ከብርሃንደጅ ሃሰን 

7August 2017 

  1. የአቶ መርሻ ዮሴፍ አርዕስት ፥ ለጥቁር ሕዝብ ፣ለአፍሪካውያን ፣ለራሳችን (ለኢትዮጵያውያን) መጭትውልድ በማሰብ ኢትዮጵያን ጠብቀን እናቆይላቸው!! አደባባይ የወጣበት ቀን ባይጻፍምእኔ ካገኘሁት ሶስት ሳምንታት አልፎታል 

    2)የተቺ የአቶ (አቢቹ ነጋን) አርዕስት ፥ አቶ መርሻ ዮሴፍ ከኑዛዜ በፊት ፤ኢትዮጵያ ፤ዕውነት፤ ተመክሮና ትምህርት ይቅደም

    ቀን ሰኔ 23/2009 .ም 

    ሁለቱም ጽሁፎች ያገኘኋቸው ከተለያዩ ኢትዮዲያስፖራ ህትመት ድረገጽ/print media ነው ። በግዜ እጥረት ምክንያት ወዲያውኑ አእምሮዬን ሰብስቤ በቅጡ ላነባቸው ስላልቻልኩ በኮምፒተሬ በያቆይልኝ ማኅደር አስቀመጥኳቸው ። 

አቶ መርሻ በግል (in person)ባይሆንምበዝናቸው ፣በምስላቸው ፣በጽሁፋቸው ፣ንግግር ሲያደርጉ በድምጻቸው ወዘተ..አውቃቸዋለሁ ። 

አቢቹ የብዕር ይሁን እውነተኛ ስም እንዲሁም በየትኛው ዕድሜ ክልል ውስጥ እንዳሉ ባላውቅም ከስማቸው በፊት የወል የአክብሮት ቅጽል የሆነውን ‘አቶ’ እጠቀማለሁ ።

አቶ አቢቹ ነጋ ቀይ ወይ የቀይ ዳማ ፣ጥቁር ወይ ጠይም ፣አጭር ወይ ረዥም ፣የኅዝብ አጋር ወይ የሌላ ይሁኑ አይሁኑ አላውቅም ። 

በብዙኋን ጭንቅላት/ሃሳብ እና በብዙኋን ድርጅት የማምን ሰው ስለሆንኩኝ ጽሁፍ/ፎች በኮፒተሬም ሆነ በሌሎች ልማዳዊ ማኅደሮቼን የማከማቸበት ወይም የማቆይበት ምክንያት ከዚያ ጽሁፍ ወይም ከእነዚያ ጽሁፎች አንጻራዊ፥ እውቀት ፣ጽንሰሃሳብ ፣ግንዛቤ ፣ምልከታ ወዘተ..አገኛለሁ ብዬ ስለማምን ነው ። 

ስለሆነም ግዜ አግኝቼ የአቶ መርሻን ጽሁፍ ደጋግሜ በጥሞና አንብቤ በጨረስኩ ማግሥት የአቶ አቢቹን ጽሁፍ ቀልቤን ሰብስቤና መላልሼ ሳነብ ከመርሻን ጽሁፍ ይዘት ጋር የማይዛመድ ፤ከእውነት የራቀና በኢሃቅ የታጨቀ ጽኁፍ ሆኖ አገኘሁት ። 

ማሳሰቢያ ለአንባቢያን 

          1. የአቶ አቢቹ ነጋን እና የእኔን ጽሁፎች ከማንበባችሁ በፊት የአቶ መርሻን ጽሁፍ ልብ ብላችሁ እንድታነቡ አደራ እላለሁ 

         2。አቶ አቢቹ ያተኮሩት በመርሻና በድርጅታቸው ኢአፓ ላይ እንጂ በጣም ብዙ ዘርፈ ባለውና አድማሰ ሰፊውን የመርሻን ጽሁፍ ላይ አይደለም

          3. እኚህ ፀሐፊ የርዮት ዓለም አሰላለፍ እውቀታቸው ግራየተጋባና የዋኅ ፖለቲከኛ ናቸው 

          4. ጽሁፋቸው ተጨባጭ ባልሆኑ ሃሳብዊ ድግግሞሽ የታጨቀ ነው 

           5.እርስ በርሳቸው መልስ በሚሰጣጡ፣ በሚጋጩ፣ በሚላተሙ፣በሚቃረኑ ወዘተ አሳቦች የተዋቀረ ጽሁፍ ነው 6.የሥርዓተ ነጥቦች፣የሆሄያት፣ የምጻረ ቃላት (አብሪቬሽን) ወዘተ. መሥፈርቶች ያላማላ ጽሁፍ ነው ። 

