ትርጉ ም

ጌ  ታቸው ረዳ (ኢትዮ – ስማይ አዘጋጅ – Ethio Semay)

ማክሰ ኞ 7/11/2017
ባለፈው ቅዳሜ 7/8/2017 በርከት ያሉ ኤርትራ ውስጥ መሽገው የነበሩ የቤንሻንጉል ተዋጊ ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ሃይሎች ከኤርትራ ሲሸሹ ከኤርትራ ድምበር ጠባቂ ሃይሎች ለ30 ደቂቃ ያህል የቶክስ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ፤ 40 የሚያክሉ ወደ ሱዳን ድምበር መድረሳቸው እና ለመሸሽ ሲሞክሩም ቁጥራቸው ያልታወቁ ተቆርጠው ከቀሩ ከነዚህ ሃይላትም በኤርትራ ወታደሮች የቶክስ ልውጥ ተከበው እንደነበር “ዜና ስምረት” ከተባለ ኤርትራ የዜና ማሰራጫ እንደተገኘ መግለጻችን ይታወቃል። ከነዚህ ተቆርጠው ተከብበው በቶክስ ፍጥጫ ቀርተው የነበሩ ተዋጊዎች ሁኑታ በውል እስካሁን ባይታወቅም፤ በጠቅላላ እስካሁን ድረስ 95 የቤንሻንጉል ተዋጊ ሃይላት ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኝ ሌላኛው ታዋቂ የኤርትራ ተቃዋሚ ሃይል “ራዲዮ ወጋሕታ” የተባለ ራዲዮ ጣቢያ በዛሬው ዕለት ማለትም በ7/10/2017 ሰኞ አስታዉቋል

የቤንሻንጉል ነፃ አውጭ ድርጅት የተባለ ኤርትራ ውስጥ መሽጎ የነበረ ሃይል በሁለት ቀን ውስጥ ማለትም ሓምሌ 8 ቅዳሜ ከቀኑ 2 ሰዓት 2017 እና ሓምሌ 10 ሰኞ እስካለው ጌዜ ድረስ በሱዳን በኩል አድርገው ከ95 ተዋጊ ሃይላት ሚያክሉ እጃቸውን ሰጥተው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ተዋጊዎቹ ኤርትራ ውስጥ በነበሩበት ወቅት እጅግ በጉልበት ስራ ተጠምደው ለኢሳያስ አገልግሎት አንዲያበረክቱ ይገደዱ እንደመነበር እና ስርዐቱ ከውስጥ ‘ኩፉኛ የበሰበሰ በመሆኑ፤ ተስፋ የሚያስቆርጥ ሁኔታ ሆኖ፤ እጅግ ደካማ በመሆኑ እንኳን ለኛ ራሱንም የመከላከል አቅም የሌለው የሰው እጥረት ኩፍኛ የሚታይበት ስርዓት ነው’፡ በማለት ገልጸዋል። ከሁሉም በላይ፤ ኢሳያስ የኢትዮጵያ አንድነት ለማናጋት የማይፈነቅለው ድንጋይ እንደሌላ ስንታዘብ ቆይተናል። በማለት እንኚህ የቤንሻንጉል ተዋጊ ሃይሎች በተደረገላቸው ቃለ መጠይቅ አብራርተዋል፤ ሲል ራዲዮ ወጋሕታ ገልጿል። ተቆርጠው ቀርተዋል የተባሉ ሃይላትም ካሉ ስለ ሁኔታቸው እየተከታተልን ይፋ እናደርግላችኋለን።

ትርጉም ጌታቸው ረዳ (ኢትዮ- ስማይ አዘጋጅ – Ethio Semay) ምንጭ ራዲዮ ወጋሕታ። getachre@aol.com