ሰርጸ ደስታ

በመጀመሪያ ሚዲያው ሕወሐት ውስጥ ሽኩቻ አለ ብሎ ለሕዝብ ያቀረበበት ምንጩ የማይታወቅ ከመሆኑም በላይ አላማው ምን እንደሆነ እኔን ምንም ሊገባኝ አልቻለም፡፡ ይልቁንም በይፋ የምናየው የወያኔ አሁን ላይ ያለው እውነታ ኦሮሞና አማራ መካከል ትልቅ ልዩነት በመፍጠር ለብዙ ቀሪ ዘመን ራሷን በስልጣን ለማቆየት ሙሉ ኃይሏን እየተጠቀመች ነው፡፡ እውነታው ወያኔን አለመረዳት ሳይሆን አሁን አሁን እየገባን ያለው ብዙዎች በኢትዮጵያ ሥም ለወያኔ ሥራ እየሰሩ መሁኑ ብቻ ነው፡፡ ሰሞኑን የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ በሚል አዲስ አበባን አስመልክቶ ኦሮሚያ ሊኖራት ይገባል ተብሎ የተሰራጨ ጽሁፍ ብዙዎቻችን አንብበናል፡፡ ሲጀምር ጽሁፉ ከየት እንደወጣ እርግጠኛ መሆን ያስቸግራል፡፡ ግን ከዚህ በፊት የሰማናቸው አንዳንድ ንግግሮች ነበሩ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት አንድ ፀጋዬ አራርሳ የተባለ የኦሮሞ አክቲቪስት ነኝ የሚል አዲስ አበባ የኦሮሞዎች ነች ማለቱ ብቻ ሳይሆን ብዙ ሥም ነው የሰጣት፡፡ በሽፍቶች የተገነባች፣ መጤዎች ምናምን ሲል ነበር፡፡ በቅርቡ ደግሞ አንድ የኦሮሞ የሰሞኑ ካቢኔ ሰው በፊንፊኔ ትልቅ የኦሮሞ ታወር እንሰራለን አገሩ የኦሮሞ ነው በኦሮሞ አገር ደግሞ የኦሮሞ ታወር መስራት አለብን ሲሉ አባባላቸው የኦሮሞ ታዎር ከመስራት ጋር ሳይሆን አሁንም ሌላውን መጤ ነው ሊሉ ነበር ከፉከራ ያልተናነሰው ንግግራቸው፡፡ ሰሞኑን በየድረገጹ የምናየው በአዲስ አበባ የኦሮሞ መብት በሚል የተነበበው ጽሁፍ ሆን ተብሎ በሕዝቦች መካከል ልዩነትን ለመፍጠር እንደሆነ ለማወቅ ተንታኝ አንፈልግም፡፡ ጽሑፉ በቀጥታ በኦሮሞና አማራ መካከል ለመፍጠር የሚያችለውን ሴራ እንጂ የኦሮሞን ሕዝብ ጥቅም ለመጠበቅ አደለም፡፡ 15 በመቶ ኮንደሚኒየም፣ በአዲስ አበባ ተወካዮች ምክር ቤት ከሕዝብ ቁጥሩ ሌላ 25 በመቶ ኦሮሞ ምናምን የሚሉ ሴራዎች በየትኛው ሕግና ሥርዓት ነው; የሕዝብ ተወካይ እኮ በሕዝብ ምርጫ እንጂ በኮታ አደለም፡፡ ኮንደሚኒየም 15 በመቶ ለኦሮሞ ተወላጆች የሚለውም እንዲሁ ነው፡፡ የኦሮሞ ተወላች 15 በመቶው ቀርቶበት ግን በትክክል ዘሩ ማንነቱ ሳይገለጽ ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ከደረሰው ጥሩ ነው፡፡ እስከዛሬ እንደምናያው ቅድመያ የወያኔ ትግሬዎች ቤት ካገኙ በኋላ ነው