  1. የአቶ መርሻ ጽሁፍ የአገራችንና የዓልምን ሁለግብ ችግሮችን ያ/ይህ ቀራቸው በማሰያኝ ቅኘት፣ዳሰሰ፣ ምልከታ (with multitudinal outlook) እና በምጥቅ ሃስቦት (with meta thinking) የተጻፈ ጽሁፍ ነው ። ቢያሰፉት ኖሮ አንድ መጽሃፍ የሚወጣው ፣የጠለቀ እውቀት የሚያስጨብጥና በእንግሊኛም ሆነ በአማርኛ ለሚጻፉ ጽሁፎች ለዋቢነት የሚያገለግል ጽሁፍ ነው። በመሆኑም ብርቱ ፀሐፊ እንዳልሆንኩ ባውቅም አጨማልቄም ቢሆን የሚታዩኝን የአቶ አቢቹ ጽሁፍ ግድፈቶችን እንዳንጸባርቅ ኅሊናዬን አስገደደኝ ። ነገር ከሥሩ ውሃ ከምንጩ እንደሚባለው እርማቴ/ትችቴ አቶ አቢቹ ለጽሁፋቸው ከሰጡት አርእስት እጀምራለሁ ። ይኽውም፡– አቶ መርሻ ዮሴፍ ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵያ፤ ዕውነት ፤ተመክሮ ፤ እና ትምህርት ይቅደም” 

    እንደ እኚኅ ጻሃፊ አመለካከት አቶ መርሻ እነዚህን ቃላት የተሸከሙትን ወይም የያዙትን መልዕክት ‘ክኅሎት’ የላቸውም ወይም አያሟሉም ነው የሚሉት/ለው ። በሌላ አነጋገር አቶ መርሻ ለኢትዮጵያ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለሃቅ የቆሙ አይደሉም ባይ ናቸው። 

    “ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵና ዕውነት ይቅደም ”

    መልስ ፦ አቶ መርሻ ኢትዮጵያ፣የኢትዮጵያ ሕዝብና እውነትን ባይወዱ ወይም ባያስቀድሙ ኖሮ በእርሳቸው የዕድሜ ዘመን ኢትዮጵያን ከገዙ ከሦስቱ ጨቋኝ ሥርዓቶች ከአንዳቸው ወይም ከሁለቱ ወይም ከሦስቱም ሥልጣን ተጋርተው ፣ የሞቀ ትዳር ይዘው ፣በተደላደለ ቁሳቁስና በሞቀ ቤት መኖር ይችሉ ነበር ። እንዴት አንድ አገሩን ፣ሕዝቡንና እውነትን ያላሥቀደመ ዜጋ ከዩኒቨርስቲ ተማሪነት ዕድሜ እስከ አዛውንትነት ዕድሜ ለሃምሳ ዓመታት እየታገለና እየተንከራተተ ይኖራል?? በሦስቱምአምባገነናዊ የመንግሥት ሥርዓቶች ለኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ስላጣው (መልካም አስተዳደር፣ፍትኅ፣ ሰባአዊና ፖልቲካዊ መብትች፣ የህግ የበላይነት ወዘተ..) ዕውነታዎችን ለማስከበር በመታገል በሕይወት ላይ ካሉት አንድ የአቶ ‘መርሻን ክኅሎት ያልው/ያላት ወይም የላቀ/የላቀች ሰው ይጠቁመልኝ !

    ከኑዛዜ በፊት ተመክሮና ትምህርት ይቅደም ተመክሮ ሲባል ፥ አንድ ሰው ከተጓዘበት የሕይወት ውጣ ውረድ ያካበተውን ወይም የቀሰመውን – 

    ተጨባጭ ልምድ ፣ግንዛቤ ፣ እውቀት ወዘተ..ማለት ይመስለኛል ።አቶ አቢቹ አቶ መርሻ እነዚህን ተመክሮዋቸውን አላጋሩንም ወይም አላስተማሩንም የሚሉ ከሆነ እጅግ በጣም ተሳስቷል። እንዴት?

    መልስ ፦1) በጽሁፍዎ ገጽ አንድ አንቀጽ ሦስት ፦ “…….ካካበቱት ልምድ ተነስተው ይህኑን ትውልድ ለመምከር እና ለማስተማር መከጀላቸው ተገቢ ነው ። ምክንያቱም ግለሰቡ የመረጃ ፣የልምድ እና የተመክሮ ቤተመዘክር ናቸውና” በማለት አቶ አቢቹ ራስዎ መስክረዋል ። 

    2) አቶ መርሻ ከላይ በሠፈረው አርእስት ለኢትዮጵያውያን ያቀረቡትን ውስብስብ ጽሑፍ የተመክሮዋቸው ውጤት ነው (is a product of practical or discursive wisdom) 

    3) በጽሁፍ ተገልጾ ባይነገርምየአቶ መርሻን ‘ተግባርና ማንነት’ ራሱ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ዕንቁ ተመክሮ ነው ።

    ገጽ አንድ አንቀጽ አንድ፦ “ከጽሁፋቸው መገመትና መረዳት እንደሚቻለው ከፖለቲካው መድረክ ራሳቸውን በጥሮታ መልክ ያገለሉ አሊያም ‘ለማሸለብ’ (hibernate)ያሰቡ ይመስላሉ። 

