By ሳተናው
May 18, 2017 05:28

ኢትዮጵያ ሀገራችን ከመቸውም ግዜ በላይ የሰው ያለህ ትላለች! ስርዕት አልበኞች አገር እየመሩ ለሀገርና ለህዝብ የቆሙ ወደ ወይኒ የተጋዙበት ብዙዎችም እስከ መጨረሻው ያሸለቡበት ክፋ ዘመን አገራችንን ገጥሟታል::

አገራችን ኢትዮጵያ ጥቂት የማይባሉ ድንቅ የኪነጥበብ ሰዎችን አፍርታለች! በተለይ በሙዚቃው ሙያ የተሰማሩት ለሀገራቸው ያበረከቱት አስተዋፅኦ ፍፁም የሚዘነጋ አይደለም! አገር በፋሽች ስትወረር ህዝብን በማነቃቃት ብርታት ሆነዋል በሀዘን ግዜ የእንባ ማበሻ አፅናኝም ናቸው::
አስቴር አወቀን የማያደንቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብለን አንገምትም በስራዎቿ ፍቅር ያበድንም እንጠፋም:: በኢትዮጵያ ሙዝቃ ታሪክ ትልቅ ቦት አላት ሆኖም ህዝባችን በስቃይ ባለበት በዚህ ወቅት እነዚህ ከህዝብ አብራክ የወጡ አርቲስቶች ለዚህ ያበቃችውን ህዝብ ባይከፍሉትም ስቃዮን ሊሰሙት በተገባ ነበር:: አስቴርን እና ሌሎቹንም ቱጃር አርቲስቶች ለዚህ ያበቃው ይህ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ምስኪን ኢትዮጵያዊ ነው::
ግዜው በአርት ሙያ ለተሰማሩ ወገኖቻችን ፈታኝ የሆነበት ሰዓት ነው:: አንባገነኑ የወያኔ ስርዓት አርቲስቶችን ወደውም ሆነ በተፅዕኖ ከጎኑ እንዲሆኑ ሲያደርግ አይተናል! የስርዕቱ ገንዘብ ማፍለቂያ የሆኑ ድርጅቶች ጋር ማንኛውም አርቲስት ከሰራ ህዝባችንን ለሚገለው ስርዕት ጥይት የማቀበል ያህል እንደሆነ መታወቅ አለበት! እኛም የዘመኑ ባላደሮች በህዝባችን ህልውና ቁማር የሚጫወት ማንኛውን ሰው የማያዳግም እርምጃ ለመስጠት ቅንጣት አናፈገፍህም! ጥያቄያችንን ካልተረዱ አርቲስቶች መሀል አስቴር አወቀ አንዷ ዋነኛዋ ናት::
አስቴር ከዳሸን  ቢራ ጋር እዳትሰራ ወይም ውሏን እንድትሰርዝ በተደጋጋሚ ለጠየቅነው ፍቅር የተሞላበት ጥያቄ ጆሮ ዳባልበስ በማለት በጊዮን ሆቴል ዝግጅቷን አቅርባለች:: የዳሸንን ቢራም አስተዋውቃለች እኛም ቃል በገባነው መሰረት በገባችበት ገብተን የውሸት “የህዝብ ነኝ “ የሚለውን የጅል ጩህት ህዝብ ማለት ማን እንደሆነ እስኪገባት እናስረዳታለን!
በህዝባችን ሞት ላይ እየቀለዱ አሜሪካ መጦ ገንዘብ መልቀም ፈፅሞ የሚታሰብ አይሆንም እንደ ጋሽ መሃሙድ ወይም አረጋህኝ ወራሽ ህዝብ የሚልሽን ብትሰሚ እንዴት ጥሩ ነበር ግን የታየሽ አልመሰለንም:: ተወልደሽ ያደግሽበት ቀየ እሳት ጎርሶ እሳት እየተፋ ህዝብሽ በአንባገነኖች የሞት አዋጅ ታውጆበት እንዴት አስችሎሽ ይሆን “ከዚም ከዛም አይደለሁም” ያልሽው? ማህል ላይ መቆም አይቻልም! ወይ ከህዝብ ወይም ከገዳዮቹ ሁኝ! በሁለት ቢላ መብላት ዋጋን ያስከፍላል::
በዚህ አጋጣሚ የአስቴር ሰለባ የሆናችሁ ፕሮሞተሮች እጅግ በጣም እናዝናለን የወያኔን ስርዕት ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ውስጥ የተፈጠረ ክስተት ስለሆነ እንደማትፅፅቱ ተስፋ እናረጋለን:: ለደረሰባችሁ ኪሳራ በሙሉ አስቴር አወቀ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል::
ከአስቴር አድናቂዎች
ህዝብ ያሸንፋል!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!