ግዜው 1967-8 ነበር። በኢትዮጵያ የመሬት ስሪት ሰፊ ለውጥ የታየበት ወቅት ቢሆንም በአንጻሩ አገሪቱ አይታ የማታውቀው መንግስታዊ አመጽም እያደገ የመጣበት ግዜም ነበር። ከማይረሱ የመንግስት አመጾች ውስጥ። ሕዳር 11 ቀን 1967 ዓም ግዜአዊ ወታደራዊ ደርግ ከስድስትወራት በፊት በቁጥጥር ያዋላቸው ታላላቅ የሀገሪቱ የቀድሞ መሪወች እና የነጉሱን ቤተሰቦች የረሸነበት ቀን ነው። ሁሉም በሚሰኝ ብዙወቹ ወደእስር የተወረወሩት በፈቃዳቸው ምንም አይነት የእንቢታን ወይንም የማንገራገር ሁኔታ አላሳዩም። ሁሉም በሚባል ጠላት አገራችንን በወረረ ግዜ የየድርሻቸውን መልካም አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሲሆኑ። ከመካከላቸው እንደነ እራስ መስፍን ስለሽ አይነቶች ደግሞ በአርበኝነቱ ጥሩ አስተዋጸኦ ያደረጉ ጉምቱ አርበኞችም ነበሩበት። ከነዚያ አርበኞች መካከል እንደነ ጀኔራል አቢይ አበበ አክሊሉ ኃብተወልድ፣ አካለወርቅ ኃብተወልድ እና ተመሳሳይ ለዚሕች ቅድስት አገር የሚቻለውን ያበረከቱ ከመሃልቸው ነበሩ። በተለይ ጸሀፊ ትእዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድ አገሪቱ ብቻ ሳትሆን ክፍለሀጉሩ ካፈራቸው ፓን አፍሪካውያን ትቂቶቹ እንደነ ክዋሜ ኑኩሩማ፣ ፓትሪስ ሉሙባ አይነቶቹ ውስጥ አንዱ ነበሩ። እናም እነዚያ ታላላቅ ሰወች ነበር በእብነበለ ፍርድ በዚያች አንድ ምሽት ተረሽነው ዜናው በጠዋት የተላለፈው። ብዙ ዜጎች እቤት ዘግተው ሙሾ አውርደዋል። በእርግጥም የክፉ ዘመን ጅማሮነቱ አጠያያቂ አልነበረም።

በያትውልድ ያነን አሰራር የተቃረኑት የትግል አይነቱንም ያኔ የለወጡ ወይንም ያሰቡት ይመስላል። ትግል ማለት መጽሀፍ ቅዱስ ይዞ ይቅርታ መጠየቅ እንዳይደለ ሁሉ። በጀብደኝነት ምንም ሳይዘጋጁ ባፍ ጢሙ የታጠቀንም መግጠም አይደለም። ትግል ማለት የሰላም ዘንባባ ይዞ ጎሮ ወሸባ ማለት ሳይሆን ፍጥጥ ያለ እና ደም አፍሳሽ ግብ ግብ የሚታይበት፤ አሞት የሚፈተንበት፣ የጥሩ መሪወች አመራር የሚስተዋልበት አውድማ ነው። እናም ያኔም አገዛዙ በሰላም እጅ የሰጡትን ሚኒስቴሮች እና ባለ ልዩ ማእረግ መኮነኖችን፣ አባት አርበኞችን እና የአገር ዳር ድንበር የጠበቁ አድባሮችን ከረሸነ በኋላ ያሳየው እና የቀጠለበት ያነኑ የአመጽ ጎዳና ህግ አልባ ነጻ እርምጃ በተባለ እና ኋላም ቀይ ሽብር በተሰኘ አመጻ ነበር። ያ መንግስታዊ ሽብር እንዲሆን ያስተማረን ጥይትን በጥይት መክት አለያ ትጠፋለህ የሚል ምልክት ነበር። የኋላ ኋላ የሆነውም ያው ሆነና የኢትዮጵያውያን ደም፣ ያውም የለጋ ወጣቶች ደም በጎዳና ፈሰሰ። እሬሳቸው በየ መንገዱ ተጣለ። ያኔ ነው እንዲህ አይነቱን መረን የለቀቀ ግፍ መመከት አስፈላጊ ብለው የያትውልድ ወጣቶች ያገኟትን ሽጉጥ የወለወሉ። ባዶ እጅ ከመታረድ አንድ ይዞ መውደቅ ወደሚል የተረማመዱ። አንዳንድ አደናቋሪወች እንደሚሉት ሳይሆን ሁኔታው አስገድዶ ወደ ዚያ የከተታቸው።