    ማሸለብ በነጠላ ጥቅስ የእኔ የተቺው ነው።

    መልስ ፦ማሸለብ ማንቀላፋት ወይም መሞት ይመስለኛል። እገሌ አሸለበ ሲባል ፣ እገሌ አንቀላፋ ወይም ሞተ ማለት እንደሆነ እርዳለሁ ። አቶ መርሻ የአገራቸውና የሕዝባቸውን ኅልውና አደጋ ላይ መሆንን አስጨንቋቸው ለመፍትሄ ቀንና ለሊት ሲሯሯጡ ነው የሚታዩት እንጂ አላንቀላፉም ፤ከዚህ ዓለም በሞት አልተለዩምም ።

    ገጽ አንድ አንቀጽ 3  “ይህ ‘ሰፊ ኑዛዜ’ አዘል ምክርና ተመክሯቸው ……..ዘግይቶ የመጣ ቢሆንም እንዲሁ ከሚቀር መደረጉ ……..መልካም ነው ።” የሰፊ ኑዛዜ ነጠላ ት/ጥቅስ የእኔ የተቺው ነው ።

    መልስ፦ በመርሻ ዕድሜ ያሉ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ የሌላ አገር ዜጎች በቋንቋቸው ለአደባባይ (for the public) ሲጽፉ የመሞታቸው ኑዛዜ ነው ያሰኛልን? ይህ አባባሎ ማንም አሚን አይለውም ያዝንብዎታል እንጂ። ብረገብነትና አርቆ አሳቢነት የጎደለው አመለካከት ነው ።

    ጽ ሁለት አንቀጽ 1 ፦ “ ‘የአክራሪ ፖለቲከኞች’ ባሐሪ የሚአስተምረንም ይህንኑ ሐቅ ነው ። ምሳሌ ለመጥቀስ ካስፈለገ መኢሶን ፣ህወሃት፣ ‘ኢሃፓ’፣ ፖልፖት ፣ ማኦዝም ፣አፓርታይድ ወዘተ በዚህ አቋማቸው የተካኑ ምስክሮች ናቸው ።”

    መልስ ፦የአክራሪ ፖለቲከኞች’ ያጠረው ነጠላ ት/ጥቅስ የእኔ ነው ። በደፈናው አክራሪ ፖለቲከኞች የሚባል ርዮት ዓለም የለም ። ከእነዚህ ውስጥ የትኞቹ ግራ አክራሪ ፣የትኞቹ ቀኝ አክራሪ ፣መሃል ግራ ፣መሃል ቀኝ ብልው ቢለዩ ጥሩ ነበር ። 

    ሕአፓ’ ነጠላ ት/ጥቅሱ የእኔ ነው። ኢሕአፓ ለመጻፍ ፈልገውን ? ደጋግመው ኢሃፓ ብለው ጽፎዋልና ያስተካክሉ !! የካቦዲያው ፖልፖት፣የትኛውም አገር የአፓርታይድ ሥርዓት መሪዮች፣ ህወሃትን ጨምሮ የትኛውም አገር ጠባብ ብሄተኞች ፣ጁንታው መንግሥቱ ሃይለማርያም ወዘተ..ቀኝ አክራሪዮች ናቸው።

    ገጽ ሁለት አንቀጽ 4፦ “ .አብዮት ልጆቿን ትበላለች ብለው’ እነመርሻ እንድሰበኩት ሁሉ አሁን ደግሞ የዚያ ግራ ዘመም ፖለቲካ ቅሪት አገሪቱን ጨርሶ ሊበላት መቃረቡስ ለምን አልታያቸውም።” 

    መልስ ፦ ‘አብዮት ልጆቿን ትበላለች ብለው’ ነጠላ ት/ጥቅሱ የጸሃፊው ነው ። 

    1) ኢሕአፓ ይህንን አላለም ፤ ይህንን መፈክር ያሰሙት መንግሥቱ ሃይለማርያምና ካድሬዎች (ለዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ፣ለሕግ የበላይነት ፣ለፍትኅ ፣ለእኩልነት ፣ለስላም ወዘተ ይጮኁ የነበሩትን ለጋና ሎጋ ወጣትች ሲጨፈጭፉና ሲረሽኑ ያሰሙት የነበረ መፈክር ነው ።ይህንን መፈክር ሲያሰሙ ፣ አንዳንድ ቀልደኞች ‘ውይ እንድ 
    ድመት! ’ እያሉ ይሳለቁባቸው ነበር ፤የዚያ ዘመን ሰው ካልነበሩ እውነትን ከሚናገር ሰው ይጠብቁ ። “Revolutions Devour Their own Children” የተሰኘው ጽንሰ ሃሳብ ከየት እንደተጀመረ ፣መቼ እንደተጀመረ ፣የተባሉት ምክንያት ለማወቅ ታሪክ ያንብቡ ። 

    2) አገራችን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ለደረስችበት ቀውስ ተጠያቂ ቀኝ አክራሪው ወይም ፀረሕዝቡ መንግሥቱና አክራሪ ብሄርተኛው ወያኔ/ህወሃት እንጂ ግራ ዘመሙ መርሻና የመርሻ ድርጀት አይደሉም ፤እይታዎን ያስተካክሉ ! እውነትን ይከተሉ