ለሌላው ዳረጎት ጣል ጣል የሚደረግበት፡፡ እሱም ለወያኔ ትግሬ አግልጋይነትን ይጠይቃል፡፡ የኦሮምኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ የሥራ ቋንቋ የሚለው ዝባዝንኬነቱ አሁንም ያልተጠየቀውን ለማደናገር ነው፡፡ የኦሮምኛ ቋንቋ የአዲስ አበባ ሥራ ቋንቋ ሳይሆን መሆን የሚገባው የፌደራል ሥራ ቋንቋ ነው፡፡ የፌደራል ከሆን የአዲስ አበባ መሆን አውቶማቲክ ነው፡፡ እየተሰራ ያለውን ሸፍጥ ያየንው በግልጽ ከምናየው ወያኔ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ሕዝብ ሥም ከሚነገዱ ብዙ ሌሎችም እንደሆነ ነው፡፡ አሁን ወያኔን ችግር ውሥጥ የከተታት አገር ቤት የአለው ሕዝብ አንድ መሆን ነው፡፡ ይህን አንድነት ደግሞ ከአላፈረሰች በተለይ በኦሞና አማራ ሕዝቦች መካከል እየተጠናከረ የመጣውን ህብረት ካላፈረሰች ወያኔ እድሜዋ አጭር እንደሆነ ታውቃለች፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ እንደ ልዩ ተጠቃሚ ሳይሆን በአግባቡ ፍትሐዊ በሆነ መልኩ በአዲስ አበባ ቦታ ቢኖረው ቢያንስ ዛሬ በወያኔ ትግሬዎች ከተያዙት ቦታ ያነሰ ቦታ ባልኖረው፡፡ እስኪ እድሉ ክፍት ይሁን አደለም አዲስ አበባ ዛሬ ሱሉልታን ለገጣፎን የመሳሰሉ ቦታዎች በማን እየተወረሩ ነው; የኦሮሞ ሕዝብ በፊንፊኔ ነባር ሕዝብ ይባል ብሎ ማለትንስ ምን አስፈለገ; ይህ ሆን ተብሎ የታሪክ ጥያቄ እንደሚያስከትል ወያኔ ስለምታውቅ ነው፡፡ ታሪክ ከተነሳ ደግሞ ወያኔ ሚኒሊክ ነው የወረረው ልትል ሌሎች ደግሞ ኦሮሞ ነው የወረረው ሊሉ፡፡ ስለዚህ ዝርዝር አልገባም፡፡ አላማው ግን እንድና አንድ ነው፡፡ በኦሮሞና በተለይም በአማራ መካከል መልሳ መለያየትን ለመፍጠር ነው፡፡

ሌላው ለወያኔ ትልቅ ራስ ምታት የሆነባት ለዘመናት አልቀየር ያላት የመረራ ቡድን ነው፡፡ ይህ ቡድን ከእስር ከወጣ ኦሮሞንና አማራን አንድ የማድረግ እድል ይኖረዋል ብላ እጅግ ትፈረዋለች፡፡ በተለይ ዋናውን መረራን ለብዙ ጊዜ አድማጭ የለውም ብላ እንጂ አስተሳሰቡ አድማጭ ከአገኘ አደጋ ሊሆንባት እንደሚችል ታውቃለች፡፡ ይህ ቡድን የኦሮሞ ሕዝብ የተለየ ጥቅም ያግኝ ሳይሆን ፍትሀዊ ጥቅሙ ይጠበቅ የሚል ልዩና በሕግም መሠረት ላይ የቆመ ነው፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ ከኦሮሞ ሕዝብ ብቻም ሳይሆን ከሌሎችም ሕዝቦች ድጋፍ አለው፡፡ በጎንደር አደባባዮች