በዚህ ደረጃ ተንቀናል ተደፍረናል እንዴ ለካ!

image_pdf

ከእግዚአብሔር በታች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምእመናንን ወይም መንጋውን እጠብቅ ዘንድ ከእግዚአብሔር አደራ የተጣለብኝና ለተጣለብኝ አደራ የቆምኩ የቅድስት ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ነኝ!” .. 20 28 የሚል አካል ካለ ሳይውል ሳያድር በአስቸኳይ ለዚህ የክህደት ተግባር አጸፋ መውሰድ የሚጠበቅበትን እርምጃ ወስዶ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ይፋ ማድረግ ግድ ይጠበቅበታል!!! ከታች በፎቶ (በምስለ አካሉ) ከቀረበው መረጃ ማረጋገጥ እንደሚቻለው የመናፍቁ የእነ አቦይ ማትያስ ቡድን ከመናፍቃን ጋር ባላቸው የእምነትና የዓላማ አንድነት ምክንያት በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ በድብቅ ሲፈጽሙባት ከቆዩበት የክህደትና የሸፍጥ ተግባር አልፈው ለእኛ ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያላቸውን ንቀት ለመግለጽ በግልጽ በአደባባይ ሕዝበ ክርስቲያን በተሰበሰበበት በመሀከላቸው ያላቸውን የቃልኪዳን አንድነት በይፋ ለማሳየት በሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤተክርስቲያን ከፕሮቴስታንት መሪዎች ጋራ ቅብዓ ሜሮን እርስ በእርሳቸው እየተለቃለቁ ለሕዝበ ክርስቲያኑ በይፋ በመታየት የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብርና ቅድስና አጉድፈው ተዳፍረው በማሳየት አረጋገጡ! “ክርስቲያን ነኝ!” የምንል ሁሉ ይሄንን በይፋ በአደባባይ  በሕዝበ ክርስቲያን ፊት የተፈጸመን የቅድስት ቤተክርስቲያንን ክብር ያለ አንዳች መሸማቀቅና ሐፍረት አብዝቶ የተዳፈረውን የክህደት የድፍረት አስነዋሪና ጸያፍ ተግባርም በቸልታ ልእንመለከት ይገባል ወይ??????….

ይሄንን በዝምታ ከተመለከትን በዝምታ ልንመለከተው የማይገባው የክህደት ተግባር ምን ሊሆን ነው??? ትላንትና በትናንሹ የክህደትና የድፍረት ተግባራቸው ዝም በማለታችን እኮነው ዛሬ እንዲህ ዓይነት ከባድ የክህደት ተግባር በአደባባይ በዐይናችን ስር ሊፈጽሙብን የቻሉት፡፡ ሕዝበ ክርስቲያን ሆይ! ይሄንንም ዝም ብለን ካሳለፍንውሾቹ ተኩሎቹ ነገ ላይፈጽሙት የሚችሉት ምንም የክህደትና የድፍረት ተግባር እንደማይኖር ጠንቅቀህ ተረድተህ ክርስቶስ የሞተልኝና ለእርሱ በመታመኔ በአባቱ ፊት የሚመሰክርልኝ፣ እግዚአብሔር በገዛ ደሙ የዋጃት የአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ምእመን ነኝ!” የምንል የስም ሳይሆን የተግባር ክርስቲያኖች ካለን ይሄው እምነታችንና ለክርስቶስ ያለን መታመንና ፍቅር ሚፈተንበት ሰዓት መጥቷልና እያንዳንድህ ውጣና ምስክር (ሰማዕት) ሁን! እንሁን! ዐይን ያወጣውን የክህደትና የድፍረት የተኩላ የይሁዳ ተግባር በኃይለኛ የቤቱ ቅናት መቃጠል እንቃወም!!!
ልዑል እግዚአብሔር ያለብንን የእምነት አደራ መወጣት ያስችለን ዘንድ ለሠማዕታት ለቅዱሳን እናት አባቶቻችን የሰጠውን የእምነት ጽናት፣ ፍቅር፣ ቁርጠኝነትና መታመን ያድለን! ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያንን መናፍቃኑ ከደገሱላት ጥፋት ይታደግልን! ይሠውርልን! አሜን!!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

No widget added yet.

← የኤርትራ ፈተናዎችና መፃኢ ሥጋቶች How long can Ethiopia state of emergency last? →

Leave A Reply

Comments are closed

Visit Us On TwitterVisit Us On FacebookVisit Us On YoutubeVisit Us On Linkedin