ከ 1997 ዓ.ም. ጀምሮ ተቃዋሚዎች ፕሮግራሞቻቸው  ውስጥ ጭምር ፣ኦሮሚፋ ፣ ለኢትዮጵያ ከአማርኛ ቀጥሎ ሁለተኛ የስራ ቋንቋ አንዲሆን አቅውማቸውን ሲያሳውቁ፣ የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት ግን አስካሁን በዝምታ አልፎት እንደነበር  የሚታወቅ ነው ።

ባለፈው ዓመት በሰፊው የኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞና በሁለቱ መሃል ጅማሮ ያሳየው የትግል ትብብር አንቅልፍ የነሳው የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት፣ ይሄንን ለማምከን በርካታ ዘዴዎች በመሞከር ላይ ይገኛል።

ባለፈው ዓመት በሰፊው የኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በአማራ ክልል የተነሳው ተቃውሞና በሁለቱ መሃል ጅማሮ ያሳየው የትግል ትብብር አንቅልፍ የነሳው የህውሃት/ኢህአዴግ መንግስት፣ ይሄንን ለማምከን በርካታ ዘዴዎች በመሞከር ላይ ይገኛል።

ከግንዛቤ እጥረት በመነሳት  አናድንድ ወገኖች በዚህ የህወሓት/ኢህአዴግ  ወጥመድ ሲጠለፉ እየተስተዋለ ቢሆንም፣ አብዛኛው ግን የወጥመዱን ምንነት በመገንዘብ ፣ትኩረቱን በህወሓት የበላይነት በሚመራው ኢህአዴግ ላይ በማድረግ፣ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰሞኑን አንደ አዲስ በርካታ የኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች  እየተስፋፋ ይገኛል።

ከግንዛቤ እጥረት በመነሳት  አናድንድ ወገኖች በዚህ የህወሓት/ኢህአዴግ  ወጥመድ ሲጠለፉ እየተስተዋለ ቢሆንም፣ አብዛኛው ግን የወጥመዱን ምንነት በመገንዘብ ፣ትኩረቱን በህወሓት የበላይነት በሚመራው ኢህአዴግ ላይ በማድረግ፣ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰሞኑን አንደ አዲስ በርካታ የኦሮሚያ ክልል ባሉ ከተሞች  እየተስፋፋ ይገኛል።

ወቅቱ የሚጠይቀው ይሄንን የህዝብ ምሬት ወደ ተደራጀና የተቀናጀ አቅጣጫ በመምራት፣ አስከፊውን የኢህአዴግ ስርዓት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጫንቃ ላይ ወደማንሳት ማምራትን ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች ይሄንን በመሬት ላይ ያለ ሁኔታ በመጠቀም ሕዝቡን ወደ ማደራጀትና እየመሩ ማታገል ካልሄዱ ግን፣ ግብታዊ ትግልና የገዥውን መንግስት ጥላቻ ብቻ ወደ ተፈለገው ድል አያደርስምና፣ ትልቅ ኃላፊነት ከፊታቸው ተደቅኗል። የሁሉም ትኩረት አዚህ ላይ አንዲሆንና ፣ ትኩረት ለማሳት በህወሓት/ኢህአዴግ የሚወረወሩትን መሰናክሎች ምንነታቸውን በመገንዘብ ችላ ብለው አንዲያልፉ ወቅቱ ይጠይቃል።