ስለ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ  የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ   መጽሃፍ  ብዙ ተብሎል።ሞያዊ ዉይይት ና ክርክሩ ባይከፋም፤ለፖለቲካ ፍጆታ ና ደጋፊ ለማርካት መዋሉ አልወደድኩትም።ለዛሬ ፖለቲካ ይጠቅማል በሚል በጭፍንነት መቀበል በሁዋላ መዘዙ ብዙ ሊሆን ይችላል.። ሃሳብ እንደ ሃሳብነቱ ይመረመራል እንጅ ጽሃፊ ተጠላ ተብሎ ሃሳቡ አይኮነንም፤ ተወደደም ተብሎም አትተቹት አይባልም።የዚህ አይነት አካሂያድ  ሞያዊ ያልሆነ ና አላዋቂነት ነዉ።

ወደ ጽሁፌ ልግባና የዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሃፍ በአራት ክፍሎች ከፍለን ልናየዉ እንቸላለን:

አንደኛ፡በመሪራስ አማን በላይ ተገኘ የተባለው ”ጥንታዊ’’ ብራና በመመርኮዝ ሰለ አማራ ና ኦሮሞ የዘር ምንጭ

ሁለትኛ፡  ስለ ቋንቋ ና ባህል በኢትዮጵያ

ሶስተኛ፡ ስለ ስልጣን በኢትዮጵያ

አራተኛ፡ ስለ ንግስተ ሳባ

እኔም ከላይ በተራ ቁጥር አንድ ጽሃፈው ያቀረቡትን ሃሳብ በመቃዎም  “ሃላፊንት የጎደለው ሞያዊ ያልሆነ ስራ በመረራስ አማን በላይ በዶ/ ፍቅሬ ቶሎሳ, (http://www.zehabesha.com/amharic/archives/71138) የሚል ጽሁፍ ና “በተራ ቁጥር  ሁለት የቀረበዉን ሃሳብ በመደገፍ “6 ጠቃሚ ነጥቦች ከዶ/ ፍቅሬ ቶሎሳ መጽሃፍ:”  (http://www.zehabesha.com/amharic/archives/72408, http://www.satenaw.com/amharic/archives/30377) የሚሉ ሁለት ጽሁፎች ከዚህ በፊት እንደ አቅሜ አቅርቤአልው።በዚህ ጽሁፍ አራት ነጥቦች  (ጥያቄወች) አነሳለዉ።