በቴዲ አፍሮ ጉዳይ – ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም -ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ

image_pdf

May 19, 2017

ቴዲ አፍሮን ቃለ-መጠይቅ ያደረገለት የEBC ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ ስራ ለቀቀ! (የስራ መልቀቅያ ደብዳቤውን ይዘናል)

ጋዜጠኛ ብሩክ እንዳለ በቴዲ አፍሮ ጉዳይ እኔና EBC ተለያይተናል ሲል ዛሬ አርብ በፌስ ቡክ ገጹ በለጠፈው ደብዳቤ – ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም ብሏል:: የስራ መልቀቅያ ደብዳቤውን ያንብቡ፡፡

#ብሩክ #እንዳለ
(11/9/2009)
እኔና #EBC ተለያይተናል
https://www.facebook.com/birukendale
ላለፉት አራት ዓመታት #ከኢቢሲ ጋር ደጉንም መልካሙን ግዜ ተካፍያለሁ 
ከሰሞኑ ከተከሰተው(#የቴዲ #አፍሮ) ጉዳይ ጋር ተያይዞ ግን ከህሊናዬ ጋር እየታገልኩ ልቀጥል አልችልም፡፡
ጉዳዩ እንድን የኪነጥበብ ሰው ማቅረብና ያለመቅረብ ጉዳይ ባቻ አይደለም፡፡ ጉዳዩ የጋዜጠኝነት ልዕልናንም የሚጋፋ ሆኖ ስላገኘሁትና ብዙዎች መሰዋት የከፈሉለትን ሙያ ክብር ለመስጠትም ጭምር ነው እዚህ ውሳኔ ለይ የደርስኩት፡፡
ያለፉትን ስድስት ቀናት በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳሳለፍኩ የማውቀው እኔ ነኝ(ግዜው ሲደርስ እናየዋለን)፡፡
እዚህ ውሳኔ ላይ ስደርስ
-በጋዜጠኘነት ሙያ ውስጥ ላላችሁ
-የጋዜጠኝነትን ትምህርት በየዩኒቨርሲቲዎች ለምትማሩ ተማሪዎችና ለምታስተምሩ መምህራን
-መላው የኢትዮጵያን ህዝብን በህሊናዬ እያሰብኩ ነው፡፡
ለኢቢሲ አጠቃላይ ሰራተኞችና በተለያዩ መንገዶች ከጎኔ ለነበራችሁ ሁሉ አመሰግናለሁ
ዝርዝር ሂደቱን በቅርቡ እንመለከተዋለን፡፡
ስራ ፍለጋው ተጀምሯል

No widget added yet.

← በደደቢቱ ማኔፌስቶ የተቀመጠውን ኦርቶዶክስን የማፍረስና ምንፍቅናን የማንገሱ ሴራ በከፋ መልኩ ቀጥሏል ” ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ – ተስፋዬም ተነሳ” – ተስፋዬ ሲያትል ግብቶ የሚዲያ ረሃብተኛ ሆነ!! →

Leave A Reply

Comments are closed