የበቀለ ገርባን ምስል ያወለበለቡት ሰልፈኞች የዚህ እውነታ ምስክር መሆን ብቻ ሳይሆን ወይኔን እጅግ ከአስደነገጣት ነገር አንዱ ነው፡፡ አስቀድማም ብታውቀውም በዚህ ያሕል በዚህ ሁሉ ርቀት ያለው የጎንደር ሕዝብ የበቀለ ገርባን ማንነት ተረድቷል ብላ አላሰበችም፡፡ ሕዝቡ ግን እያንዳንዷን ነገር ይከታተል ነበር፡፡ በቀለ ገርባ በወያኔ ቲቪ የተናገራቸው ንግግሮቹ ሕዝብ ጆሮ የገቡት ፈጥነው ነው፡፡ ሊያውም አንድ ጊዜ ብቻ በተናገረው፡፡ ዛሬ ላይ የእነ በቀለ ገርባ ቡድን ከእስር ተፈቶ ነጻ እድል ተሰጥቶት ምርጫ ቢካሄድ ኦሮምያ ብቻ ሳይሆን አማራ ወያኔ የእኔ እያለች የምትደነፋበት ትግራይ እንደሚያሸንፍ እንረዳለን፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ ያደረገው እውነት ለወያኔ አፍጦ መጥቶባታል፡፡ ሥለዚህ በውጭ ባሉ ሚዲያዎች፣ አክቲቪስቶችና ሚዲያዎች በመጠቀም አገርቤት ደግሞ የራሷን ኦፒዲዮዎችን ተጠቅማ ዳግም በሕዝብ መካከል ልዩነት እንዲፈጠር የሞት ሽረት ትግል እያደረገች ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይንና ጆሮ ነኝ የሚለው ኢሳትን በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲነሳበት ቆይቷል፡፡ ሰሞኑን ደግሞ በወያኔ መካከል መከፋፈል እየተፈጠረ ነው የሚል ወሬ እንዲናፈስለት የፈለገበትን ነገር ህዝብ በግልጽ ማዘናጋት ነው እያለ ሲቃወም ዝም በሉ ትግሉ በዚህ መልኩ እያፋጥን ነው ብሎን አረፈው፡፡ ቀጥሎ ጭራሽ ኃይሌና ኤፍሬም ሽምግልና ተጠርተዋል ተባልን፡፡ በዚህ እልህ ነበር እኔም ፕ/ር ኤፍሬምን በቀጥታ ደውዬ ማናገር ግድ የሆነብኝ፡፡ ኤፍሬም እንኳን ሽምግልና ሊጠሩ ሆነ ስለተባለውም ጉዳይ ምንም መረጃ እንደሌላቸው ነገሩኝ፡፡ ኢሳት ይህን ወሬ ማሰራጨት ለምን ፈለገ; ሰሞኑን እየተነዙብን ያሉት ወሬዎች እጅግ የሚያስተዛዝቡን ናቸው፡፡ ሁሉም የወያኔን አደገኝነት እየነገረን ነው ትንታኔውን የሚቋጨው፡፡ የ20ዓመቱ የደህንነት ሰው ነኝ የሚሉት ወያኔ እንዴት የተወሳሰበ እንደሆነ ሊነግሩን ብዙ ጥረት አደረጉ እንጂ ሚስጢር አልነገሩንም፡፡ የኢሳቱ የፖለቲካ ተንታኝ ነኝ የሚሉትም እንዲሁ፣ ሌላው ቀርቶ ወያኔን በጣት መግፋት ነው እያሉ ይናገሩ የነበሩት ኦኤምኤኑ ሥራአስኪያጅ ዛሬ ወያኔ አደገኛ ነው ይሉናል፡፡

