July 20, 2017 06:21

Dek island lake Tana in Ethiopia On the banks of the island is lying an old traditional boat made with papyrus

Dek Island, Lake Tana In Ethiopia –

 Man on the traditional boat made with papyrus lake Tana in Ethiopia

Man On The Traditional Boat Made With Papyrus,

Lake Tana In Ethiopia –

 

Bathing Zege Peninsula lake Tana in Ethiopia

Zege Peninsula, Lake Tana In Ethiopia –

Fisherman on the traditional boat made with papyrus lake Tana in Ethiopia

Fisherman On The Traditional Boat Made With Papyrus,

Lake Tana In Ethiopia –

Dek island lake Tana in Ethiopia

Dek Island, Lake Tana In Ethiopia –

 

Fisherman on a traditional boat made with papyrus lake Tana in Ethiopia

ይህን ደብዳቤ የምጽፈው እንዴው አንዱ የርሶ የቅርብ የማህበራዊ ሚዲያ ተላላላኪ ካየው ብየ እንጅ እርሶ ይህን የሚያዩበት ግዜ እንደሌሎት አውቃለሁ ምክንያቱም እርሶ የጌቶቾን ትእዛዝ በማስፈፀም ስራ ረፍት የለዎትም፤ የርሶ ሰው አይቶ ባይነግርዎትም ይህ ትውልድ በእርሶ እና በወያኔ የስልጣን ዘመን ጣና ሃይቅን ያክል ሃብት እንደተቀማ ማስታወሻ ሁኖን ያልፋል።

ጣና ሃይቅ በሃገርም ይሁን በአለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቅ ሃብት ነው። በአለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት(UNESCO)ስር በብዝሃ ሂወት ሃብት አያያዙ እና የተለያዩ ብቸኛ የሆኑ የአሳ ሃብት የያዘ በመሆኑ እንዲሁም ለተለያዩ አእዋፍት መገኛ በመሆኑና የተለያዩ የግብርና ዘር ጄኔቲክ መገኛ በመሆኑ በ ዩኔስኮ ይታወቃል።

ከዚህ በተጨማሪ

** በስነ ምህዳር አያያዙም የአባይ ወንዝ መገኛ፤

**ከ67 በላይ የአሳ ዝርያ የያዘ ከነዚህም ውስጥ 70% የሚሆነውን የአሳ ዝርያ በጣና ሃይቅ ብቻ የሚገኝ እና የትም አለም የሌለ፤

**ከ217 በላይ የወፍ ዝርያዎችን የያዘ፤

**ሃገር በቀል ዛፎች እንደ ሰሳ፤ብርብራ፤ዋንዛ መገኛ

**ሃገር በቀል ለሆኑ የግብርና ምርቶች እንደ ኑግ፤ጤፍ፤የጫካ ቡና የመሳስሉት የጂን መገኛ በተለይ ደግሞ ዘጌ እና ጉረር

በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፍም

** በጣና ሃይቅ ዙሪይ ከሚኖሩት 2,031,820 ህዝቦች ውስጥ 15,000 ህዝብ በጣና ሃይቅ ደሴቶች ውስጥ ይኖራል።

** ከ 6000 በላይ አሳ አስጋሪዎችንም በማስተናገድ የስራ እድል የፈጠረ

** ከ 13ኛው ክፍለ ዘመን ወደ ኋላ የሚያስጉዙን የሃገሪቱን ታሪክ የያዙ ጥንታዊና ባህላዊ ገዳማትንና ቤተክርስቲያንን በቁጥርም ከ20 በላይ ደሴቶችን እና ገዳማትን አቅፏል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ካሉት ሐይቆች ትልቁ፤ ከአፍሪቃ ደግሞ በስፋቱ ሦስተኛዉ መሆኑ ይነገርለታል። ጣና ሐይቅ፤ የአባይ መገኛ ብቻ ሳይሆን መጓጓዣም ሆኖ ያስተናግዳል በቱሪስት መስህብነቱም ሃገሪቱንም ሆነ ህዝቡን እየጠቀመ ይገኛል ከ 2 ሚሊዮን ህዝብ በላይም ከሃይቁ በሚገኝ ጥቅም ይተዳደራሉ።

ይህን ሁሉ ሃብት ነው እንግዲህ በጣና ዙሪያ የምናጣው
ካለፉት ጥቂት የማይባሉ ዓመታት ወዲህ ይህ ታላቅ ሐይቅ በመጤ አረም ተወሯል፤ በዉስጡ የሚያስተናግደዉ ብዝሐ ሕይወትም እንግዳ ክስተት አደናግሮታል።

በመሆኑ፤ በእርሶ እና በመሰሎቾ የስልጣን ዘመን ይህ ህዝብ ካጣው እና ከተወረሰው እንዲሁም ከተቀማው ሃብትና ንብረት በላይ የሆነውን ጣናንም እየተቀማ እንደሆነ እንዲገነዘቡት ያስፈልጋል።

ይህን የምለው የክልሉ ነዋሪ ህዝብ ከደረሰበት የሃብትና የንብረት ዘረፍ አንጻር ሌላው ቀላሉ ነው ማለቴ ሳይሆን ጣናን ካጣነው የማንመልሰው ሃብት እንደሆነ ስለማውቅ ነው። ይህንም ያልኩት ተማሪ በነበርኩበት ወቅት ባይኔ እያየሁት የደረቀውን የአለማያን ሃይቅ ታሪክ ስለማውቅ ነው። ስለ ኢትዮጵያ ሃይቆች መድረቅ በርግጥ ገዥው መንግስትና እርሶ ምኖትም ላይሆን ይችላል ነገር ግን ህዝቡን ደግፍት ህዝቡ ሃብቱን ይፈልገዋል ይህ ካልሆነም ከመሬቱ ቀጥሎ የጣና ሃብቱንም ይህ ትውልድ በእርሶ የድንጋይ ዘመን እንደተቀማ እንዲያውቁት ያስፈልጋል። እንደሚታወቀው በእርሶ እና በመሰሎቾ የስልጣን እና የድንጋይ ዘመን ይህ ትውልድ ለታሪክ የሚሆኑ ብዙ ነገሮቹን አጥቷል።

ጣና ሃይቅን የማስተዳደር ስልጣን የማን ነው?????