    ገጽ ሁለት አንቀጽ 4  “ …..ጥቂት የተደራጁ አላዋቂ አክራሪ የግራ ፖለቲካ አቀንቃኞች ኢሕአፓ ፣ መኢሶን ፣ሕወሃት ፣ሻቢያ ወዘተ በሃገራችን እና በሕዝባችን ላይ ያደረሱትን ጥፋት እና እልቂት በቀላሉ የሚገመት አይደለም።” 
    መልስ ፦
    እዚህ ጋ ከጠቀሷቸው የፖሊቲክ ድርጅቶች አንዳቸውም አክራሪ ግራ(far left or radical left) አይደሉም ። ሕወሃት ቀኝ አክራሪ (far or extreme right wing)እንጂ ግራ አክራሪ አይደለም ፡፡ ሕወሃት አክራሪ ብሄርተኛ ነው ፤የሱ ጎሳ ያልሆኑትን ሁሉ የሚጠላ፣ የሚገል፣የሚያሸማቅቅ፣ በእሥር፣ በበሽታ፣ በድኅነት ወዘተ.. የሚቀጣ (Nazism,neo-Nazism ,Fascism,neo-Fascim,Racism etc) አቻዎቹ ናቸው። 

    ሻቢያ = ኢሳያስ አፈወርቅ ማለት ስለሆነ በጭካኔውና በሕዝቡ ላይ ከሚፈጽመው ግፍ አኳያ ሲታይ አምባገነን ነው ፣ ፀረሕዝብ ነው ፤ ከመንግሥቱ ሃይለማርያም እምብዛም አይለይም ።በመሆኑም ቀኝ አክራሪ (right wing reactionary) ነው ።

    Yet,he is the darling democrat comrade of G 7

    ገጽ ሦስት አንቀጽ 2 “…….ከምዕራቡና ከምሥራቁ ዓለም በበለጠ በሃገራችን ፖለቲካ ትልቁን ሚና እና ተጽኖ ያደረገው የዛ ትውልድ ለመሆኑ መቀበል ከእያንዳንዳችን ይጠበቃል ። አሁንም እያደረገ ይገኛል።” 

    መልስ ፦ ያ ትውልድ ሲባል መሬት ላራሹ፣ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብት ይከበር፣ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ይኑረን፣የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ፣ ትምህርት ለሰፊው ሕዝብ ይዳረስ ፣ ማኅበራዊ ፍትህ ፣አንድ ስው አንድ ድምጽ በሚል መተክል ሕዝባዊ መንግሥት ይኑረን ወዘተ..በሎ የታገለው ትውልድ ይመስለኛል ። እርስዎ ያ ትውልድ ሲሉ በፀረሕዝቡ መንግስቱ ሃይለማርያም አጋፋሪነት የደርግ ሥርዓት እና ጎሰኛው የወያኔ ሥርዓት አጅበው ያንን ትልቅ እራዕይ የነበረውን፣ጀግናውን፣ የነቃውና በትምህር ዓይኑን የከፈተውን ትውልድ የጨፈጨፉትን ነው የሚሉት? አዎን ኢትዮጵያችንን በምብርክክ ያስኬድዋት የእነዚህ ሥርዓቶች ቁንጮዎችና አሽክሮቻቸው ናቸው ።

ገጽ ሦስት አንቀጽ 2 “……ከአቶ መርሻም በድርጅት አባልነታቸውና እንድ አንድ ፖለቲካ አዋቂነታቸው የበለጠ እንጠብቃለን። ”

መልስ ፦ አንድ የአንድ አገር ዜጋ ከለጋ የተማሪነት ዕድሜው እስከ አዛውንት ዕድሜው ለተወለደበትን አገር ሕልውና ፣ለሕዝቡ (ደኅንነት፣መብት፣ፍትኅ፣ ማኅበራዊ ኑሮ መሻሻ ፣ለመልካም አስተዳደር ወዘተ..)ከመታገልና ለዚያ ሕይወት ከመስጠት የላቀ ምን ይጠበቅበታል? አቶ መርሻ ይህንን እያደርጉ ነው ያሉት። የአቶ መርሻ ድርጅት ኢአፓም ኅልው ከሆነበት 1964 .ም ፤በተለይም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይፋ ከሆነበት እ..1967 .ም ጀምሮ እስካሁን ለ 42 ዓመታት ከላይ ለተጠቀሱት ግቦች እየታገለ ያለ ደርጅት ስለሆነ ከዚህ የበለጠና የተለ ምን እንዲያደርግ ይጠበቅበታል?