በአንጻሩ አገር ሊሰነጥቁ በዘር ጥላቻ የተነሳሱት የነ (ሹምባሽ፣ ቁልባሽ) ልጆች በዝቅተኝነት መንፈስ ሲሰቃዩ ቆይተው አጋጣሚውን በመጠቀም አገር ለመሰንጠቅ ከከባቢ አረብ አገራት ጋር ዶልተው፤ ለሲያድባሬ እና ኑሜሪ ቃል ኪዳን ገብተው አጋጣሚውን ተጠቀሙበት። ፍትህ፣ ዴሞክራሲ፣ ሰብአዊ መብት ያሉት የአገሪቱ ልጆች በየከተሞች በጥይት ሲደበደቡ። እነወያኔ እና ግብረአበሮቻቸው እራሳቸውን በአረብ ፔትሮዶላር ያደራጁ ገቡ። መሳሪያ፣ ስንቅ እና ትጥቅ ከአረብ አገራቱ ገባ። የአሜሪካን እና የእንግሊዝ መልእክተኞች ወደሱዳን ከሰላ መመላለሱን ያዙት። በርሐብ እርዳታ ተመካኝቶ የምእራባውያን ገንዘብ ለነዚህ ድርጅቶች እንደመና ፈሰሰላቸው። በጎን ለስልጣኑ ብቻ ያለው ማህከላዊ መንግስትነቱን የያዘው ወታደራዊ ክፍል የአገሪቱን እንቁ ልጆችን ማጥፋቱን፣ በእየ እስርቤቱ ማጎሩን ተያያዘው። ወያኔወች እና ሻብያወቹም አገዙት። እነገብረሕየወት እና መላኩ ተፈራ ተባብረው የጎንደርን ወጣት እንዳረዱት ሁሉ። እነ ካሳየ አራጋው፣ አሊ ሙሳ አይነቶችም የማሀል አገሩን አቅማቸው እስኪችል ገደሉት፣ በዶዘር በቆፈሩት ጉድጓድ አፈር አለበሱት። ከዚህ ተያያዥ እና ቀዩ መንግስታዊ የጅምላ ጭፍጨፋ ከመጀመሩ አመት ተኩል ቀደም ብሎ የታየ ፋሽስታዊ ወንጀል ልጥቀስ። ቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ይባላሉ። አገውምድርን ወክለው የህግ መወሰኛ አባል ነበሩ። ግዜው ስላስቸገራቸው አኩርፈው ከቆዩ በኋላ ወታደራዊው መንግስት እንደሚፈልጋቸው ሲሰሙ ሸፈቱ። የሸፈቱትም በባህርዳር አውራጃ በአቸፈር፣ እና ሜጫ ወረዳወች ከፊታውራሪ አውደው አበሻ ጋር በመሆን ነበር። የሸፈቱት አንዳንዶች እንደሚሉ ለመረበሽ ሳይሆን ፍትህ ይመለስ በማለት ነበር። የግዜው መንግስት ወደሰሜን ዘምቶ ገንጣይ አስገንጣዮችን ከመመከት ይልቅ ያለ የሌለ ሀይሉን በነዚህ የአገሪቱ አባት አርበኞች ላይ አሰለፈ። ሀምሌ 12 በእለተ ሚካኤል በዋለው ውጊያ ቆላ አምቦ ላይ ቀኛዝማች ስሜነህ ደስታ ቆስለው ወደቁ። የመንግስቱ ካድሬ እንደምርኮኛ ለመያዝ አልፈቀደም። ትእዛዝም ሰጠ እና የጠላት ግዜ አርበኛው ቀናዝማች ስሜነህ አንገታቸው ተቆረጠ። በግልጽ ፒካፕ አንገታቸው ተይዞ በዚያ እምነት ባለው ሕዝብ አገር በዳንግላ፣ ዱርቤቴ መራዊ እና ባሕርዳር እየተዞዟሩ እንዲታይ ሆነ። ይህ ነበር የነበረው ግፈና መረን የለቀቀ ብልግና። ይህን ያዩ ወጣቶች ያላቸውን ይዘው በመንግስት ላይ የወጡትም ከዚህ ግዜ በኋላ ነበር። በእርግጥም ትግሉም ሆነ ግብግቡ አዲስ በመሆኑ በቂ ዝግጅት ስላልነበር የወጣቱ ትግል ለሁለት አመታት አርድ አንቀጥቅጥ ሆነ ከመዲናችን እስከ ሁሉም ከተሞች ቢጎመራም አረመኔነት አይሎ ለመረታት በቅቷል። ዛሬም ትግል ስንል ትግል ቁርጠኝነትን ይፈልጋል። መሞትን እና ሞትን መድፈርንም የግድ ይላል። መታሰር፣ መገረፍ፣ መሰቃየት ሁሉ የዚሁ አንድ ፓኬጅ ነው።

በተመክሮ ያየነው ከዘመን ዘመን አንባገነኖች ከምር ተይዘው እስካልተመከቱ ድረስ መግደል ዋናው ፍቱን የስልጣናቸው ማራዘሚያ መፍትሄ አድርገው ይይዙታል። እናም የድሀን ልጅ መግደል እንደተገቢ ሆኖ ይወሰዳአል። ይህን ለማቆም እራስን በጥሩ አመራር አደራጅቶ አይቀሬውን ግብ ግብ መግጠም ደግሞ የግድ ነው። ከዘመን ዘመን የሚሸጋገር ግፍን ለማቆም የአንዴ የምር ትግል ይፈልጋል።