ወያኔ ስብዕና በሌላቸው አረመኔውች ስለተሞላች አረመኔያዊ ተግባር እየሰራች ሕዝብን ማሸበር እንጂ ደህንነቷ አደለም ያኖራት፡፡ በገንዘብ የምትገዛቸው ሆድ አደሮች እንጂ ደህንነቷ አደለም፡፡ ሥሜቱን እንኳን የማይቆጣጠር ባዶዎች ነው የሞሉባት፡፡ የአማራና ኦሮሞ ሕዝብ አንድነትን ባርቆባቸው በይፋ ለሕዝብ መገናኛ የሚያወሩ፡፡ ይህ ነው ደህንነቱ እንግዲህ፡፡ ደህንነቱ ጥብቅ ቢሆን ሊመጣ የሚችለውን ባወቀች፡፡ ሕዝቡንም በተረዳች፡፡ እስካሁን ሕዝብ ታገሰ እንጂ ወያኔን አይፈራትም፡፡ ወያኔም ሕዝብ እንደሚንቃት ታውቃለች፡፡ አስከምናውቀው ወያኔ አረመኔነቷን እንደ ልዩ ሥልት ከደደቢተ ጀምራ ነው የምትሰራበት፡፡ ለዛ ተቃዋሚህን ሁሉ አጥፋ ብሎ ለተነሳው የ60ዎቹ ትውልድ የወያኔ ሥልት የተሳካላት ነው፡፡ በጭንቅላት ለሚሰራ ትውልድ ግን የወያኔን ሥልት ማፍረስ ከባድ አደለም፡፡ ችግሩ አሁንም ያ የ60ዎቹ ትውልድ በሽቶች ሕዝብን መበከል ነው፡፡ ሰውን ለመግደል ልዩ ችሎታ አይጠየቅም፡፡ ኃላፊነት የማይሰማው ወሮበላ ውጤታማነት እንደምንም ይሁን እንደምንም ለራሱ መብላት እንጂ ሌላ አደለም፡፡ ይህ ባሕሪ በኢትዮጵያውያን ብዙም ያልተለመደ ስለነበር መዘናጋትን ፈጥሮ ቆይቷል፡፡ አሁን ግን ሕዝብ በግልፅ አረመኔነታቸውን ተረድቷል፡፡ ገዳዩን ወያኔን የሚገድሉ እየመጡ ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለ ሰራዊቱም ጋር የሚቆይ ተስፋ የለም፡፡ ስለዝህ ወያኔ እስከዛሬ የክት አደርጋ ያቆየቻቸውን ለሕዝብ አገልጋይ የመስሉ የነበሩትን መጠቀም ግድ የሆነባት ይመስላል፡፡ አዛኝና የኢትዮጵያ አሳቢ መስለው ጀንራል ጻድቃን ጽሁፍ ሲያቀርቡ የወያኔ የክት ሰው እንደነበር ለማስተዋል ብዙም ሚስጢራዊ አልነበረም፡፡ ግን ያልተገለጠልን የጻድቃንን ጽሁፍ እየተቀባበሉ ሲተነትኑልን የነበሩ መገናኛ ብዙሀኖች ነበሩ፡፡ ጻድቃን እኮ ግን በድሮው አንጃ ተብለው ከተገለሉትም ነበሩ፡፡ ጻድቃን በአንጃነታቸው ከወያኔ ተወገዱ ወይስ የሚፈልጉትን ሁሉ አግኝተው ሌላ ሥራ ተሰጣቸው; በዩኤን የወያኔ የውትድርና ኮንትራክተር (ወታደርና፣ የኢትዮጵያ ንብረት የሆነውን የውትድርና ቁሳቁስ በማከራየት) ሆነው እንዲሰሩ የተደረገው በገለልተኝነት ነበር; ሥንቶች ትግሬ ያለሆኑ ኢትዮጵያውያን ገና ጥሩ የምታስብ አይመስለኝም በሚል እኮ ነው መከራ እየተቀበሉ ያሉት፡፡ ሌላውን እንተወውና ሰሞኑን የታሰረው መረራን ለማሰር ምክነያት ማግኘት አላስፈለገም ትግሬ ወያኔ የማይሆን (ለሆዱ የማይገዛ) ኢትዮጵያዊ ኦሮሞ መሆኑ በቂ ነበር፡፡ የወያኔን የሴራ ወሬ የሚያናፍሱልን