ገጽ ሦስት አንቀጽ 2  ”…ያ ትውልድ የሠራቸውን በጎና መጥፎ ተግባሮችን ነቅሰን መነጋገር ይኖርብናል። ይህ ሲሆን ነው አዲሱን ትውልድ መምከርና ማስተማር ዮምንችለው።” 

መልስ ፦የዚህ መልስ እንዲሆኖት የአቶ መርሻን ጽሁፍ፣ በገጽ 11 ኢትዮጵያ በሚል ኑዑስ አርእስት ሥር ‘እኛነታችን ግልጥልጥ አድርገን እንወያይን ጥሪያቸው’ያንብቡ ።

ገጽ አራት አንቀጽ 1 አቶ አቻምየለህ ታምሩ ‘ኢ ሕ አ ፓ’ የኤርትራን ነጻ መውጣትን፣የአፋር፣ የኦሮምወዘተ..ብሄሮችን መገጠልና የሱማሊ ወረራን ደግፏል፣አማራ ትምክኅተኛ ነው በማለት ሌሎች ብሄር/ብሄረሰቦች በአማራ ላይ እንዲዘምት ቀስቅሷል ፣በቀይ ሽብርና በነጭ ሽብር ከደርግ እኩል ተጠያቂ ነው ብሎዋል ፤ነገር ግን አንድም የኢሕአፓ አባል መልስ አልሰጠበትም ።

መልስ፦ የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ ካልሆነ በስተቀር ፤በእነዚህ ነጥቦች ላይ በተለያዩ ግዜያትና በተለያዩ ኢትዮዲያስፖራ የሚዲያ አውታሮች ተነስተው ኢህአፓዎች መልስ ሰጥተውባቸዋል የኤርትራን ነጻ መውጣት መደገፍን በተመለከት ያ ከሆነ ለምን ነበር በ 1967 .ም ሻቢያ የኢሃፓ አስኳል የደፈጣ ተዋጊዮችን ለአንድ ዓመት አሥሮ በበረሃ ያስቀመጣቸው? ለምንድነው ሻቢያ ወያኔዎችን አስልጥኖ፣ አስታጥቆና ስንቅ ስጥቶ ኢ ህ አ ፓን ከትግራይ ምድር እንዲወጥ ያገዛቸው? ለምንድነው ኢስያስ ኢህአፓዎችን የሚጣላው 1969 .ም ሶማሌ ኢትዮጵያን መውረርን ኢአፓ መደገፏን አስመልክቶ ደርግ የኢትዮጵያ ሕዝብ አሳምኖ የኢ ህ አፓ አባላትን ለመጨፍጨፍ የተጠቀመበት ፕሮፓጋንዳ ነው። ያ ከሆን ዚያድ ባሬ ለምን ተሰደው ወደ ሶማሊያ የገቡትን የኢ ህ አ ፓ አባላት አስረ፣ ገረፍ፣ አስቃየ ፣ ክአገሩ እንዲወጡለት አዘዘ ? ለዋቢነት አቶ መርሻና በካናዳ የሚንኖረው ገጣሚና አክቲቪስት አቶ አሊ ሁሴን ይጠይቁ ። ነገር ግን ዚያድ ባሬ ለወያኔዎች ትጥቅ፣ ስንቅ፣ ፓስፖርት ወዘተ..እየሰጠ ያስተናግዳቸው ነበር ። ከመለስ ዜናዊ ድርብርብ ፓስፖርቶች አንዱ የሱማሌ ፓስፖርት ነበር።

አማራ ትምክኅተኛ ነው በማለት ሌሎች ብሄር/ብሄርስቦች በአማራ ላይ እንዲዘምቱ ቀሰቀስ በተመለከተ በኢህአፓ ውስጥጎጃሜዎች ፣ጎንድሬዎች፣ መንዜዎች፣ ፣ቡልጋዎች፣ምንጃሬዎች፣ መርሃቤቴዎች ፣ወለዬዎች ወዘተ..አልነበሩምን ? የሉምን? ለምንድነው ወያኔዎች ኢህአ ፓ ማለት አማራ ማለት ነው ፤ ስለሆነም እናንተ አባአማሮች ከትግራይ ውጡልን ብለው ያስወጥዋቸው ?

አፋር፣የኦሮሞና ሌሎች ብሄር/ብሄረስቦች በተመለከተ ኢሕአፓ አንድም የብሄር/ብሄረሰብ አባል ሳያገል ለ 42 ዓመታት የታገለው ለምን ነበር? ይህ መገነጣጠል የሚሉት በሽታ ለማስቀረት አይደለምን? አንተም ፣አንቺም፣ እሱም፣ እሷም ፣ እናንተም ፣ሁላችንም የአንድ ኢትዮጵያ ልጆች ነን ፣የሚያጣሉንና የሚከፋፍሉን ገዢዮቻችንና የአገዛዝ ሥርዓቶቻቸው ናቸው ፣ ብኅብረት፣ ታግለን ዲምክራሲያዊ ሥርዓት መሥርተን ፣ኢትዮጵያችን አስከብረን በእኩልነት እንኑር ነው ኢህአፓ ያለው የሚለውም ፤ ኢሕአፓ በመገነጣጠል ቢያምን ኖሮ ሁሉም ኢትዮጵያን የሚጠሉ ባዕዳን መንግሥታትም ሆኑ የአገር ውስጥ እንገንጠል ባዮች ምንያህል በወደዱትና በተንከባከቡት ነበር ፤ወያኔዎችን ይመልከቱ ፤ለምንድነ የምዕራባውያንና የአረብ አገሮች እጅግ በጣም ተወዳጅ አጋር የሆኑት??

