July 25/2017

አሁን ከፍተኛ ግርግር ተፈጥሯል፡፡ የህዝብ ድል እየተቃረበ ነው መላው የሀገሪቱ ህዝብ ያስቆጣው የቀን ገቢ የግብር ትመና እሳቱ እየተቀጣጠለ ቄራ ደርሷል፡፡ በአዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ቄራ ትልቁ የገቢያ አዳራሽ ከ500 በላይ ሱቆች በኡሁኑ ሰዓት አንከፍትም በማለት የተቀናጀ አድማ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ሁሉም ነጋዴ በአንድ ድምጽ እየዘጉ በመውጣት ላይ ሲገኙ አካባቢው በፖሊስ ኃይል ተከቧል፡፡ ነጋዴው መሮታል የዘረፋ ግብር ተጭኖብን አለመክፈት መብታችን ነው በሚል ከስርዓቱ አመራር ከፖሊስ እና ከባለ ጉዳይ አካላት ጋር ጭቅጭቅ ተፈጥሯል፡፡

                                                                                  

ድል ለጭቁን ህዝብ ዘንድሮ መላቀቅ የለም ቄራ አንበሳ !

ሳተናው