July 21, 2017

  

ገዢው ፓርቲ ሕግ ወጥ በሆነ መንገድ የደነገገውን መንግስታዊ ዘራፊነትን በመቃወም በአዲስ አበባ በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ተቃዉሞዎች እየተጠናከሩ ነው። አገዛዙ በአንዳንድ ከተሞች ሕዝቡን ጠርቶ የማግባባት ሥራ እየሰራ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ነጋዴዎችን እያስገደደ ሱቃቸውን እንዲከፍቱ ማስፈራራቱን አላቆመም። አንዳንድ ሱቆችም ላይ “ታሽገዋል” የሚል ወረቀት ለጥፈዋል።

ከዚህ በታች  በወሊሶና በጭሮ/አሰበ ተፈሪ ሕዝብን ለማግባባት የተደረጉ ስብሰባዎች ናቸው። በወሊሶ የኦህዴድ ባለስልጣናት ከሕዝብ ለቀረበላቸው ጠንካራ ጥያቄ ምላሽ መሰጥት አቅቷቸው ሲቸገሩ የነበረ ሲሆን፣ ለጠየቃችሁት ጥያቄ መልስ ይዘን እንመለሳለን ብለዋል። ህዝቡም “ ለምን እንናተ መልስ መሰጥት አትችሉም ? ሌላ ጋር መሄድ ምን አስፈለጋቹህ ?” ብሎ ቢያፋጥጣቸውም ኦህዴዶች ያለ ሕወሃት ፍቃድ ምን ማድረግ ስለማይችሉ፣ ምላሽ ሊሰጡ አልቻሉም።

በጭሮ ባለስልጣናቱ ህዝቡ ስራዉን እንዲጀመር ለማስገደድና ለማስፈራራት ነበር የሞከሩት። ሆኖም በአንድ ልብ ያለውን ጠንካራ አቋም ነበር የገለጸላቸው።

አገዛዙ አንድ የተካነበት ነገር ቢኖር፣  ከሕዝብ ከፍተኛ ግፊት ሲመጣበት፣ የሕዝብ ግለቱን ለማብረድ “እንወያይ፣ እንነጋገር፣ ችግር እንዳለብን እናወቃለን፣ ችግሮቻችንን እንፈታለን ፣ እናስተካክላለን ..” በሚል  ህዝብን የመደለል ባህሪው ነው። ይሀንንም በማድረግ በሕዝብ መካከል የሐሳብ መከፋፈልና የሐሳብ መበታተን እንዲኖር ረድቶታል። በኦሮሚያ ተነስቶ የነበረዉ ተቃውሞ በጣም የተደራጀ  ስለነበረ አገዛዙ በቀጥታ የኃይል እርምጃ ነበር የወሰደው። በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖችን ሲገድል በአሥር ቺህ የሚቆጠሩትን ገድሏል። በአማራ ክልል የተነሳውን እንቅስቃሴ ግን፣ የሃይል እርምጃ ከመዉሰድ በተጨማሪ፣   ህዝብን በመደለል ታክቲኩ በአንዳንድ ቦታዎች ነገሮችን ለማቀዝቅቀዝ የቻለበት ሁኔታ ነው የነበረው። እነ በረከት ስምኦን በየጊዜው ነበር ሕዝብን ሰብስበው ለማናገር ሲሞክሩ የነበሩት። በጥቂት ሳምንታት ጉዜ ዉስጥ ብቻ በረከት ስምኦን፣ ሶስት አራቴ  ህዝብን አነጋግሯል። ያኔ እግር ስር ወድቀው መለመን ነበር የቀራቸው።

በድለላ ነገሮችን ካረገቡና በቂ ጊዜ ካገኙ በኋላ ፣ በረከት ስምኦን ድራሹ  ጎንደር ሊታይ አልቻለም። ከዚያ በኋላ ደረጃ በደረጃ፣ በጥናት ወጣቱን እያሰሩ፣ ክልሉ በኢኮኖሚ እንዲመታ አደረጉ።

አሁንም ያንን ስትራቴጂ ነው እየተጠቀሙ ያሉት። ሕዝብ ከገዢዎች በስብሰባ የሚሰጠው ድለላና ባዶ ተስፋ ተቀብሎ መቀመጥ የለበትም። በሜዲያ የግብር ተመኑ ተግባራዊ እንደማይሆን እስኪነገር ድረስ ፣ ግምቱ መሻሩ በሜዲያ እስኪገለጽ ድረስ፣ ህዝብ ማቆም ያለበት አይመስለኝ። ህዝብ ካቆመ በርግጠኝነት የተባለውን ግብር ይከፍላል። እነርሱ የበላይነት አገኙ ማለት ነው። ያንን አያድርገው። ለምን ቢባል በሕዝቡ ላይ በመከራ ላይ መከራ ስለሚጭን።