አቻምየለህ ታምሩ ወያኔዎች የእኛ ናቸው የሚሏቸውን ሃይሎች በሚያስተምሩበት መቀሌ ዩኒቨርስቲ አስተምረውት ፣ እዛው እንዲያስተምር አድርገውት ፣በጣም ታማኞቻቸው የሆኑትን አድርባዮች ከሚልኩባቸው አገሮች አንዱ ወድ ሆነው ኖርዊ ልከው ካስተማሩት በኋላ ፤ለስለላና ተቋሚዮችን ለመበተን ወደ አሜሪካ ከተላኩ የወያኔ ካድሬዎች አንዱ ነው። ስለሆነም ሃቀኛ ጸረወያኔ ታጋዮችን በመበተን የወያኔ ዕድሜ ለማራዘም በርትቶ የሚሰራ ሰው ነው ፤በመሆኑም ብዙ ነገር ሊቀባጠር ይችላል። የ 16 ኛው መ/ክ ዘመን ጭብጣዊው ጣላሊያናዊ ፖልቲከኛ (pragmatist politician)በመባል የሚታወቀው፤ በአሁኑ እውነታ የፖለቲካ ሳይንቲስት (political scientist) ማኪያቫሊ (Machiavelli) “በማኅብራዊ ንቃተኅሊናና በአስተሳሰብ ከማይመጣጠናችሁን ሁሉ መልስ የምትሰጣጡ ከሆነ ፤ወደ እነሱ ዝቅ ማለት ነው “ይላል። ለአቻምየለህን ቅብጥርሶ መልስ ያልተስጠበት ምክንያት ከዚያ አኳያ ነው።

 ገጽ አራት አንቀጽ 1 ”…እስኪ ያ ትወልድ የያዛቸው አቋሞች ስህተት ነበሩ ብላችሁ መርሻዎች በአደባባይ አውጁ ። የኢትዮጵያን ሕዝብም ይቅርታ ይጠይቁ።”

 መልስ ፦ ምኖ ይህንን ጥያቄ ደጋግመውታል ፤ ያ ትውልድ ሲባል በሁለት ከፍለን ማየት እንዳለብን ከላይ አስቀምጬዋለሁ ። እርሶ ያ ትውልድ ሲሉ የትኛውን ነው የሚከሉት ? መርሻም ሆኑ ኢህ አፓ የያ ትወልድ ሁሉ ሃላፊ አይደሉም ወይም ያ ትውልድ ሁሉ አይወክሉም ። ኢአፓ ሁኔታዎችን አስገድደውት ስለፈጸማቸው ስተቶች ከአንዴም ሁለቴ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይቅርታ ጠይቋል። እነዚያ እውነተኛ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ልጆች ራዕያቸው ምን እንደነበረ፣ ለምን እንደተሰው ፣ ለመረዳት፤ የመርሻን ጽሁፍ ገጽ 13 አንቀጽ 3 እና ገጽ 14 አንቀጽ 2 ያንብቡ።

 ገጽ 4 አንቀጽ 2፦ “….እርስዎ እንዳሉት በ 1997 .ም ፌደራላዊ ምርጫ ህወሃት/ኢ ህአድግ በቅንጅት መሸነፉን አልቀበልም እንዳለ ጠቅሰዋል። .. ግን ከመጀመርያው ቅንጅት እንዳያሸንፍ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ቅስቀሳና ተቃውሞ ያደረገ እርስዎና ድርጅትዎ አልነበረምን ። ከብርሃኑ ነጋ ጋር በነበራችሁ ታሪካዊ አምባጓሮ ምክንያት በጅምላ አልተቃወማችሁትም።”

መልስ ፦ ) አቶ መርሻ የዚያ ምርጫ አሸናፊ ቅንጅት መሆኑና ህወሃት/ኢሕአድ በጉልበት ድምጽ የቀማ መሆኑን አምኖ መናገራቸውን እየነገሩን መርሻና ድርጅታቸው በቅንጅት ላይ አሻጥር ሠርተው ወያኔ እንዲያሸንፍ እገዛ አድርገዋል ሲሉ ፤ አሳቦዎን እርስበርሱን አይላተምምን? እንዴትና በምን አሰላለፍ ነው መርሻና ድርጅታቸው ከወያኔ ጋር የወገኑት?

 ) የቅንጅት አሸናፊነት እውቅና መሰጠት ማለት ወያኔን መደገፍ ማለት ነውን

 ) ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የኢሕአፓ ታጋይ ነበሩ ማለት የመርሻና የኢሕአፓ ታሪካዊ አምባጓሮ/ጠላት ነበሩ ማለት ነውን

 ) ነገሩ በአባዬን ጥፋት እማዬን መወንጀል አይሆንምን?