ዛሬ የትግል አይነቱ ተቀይሯል። ዜጎች ከመጥፋት እራስን መከላከል ግድ ሆኖባቸዋል። ሕወሐት ቋንቋ የማያውቁ አጋዚ የተባለ ጦር ፈጥራ ያለምንም ወንጀል ዘር እያጥፋች ነው። ጠላት የሚል የዘር ጠላት የሌለ ጠላት ፈጥራ ላለፉት 26 አመታት ብዙ ግፍ ፈጽማለች። ከሁሉም የአገሪቱ አካባቢወች አንድ ዘርን እንዲሳደድ፣ እንዲጠላ፣ ሌት ከቀን በመስበክ እና በፕሮፖጋንዳ አጋጭታለች። ዜጎች ተወልደው ባደጉበት ቀየ ተንሱ ተብለው ወደማያውቁት የእውር ጭፍን ጉዞ እንዲያደርጉ ተደርጎ መዳረሻ ሳይኖራቸው የአውሬ እና የበሽታ ተጠቂ ሆነው እረግፈዋል። ይህ መቆም አለበት። ሊቆም የሚችለውም በልምምጥ፣ ወይንም በእውሸተኛ እርቅ ሳይሆን ከምር በሚደረግ አመጻዊ ትግል ነው። ሕወሀት የምታውቀውም ያነን ብቻ በመሆኑ። ትግል አይነቱም ሁኔታውም ተቀይሯል። አለም በሁለት ሀይሎች በተከፈለችበት ዘመን የተራዘመ ትጥቃዊ አመጽ የተለመደ ነበር። ግዜውም በመላ አለም የነጻነት ትግሎች የፈኩበት እና በሁሉም ጠርዝ የሚካሄዱበት ዘመን ስለነበር። ድጋፍም እንዲሁ ካንዱ ከሁለት አንድ ጎራ መርጦ ድጋፍ ይገኝ ነበር። ዛሬ አለም በአንድ ልእለ ሀይል ስር በመሆኗ መፍትሄውም እንደዚያ አማራጭ አልባ አንድ ወጥ ሆኗል።

የእኛን አገር እና ሕዝባችንን በሀይል የያዘችው ሕወሐት እንደጎማ እራሷን እያጣጠፈች ለአንድየው ልእለ ሀይል አድራ ሕዝብን ለጥ እና ሰጥ አድርጋ ለመግዛት ቆርጣ የተነሳች ናት። አመጽ እስካልተነሳባት ትንፍሽ ያለውን ሁሉ ወደ እስር እየወረወረች አስራም እየገረፈች፣ ባለም ያልታየ አሰቃቂ ወንጀል እየፈጸመች ዜጋን አንገት ማስደፋቱን ተያይዘዋለች። በሰላም መኖር ካልተቻለ አምጾ መሞት ነጻነት ነው። የዚህች ግፈኛ ጸረ ሕዝብ ድርጅት የበላይነት መቆም ካለበት የሚቆም በሁለመናዊ አመጻዊ ትግል ብቻ ነው። ይህን አምነው ለተነሱ ታጋዮች ሁሉ ድጋፉን እና ትብብሩን መለገስም አገራዊ ግዴታ ነው። የታሰቡ እና የታለሙ አመጾች በከተሞች እና በገጠሮች መፋፋም ይኖርባቸዋል። የተናጠሉ ትግል አያዋጣም። ሕወሐት አናሳ ቡድን እንደመሆኗ በሁሉም የአገሪቱ ጠርዝ ልትወጠር ይገባል። ያኔ ቁመቱም፣ ወርዱም ስለሚያጥራት ትወገዳለች።

ዛሬ እንዳየነው ሌላውን ለመግደል ከአንዱ ልደራደር፣ ልታረቅ የሚል የተለመደ ዘዴዋን ትጠቀማለች። ለአለፉት 12 ወራት የጎንደርን እና የጎጃምን ወጣት ተማሪወች፣ አራሽ ገበሬወች ስትጨፈጭፍ ከርማለች። ቁጥሩ የት የሌለ ወደ እስር ሰዳለች፣ ገርፋለች፣ በየደጃፉ በግፍ ገድላለች። ዛሬ በኦሮሚያ የተነሳሳውን ትግል ለመመከት አዘናጊ መፈክር በሎሌወቿ ተዘይዶ አማራን ከትግሬ የማስታረቅ ትያትር መቀሌ እየተከናወነ ነው። ይህ ሲሆን በጎንደር ሁሉም ቀበሌወች የሚካሄደው ወያኔያዊ ግድያ እንደቀጠለ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በባሕርዳርም ግድያው አላቆመም። የከተሞች አመጽ መልክ ይዞ፣ ጠላትን ከወዳጅ ለይቶ ከተከናወነ ጥሩ መፍትሄ ነው። ዛሬ ትናንት የነበረው የገንዘብ እና የሎጅስቲክስ ችግር ላይኖር ይችላል (ከታሰበበት እና መተባበር፣ መተጋገዝ ካለ)

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!