ሚዲያዎች የመረራን መታሰር አንደምስራች ነገሪ ሰበር ዜና ብለው ከመናገር በቀር መረራ የታሰረበትን ምክነያት ሕዝብ እንዲጠይቅ የሚያነሳሳ ዝግጅቶች ሲያደርጉ አላየንም፡፡ መረራ በዲያስፖራው አማሮች ነን የሚሉት በሚመሩት ኢትዮጵያዊ ትግሬ ወያኔ የማይሆን ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን አማራ ያልሆነ ኦሮሞ በሚል እይታ ነበር የታየው፡፡ የእስልምናን ጽንፈኝነት በሚያልሙና አማራ የተባልን ሕዝብ እንደጠላት በሚያዩ የኢትዮጵያን መፍረስ በሚናፍቁ የወያኔ ቅትረኛ ኦሮሞው ዲያስፖራ የሚጠሉት መረራ ኢትዮጵያያዊነትን የሚደግፍና ከአላማቸው የሚያስቀር በመሆኑ አይወደድም፡፡ በዚህ ምክነያት የመረራ መታስር በዲያስፖራው ዘንድ ትልቅ ቁጣን ያስከትላል ተደማጭነትም የሚኖራቸው ትልልቅ ሰላማዊ ሰልፎች በአውሮፓና አሜሪካ ከተሞች ይታያሉ ተብሎ በየቧህያን ቢታሰብም ሲሆን አልታየም፡፡ ለሌላው የሆኑ በውል ሥማቸውን የማናውቃቸው ሁሉ ታሰሩ ምናምን ተብሎ በኢትዮጵያዊነት ሥም አሳጅበው አገር ምድሩን ቀውጢ ሲያደርጉ ታዝበናል፡፡ የዲያስፖራውን ቁልፍ የያዙት የወያኔ ቅጥረኞች ሊሆኑ እንደሚችሉ በማሰብ የመረራ መታሰር ዲያስፖራውን የተባለውን ተቃውሞ ባያካሂድ እንብዛም አያስደንቅም፡፡ የኢትዮጵያን ሕዝብ ትግል እደግፋለሁ የሚለው ዲያስፖራ እንዴት እንደባዘነ ራሱን ቢጠይቅ፡፡ ከመረራ መታሰር በላይ ለዲያስፖራው ትልቅ አለም አቀፋዊ ጫና እንዲመጣ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርግበት እድል በሆነ ነበር፡፡ መረራ 25ዓመት ሰላማዊ ትግልን ብቻና ብቻ መሠረት ያደረገ ምክነያት የማይሰጥበት ታጋይ፣ በሕዝብ ተወክሎ ፓርላማ ያገለገለ፣ በሙያውም በቀጥታ የፖለቲካ ሳይንስ ሊቅ የሆነ፣ በአላም አቀፍ ደረጃም ትልቅ ዕውቅና ያለው ሰው ነው፡፡ ይሄን ሰው ማሰር የወያኔን ቡድን ወሮበላነት ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳየት ትልቅ ድርሻ ነበረው፡፡ አልሆነም፡፡ እኛም ሞኝነታችን ነው፡፡ ዲያስፖራውን የሚመሩት ጭራሽ የወያኔ ቡድን አገልጋዮች ሊሆኑ እንሚችሉ ማሰብ ነበረብንና፡፡ ለመሆኑ ግን ለትዝብት እነዚህ ተቃዋሚ ነን የሚሉ በውጬ የሚገኙ ድርጅቶች ለይስሙላ እንኳን የአቋም መግለጫ ሲያወጡ፣ የዲፕሎማሲ ሥራ ሲሰሩ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ;