97 አገራዊ ምርጫ ወያኔ ከሙት አልጋ ያነሳው ቅንጅት መሆኑን ይክዳሉን? በወቅቱ ወያኔ/ኢህአድግ በአስተማማኝ ለማሸነፍ ከወጡ ሰፊ ታክቲኮዎች ፣እስትራተጂዎች እና መስፈርቶች ጥቂቶቹን ልጥቀስልዎት ፦ 

የተቋዋሚ ድርጅቶች እንደ አንድ ሃይል ተሰልፈው ምርጫውን እንዲወዳደሩ 

) ገለልተኛ የምርጫ ኮሚሽን ቦርድ (neutral electoral commission board) ካልተቋቋመ የተቃዋሚ ድርጅቶችም ሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ

በምርጫው ላለመሳተፍ የተሰኙ ውሳኔዎችና ስምነቶች በመጣስ ፤ 

1) የቅንጅት ሃይሎች ስልጣን በመኖፖል ለመያዝ እጅግ በጣም ቋምጠው ስለነበረ ፣ ከአገር ውጭ ከተደራጁት እንደ የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ኅብረት(ኢዲሃ) ዓይነት ተቃዋሚ ድርጅቶችን ሥልጣን ላለማጋራት የምርጫ ቦርድን ከወያኔ እጅ ሳይወጣ ምርጫ እንዲደረግ ከወያኔ መሪዮች ጋር ከመጋረጃ በስተጀርባ በመፈራረሙ ።

2)የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን አንቅሮ የተፋበትን ምርጫ ውጤት ወያኔዎች በጉልበት ሲቀሙት ያንን በመቃወም የዩኒቨርሲቲ ተማርዮችና የአዲስ አበባን ወጣቶች ሆይ ብሎ አደባባይ ሲወጡና ሲያምጹ የያኔ ዶክተር ያሁኑ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤እኛ ወጡ ፣ አምጹ አላልንም ፣ውስጥ ውስጡን የሚቀሰቅሱት ኢሕአፓዎች ናቸው በማለት በዜና አውታሮች በይፋ ኢህአፓን ወንጅለዋል ። ታዲያ በምን ዘዴ ነው ለቅንጅት ውድቀት መርሻና ኢህ አፓ የሚሆኑት

ገጽ 4 አንቀ 3፦ “………..ከብርሃኑና ከግንቦት ሰባት ጋር አንድነት ከመፍጠር ከህወሃት ጋር መስራትን እንመርጣለን አላላችሁም ። ..በርሃኑ እና አንዳርካቸው አዲስ አበባ ገብተው ከወያኔ ጋር ስለሰሩ በየአደባባዩ ስታወግዙ፣ ስታሳጧቸው … አልነበረም።” 

  1. መልስ ፦ እጅግ በጣም ተሳስቷል ፤ እስቲ እነዚህን ክስዎ የሚያጠናክር አንድ ማስረጃ ይጥቀሱልኝ ! መርሻና ድርጅታቸው ላለፉት 26 ዓመታት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስቀደሙ ፣ድርጅቶች ኅብረትና አንድ የትግል ማአከል ይኑረን እያሉ ሲማጸኑና ጥሪ ሲያደርጉ ኖሯል፡፡ ይህንን አስመልክቶ እውነትም እነመርሻ ካሉበት የኅብረት ድርጅት (ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ብሄራዊ ሸንጎ) ጥሪ ተደርጎልን ነበርን ብሎ ድርጅቶን ይጠይቁ ። አሁን የድርጅትዎ አቋም ተቀይሮ እንደሆን እንጂ ፣ግንቦት 7 ከተመሰረተበት ማግሥት አንሥቶ አንድ ኢትዮጵያ ፣አንድ ሕዝብ የሚል የትግል መተክል ይዘው ከሚታገሉትን ከእውነተኛ ኢትዮጵያዊ የፖልቲካ ድርጅቶችና መሪዮችሲሸሽ/ሲርቅ እንጂ ሲቀርብ አይታም ። ከዚያ ይልቅ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመሸንሸን የሚሯሯጡትን ብሄርተኛ ድርጅቶችን ሲኮተኩትና ሲያሽሞነሙን ነው የሚታየው ። ምናልባትም የእነዚህን ጥቅም/ኢንትረስት ካስጠበቅኩ የድኽረ ወያኔ ኢትዮጵያ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ሥልጣን ለመጨበጥ ያበቁኛል ብሎ ከማሰብ ሊሆን ይችላል። ስለሆነም ችግር ያለው ከእርሶን ጓዳ ስለሆነ ፤ግንቦት 7 አቋሙን እንዲያስተካክል ይማጸኑ።

    ገጽ 4 አንቀጽ 2፦ “……..ዛሬ በህወሃት በኩል ምን ተቀረና ነው አሁን አገር ገብታችሁ ከመንግሥት ጋር መሥራት የፈለጋችሁት።የተለወጠ ነገር ኖሮ ሳይሆን ብርሃኑን ለመቃወም ሲባል ብቻ የተደረገው የእርሶ እስትራተጂካዊ ለውጥ ነው። ሐቁ ይሄን ብቻ ነው ሌላው ይተውት።”

