንድስቲሪዎች በሞኖፖል ይዘው እያሉ ለቡዙሀኑ ተራ መጠልያ ለመስራት ሰፋ ያለ መሬት መከልከላቸው ምን ያህል ክፎች መሆናቸው ነው ። በተለይ ደግሞ የህወሐት ፣ የባአዴን ፣ የኦሆዴድ ፣ የዲህደን ፣ የአጋር ፓርቲዎች አመራሮችና ሸሪኮቻቸው የሰሩት ቤት የያዙት መሬት እጅጉን ሰፋፊ ቦታዎች ናቸው ። እንዳው ለራሳቸው ከሁለት በላይ ይዞታ መሬትና ቦታ በባለቤትነት ይዘው በአሁኑ ጊዜ ምን ሊታወጅ እንደታሰበ አላውቅም ፣ በአዲስ አበባ በጎንደር ፣ በትግራይ ፡ በባህርዳር ፣ በአዋሳ ፣ በአዳማ ፣ በወሎ በሌሎቹም ወ ዘ ተ በሚሊዮኖች ብር ቤትና ቦታ እሸጡ መሆናቸው ቡዙ ዜጎች ተቃውሞዋቸው እየገለጹ ይገኛሉ ።

3 ቤት ሰሪዎች የቤት መስርያ ገንዘብ ብድር ከሌሎች ባንኮች አወዳድረው እንዳይ በደሩ የህወሐትና ሌሎች ፓርቲዎች ኪስ ከሆኑት የብድርና ቁጠባ ሊበደሩ መገደዳቸው ነው ። መቸ ይህብቻ ገና ስሚንቶ ብረት፣ ጣውላ ፣ የሳኒተሪና የኤለክትሪክ ከጉናና ከአንፓሰል እንዲገዙ ይገደዱ ይሆናሉ ።

4 ህዝብ ለለከቲት 11 42ኛ ህወሐት የተመሰረተበት የትጥቅ ትግል የትግራይ ታሪካውነቱ አምኖ በፍላጎቱ እንደማክበር ፈንታየመሬቱ እጣ ከየካቲት ማያያዙነው።

ይህ ሁሉ ሸፍጥ ግን በትግራይ ብቻ እየተፈጸመያለ ነው። 5 ትልቁ ወንጀል ደግሞ ለአርሶ አደሮች የተወሰደባቸው መሬት ለአንድ ሜትር ካሪ ከቤት ሰሪዎች ብር 62 .00 እያለ ለአርሶ አደሮቹ ግን ይሰጣቸው ከነበረው ብር ቀንሰው 23 .00 ብር ሰጥተው 57 %ለገዥዎች ኪስ መሙያ ሆነዋል ። አርሶ አደሩ የወሰደው በር ደግሞ ሲሰላ 43%በመሆኑ የኔ ተቃውሞ ለቤት ሰሪዎች መሬት ማግኜታቸው መቃወም ሳይሆን የጭቁን አርሶ አደር ካሳ መቆረጥ የለበትም ። ለዚሁ ግፍ ቤት ሰሪዎችም ገ ከገንዘቡ ከተቀማ አርሶ አደር ጎን መቆም ነበረባቸው ። አሁንም ጥያቄ ማንሳት አለባቸው ። ከዛ አርሶ አደር ጋር ለወደፊት ም ገረቤት ሆነው ስለሚኖሩ ከወዲሁ ግንኝነታቸውን ማበጀት አለባቸው ።

6 እነዚህ አታላይ ገዥዎች ሳያፍሩ ትናትና መሬት የመንግስት ናት አንተ ህዝብ የመንግስት ጢሰኛ ነህ አርፈህ ተቀመጥ እያሉ ህዝቡን እያሻማቀቁ መሬቱ እየቀሙ በሊዝ 26 አመት ሙሉ በውድ ዋጋ እየቸበቸቡት ነረው አሁን ደግሞ ሲጨንቃቸው አሁን በአስርሺ የሚቆጠር ህዝብ የቤት ባለቤ አድርገናል ለቀረውም ከሚቀጥለው መጋቢት ወር የቤት በለቤት እናደርገዋለን ብለዋል። አሁን ይዘውት ያሉ መፎከር ደግሞ አላማችን ሁሉ ቤት የለለው ትግራዋይ የቤት ባለቤት እናደርገዋን ብለዋል ። ይህ ወደው ሳይሆን በግድ ሊተገቡሩት ናቸው ይህ እርምጃ መውሰዳቸው ደግሞ የሰላማዊ ተቃዋሚ ፓለቲካ ሀይሎች ነው ። ከመሬት መስጠት ተያይዞ ግን ከቤት ሰሪና አርሶ አደሩ ቡዙ ምዝበራ እንደሚፈጽሙ የተረጋገጠ ነው ። ግን ደግሞ ህዝብ ነቅቶ ስላለ ማሳለፍያ መንገዱ ሁሉ ተዘግተዋል ።

ከአስገደ ገብረስላሴ መቀለ ፣

12 / 6 / 2009 / ዓ ም