በተነሳው ቃጠሉ አካባቢው በጭስ እየተሸፈነ ይገኛል

July 25, 2017 

(EMF – 25 ጁላይ 2017) የአማሮ ህዝብ (ኮሬ ጎሳ) እና በጉጂዎች መካከል

ከእሁድ (23 ጁላይ) ምሽት ጀምሮ ከባድ በሆነ የድንበር ግጭት መቀስቀሱን ወደ ስፍራው የተጓዙ እማኞች አረጋግጠዋል።   ከሁድ  ምሽት ጀምሮ በተነሳው የጎሳዎች ግጭት እስከአሁን ያልበረደ ሲሆን በግጭቱ ሳብያ በርካታ ቤቶች በመቃጠል ላይ መሆናቸውን ስፍራው ድረስ ስልክ በመደወል ለማረጋገጥ ችለናል።

በፎቶው ላይ እንደሚታየው  በተነሳው ቃጠሉ አካባቢው በጭስ እየተሸፈነ ይገኛል።

የአማሮ  መንገድ በግጭቱ ሳብያ  ስለተዘጋ ወደ ዲላ ከተማ መውጣትም ሆነ ወደ ወረዳዋ መግባት እንዳልተቻለ የአይን ምስክሮቹ ገልጸዋል።  የጸቡ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በውል ባይታወቅም የሚመመለከተው አካል ጉዳዩን ችላ እንዳለውም ለማወቅ ተችሏል። አንዳንድ ታዛቢዎች ወያኔ አሁን ከገባበት ማጥ ለመውጣት ሲል እንዲህ አይነት ግጭቶችን ሆን ብሎ እንደሚያስነሳ ይናገራሉ።

የጎሳ ፖለቲካን በሃገሪቱ ላይ የዘራው የህወሃት ስርዓት በጎሳቆች መካከል በሚደረግ ግጭት ሳብያ ራሱን በስልጣን ለማቆየት እየተጠቀመ መሆኑ አይዘነጋም።  በአሁን ሰዓት በመላ ሃገሪቱ ኢፍትሃዊ የሆነውን የግብር አዋጅ በመቃውም  የተነሳው የስራ ማቆም  አድማ እና  አመጽ  አገዛዙን እየነቀነቀው የሚገኝ ሲሆን – እልቂት እያስከተለ ያለው በጉጂ እና በአማሮ የተከሰተው ግጭት አስተዳደራዊ መፍትሂኤ ያገኛል ተብሎ አይገመትም።