ወያኔ አደገኛ ነው የምትሉት፣ አደገኛ ሴኩሪቲ ቢኖረው ነው በአንድ ጊዜ ውሉ ጠፍቶበት በቀጥታ የአስቸኳይ ጊዜ በሚል በሕዝብ ላይ ጦር ያዘመተው; አስፈራሩልኝ ተብሎ ትዕዛዝ የተላለፈ ነው የሚመስለው፡፡ የወያኔን ሴኩሪቲ አንድና አንድ ነው አረመኔያዊ ሽብርተኝነት፡፡ የማያስቡ ቅልቦች በሕዝብ ላይ ማሰማራትና የመሣሰሉት ናቸው፡፡ እስኪ ስለወያኔ ምን የማናውቀው አለ; የደህንነቱ ሰው ባይነግሩን፡፡ ወያኔ ውስጥ መከፋፈል አለ የሚል ሰርፕራይዝ መሆኑ ነው; ሊኖር ይችላል፡፡ ግን እኛ ጅሎች አደለንም ወያኔ በዚህ ወቅት ኤርትራን አስመልክቶ ክፍፍል ይኖራል ማለት፡፡ ሲጀምር ሰዎቹ በአደገኛ ቢዝነስ የተጠላለፉ ናቸው፡፡ ከዛም በዘለለ ዘመዳማቾች ናቸው፡፡ አርከበ ብቻ ነው ሀብት ያፈራው ነው የሚሉን የኢሳቱ ተንታኝ ለመሆኑ ሌሎቹስ; ነው እንዲህ ሕዝብ ለማምታታት; ወያኔ መረራን የኦሮሞን ዲያስፖራ ከሚዘውረው ጀዋርና መጣሁ ኤርትራ ነኝ እያለ ይሄው 10ዓመት የሞላው ብርሀኑ ጋር የመክሰሷ ሚስጢርንስ ምን ታዘባችሁ; ጠላቷ መረራ ብቻ እንደሆነም እናውቃለን፡፡ ሕዝቡ ከመረራ ጋር በመከሰሳቸው እውንም የወያኔ ጠላት መስሎት እንዲከተላቸው ያደረገችው ጥረት እንደሆነ ነው የገባን፡፡ ጀዋርና ቡድኑ እንዴት ኢትዮጵያን የማፈራርስ፣ ቻርተር ምናምን እያለ የሕዝብን ትግል በረዶ ውሀ ከልሰው እንዲመክን በማድረግ ወያኔን እንደታደገ አንረሳም፡፡ ጀዋርና ቡድኑ ባይኖር ወያኔ እኮ እስከዛሬ ሊለይላት ሁሉ በቻለ ነበር፡፡ ወያኔ ይህ ውለታ ለማሰብ በቀሪም እንዲጠቅማትና ከሕዝብ ድጋፍ እንደይለየው ማድረጓ ነበር ጀዋርን ከመረራ ጋር መክሰሷ፡፡ እግረ መንገዷንም የመረራን ትግል ለማሳነስ፡፡

አሁን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሊነቃ የሚገባው ወያኔ ውስጧ እየተሸረሸ ሳይሆን አማራና ኦሮሞ ሕዝቦች መካከል እየተገነባ የመጣውን አንድነት ማፍረስ ነው፡፡ በቃ ኦሮሞና አማራ አንድ የሆነ ዕለት ወያኔ ግባተ መቃብሯ እንደሆነ ታውቃለች፡፡ እና ለዛ መስሎኝ በውጭ ያሉ ቅጥረኞቿ ይህ አንድነት እንዳይጠነክር መከራ የሚያዩት፡፡ የአማራ ቤሄረተኛ የኦሮሞ ጽንፈኛ ምናምን እያሉ አይን አውጥተው የሚያፏጩብን፡፡ ለእነሱ እኮ የእንጀራ ጉዳይ ነው፡፡ ሌሎች ደግሞ ለስለስ ብለው የሚያዘናገ ወሬ የሚነዙብን፡፡ ወያኔ አደገኛ ነው የሚሉን፡፡

ማስተዋሉን ይስጠን!

አመሰግናለሁ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!

አሜን!