በነገራችን ላይ በዚህ ዙሪያ አከራካሪ ጉዳዮች ቢኖሩም እንዲህ እንየው በፌድራሉ ህገ መንግስት አንቀጽ 50 (2)መሰረት በመርህ ደረጃ የፌድራሉ መንግስት ከፍተኛ የስልጣን አካል የፌደራሉ መንግስት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው። ተጠሪነቱም ለሃገሪቱ ህዝብ ነው። የክልል ከፍተኛ የስልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለህዝብ ነው። ከዚህ በተጨማሪም በአንቀጽ 51(11) መሰረትም የፌደራሉ መንግስት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚያስተሳስሩ ወይም ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንዞችን እና ሃይቆችን አጠቃቀም ይወስናል ያስተዳድራል ይላል ። ይህ ከሆነ እንግዲህ ጣናን በተመለከተ ድንበርም ሆነ ክልል ተሻጋሪ ባለመሆኑ ምከንያት ይህን የውሃ አካል የክልሉ መንግስት ያስተዳድራል የሚል መደምደሚያ እንዳናቀርብ የፌድራሉ መንግስት አዋጅ 197/2000 የሚል የሃግሪቱን የተቀናጀ የውሃ ሃብት የማስተዳድር እኔ ነኝ የሚል ህግ በማውጣቱ የክልሎችን ስልጣን የውሃ ሃብትን ለማስተዳደር መልሶ የወሰደው ይመስላል ይህ ጉዳይ ጥልቅ የሆነ የህግ ክርክር ያለበት በመሆኑ እዚህ ላይ እንተወው ። ዋናው ነገር ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት አቶ ገዱ የሚያስተውል ልቦና ካለዎት የክልል ከፍተኛ የስልጣን አካል የክልሉ ምክር ቤት ነው፤ ተጠሪነቱም ለህዝብ ነው ይላል የርስዎ መንግስት የድንጋይ ዘመን ህግ። ስለዚህ ይህ ከሆነ የህዝቡ ጥያቄ ጣናን የሚያክል ሃብት እንዳጣ እየተናገረ በመሆኑ ተጠሪነታቹህ ለህዝብ ከሆነ የህዝቡን ጩኽት ስሙ። የተቀማነውን ጣናንም ከህዝቡ ጎን ሁናቹህ መልሱልን ።

የብአዴን ምክትል ሊቀመንበርና የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
በርግጥ የጣና ሃይቅን ጉዳይ በተመለከተ እኔ የአለም አቀፍ የውሃና የአካባቢ ህግ ሁለተኛ ድግሪየን በምሰራበት ወቅት እኔ እና ጓደኞቸ ባደረግነው ጥናት በጣና ሃይቅ ዙሪያ የተጋረጡት ችግሮች እንዲህ በቀላሉ የሚታለፉ ባለመሆናቸው ችግሮቹ መፍትሔ ባለው መንገድ የእርሶ መንግስት መልስ ቢሰጡበት መልካም ነው ይህ ካልሆነ ግን በአለም አቀፍ ደረጃ በ ዩኔስኮ የተመዘገበ ቅርስ ቢወድም ሲያስተዳድረው የነበረው እርሶ እና የእርሶ መንግስት ነገ ከተጣያቂነት እንደማያመልጡ እንዲያውቁት።

የተለያዩ ምሁራንም በጣና ላይ ጥናት በማድረግ ለክልሉ መንግስትም ይሁን ለፌድራሉ መንግስት ቢያቀርቡም መልስ እንዳላገኙ አውቃለሁ ስለዚህ ሌሎች ቀጣይ እርምጃዎችን ትተው የእርሶ መንግስት አሁን ጣናን የወረረውን አረም በጉልበቱ ከሚታገለው ምስኪን ህብረተሰብ ጋ ሁነው መፍትሔ ይሰጡበት ዘንድ የህዝብን ችግር እና ጥያቄ ለማይሰማው ለእርስዎ እና ለአዛዦቾ ጥያቄየን አቀርባለሁ። በርግጥ በእናንተ የስልጣን ዘመን የህዝብ ጩኽት በዝሆን ጀሮ ዙሪያ ከምትጮኽው የቢንቢ ድምፅ ያነሰ ነው። በርግጥ በህዝብ የተመረጠ እና ለሃገር የሚያስብ መንግስት ቢኖረን ኑሮ ይህ የጣና ሃይቅ የህልውና ጥያቄ ማቅረብ የነበረበት መንግስት እንጅ ህዝቡ አልነበረም። ጣናን የተቀማው ትውልድ ተስፋ የሚያደርገውም በህዝቡ ጥያቄ ላይ ተመስርቶ የእርሶ መንግስት መልስ መስጠት ሲጀምርና ለተግባራዊነቱም በዘርፉ ምርምር የሰሩ ምሁራንን አቅርቦ አማክሩኝ ማለት ሲጀምርና ለተግባራዊነቱም ግዜ ሳይፈጅ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ነው። ይህ ካልሆነ እንግዲህ በእኔ የድሜ ዘመን በአይኔ የሁለተኛውን ሃይቅ መድረቂያ ቀን እጠብቃለሁ።

(ደግ ደጉን ያሰማን)

#SAVE_LAKE_TANA