    መልስ፦ ) በህወሃት በኩል ምንም የተቀየረ ነገር እንደሌለ ካወቁ በርሃኑስ ለምን አገር ቤት ይገባሉ?
    )ከወያኔዎች ጋር ለፖልቲካ ሥልጣን መደራደር ያለባቸው ፕ/በርሃኑ ነጋ ብቻ ስለሆኑ ሌሎች ተቃዋሚዮች አርፋችሁ ተቀመጡ ማለትዎን ነውን? ) አቶ መርሻ አገር ቤት ለመግባት የተዘጋጁ ወይም የገቡ ለመሆኑ ምን ማስረጃ አልዎት? )የአቶ መርሻን ጽሁፍ ገጽ 15 እና 16 ያንብቡ እንዴት አሁን አገር ቤት ያለ ወይም አሁን ከወያኔዎች ጋር ለመደራደር ወደ አገር ቤት ለመሄድ ያሰበ/የተዘጋጀ ፖልቲከኛ የዚህ ዓይነት የከረረ ጽሁፍ ይጽፍባቸዋል? እርሶ በእውነትም በፖለቲካ ዓለም ያሉ ሰው ኖትን?

    ገጽ 4 አንቀጽ 3፦ “ለአቶ መርሻ ቡድናቸው የምንሰጠው አንድ ተመክሮ ወያኔ ከርሰዎ እና ከቡድኖ ጋር ከሚሰራ ከብርሃኑና አንዳርጋቸው ጋር እርቀሰላም ፈጥሮ አብሮ መሥራትን እንደሚምርጥ ነው። ለምን ቢባል እናንተ ‘ለሥልጣን የምትቋምጡ አደገኞች’፤አንዳርጋቸዎች ደግሞ ለሃገር እድገት እና ለስላም የሚሠሩ መሆኑን ጠንቅቀው ያውቃሉና።” 

    መልስ፦ )ወያኔዎች ለሃገር እድገትና ለስላም የሚሠራ/ሩ ተቋሚዎችን ይወዳሉ ማለትዎን ነውን? )ታዲያ ግንቦት 7 ለምን ወያኔ የሚገባው ቋንቋ ጠመንጃ ብቻ ነው ይላል?

    ) ለምንስ ነው ኤርትራ ውስጥ ወያኔን በትጥቅ የሚፋለም ሠራዊት እያሰለጠን ነው እያላችሁ ከኢትዮጵያውያን ገንዘብ የምትሰበስቡት?

    )አቶ አንዳርቸው ከእነሱ የሚስማማ ስው መሆኑን ካመኑ ለምን በአሸባሪነት አሰርዋቸው? ወይስ አቶ አንዳርቸውና ፕ/ብርሃኑ ድሮ ወዳጆቻቸው ስለነበሩ አሁንም ከሌሎች ተቃዋሚዮችን ከሚደራደሩ ከእነሱ ጋር መደራድርን የመረጡ መሆኑን የሚያውቁት ነገር አለን? ወይስ የሻቢያው መሪ ኢሳያስ ሊያደራድራቸው እንደታሰበ የሚያውቁት ነገር አለን

    ለስልጣን የምትቋምጡ አደገኞች’ ፦ “ገበያ በውጣሽ ይሉሽን በልሰማሽ” ። ሳትገድሉ ገደልን፣ ሳትማርኩ ማረክን፣ ባልዋላችሁበት ዋልን፣ በሬ ወለድ ፣በስድስት ወር ወይም በዓመት ውስጥ ወያኔን ጥለን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲ እናነክሳለን ወዘተ እያላችሁ እንታገልለታለን የምትሉትን ሕዝብ የምታታልሉ ፣የምትዋሹ ፣የምታዘናጉ ወዘተ እናንተ ግንቦት 7 ዎች አይደላችሁምን? ምክንያቱም በውሸት የሕዝብ ድጋፍ አግኝታችሁ ባጭር አቋራጭ ሥልጣን ለመጨበ ። በ 97ው አገራዊ ምርጫ በቅንጅት የሥልጣን ቆማጭነት ምክንያት ወያኔ ከሞት እንድተነሳ ሁሉ ግንቦት 7 –ኅልው ከሆነበት እ..አ ከ 2008 .ም ጀምሮ በመዋሸትና በዲያስፖራው ዓለም ያሉትን ተቃዋሚ የፖለቲካና የሲቪል ድርጅቶች ኅብረት ፈጥሩው እንዳይታገሉ እንቅፋት በመሆን የኢትዮጵያን የፖለቲካ አቅጣጫ አዛብቷል፤አበላሽቷል፤አተራምሷል ።

     ለአገርና ለሕዝብ የቆሙ ሃቀኛ ታጋዮች ሕዝብን ዋሸተው አታልው ሥልጣን ላይ መውጣት በሕዝብ ላይ ለመቆም እንጂ ለሕዝብ ለመቆም እንዳልሆነ ያምናሉ። አለኝታቸውና ሃይላቸው የሚታገሉለት ሕዝብ መሆኑን ያምናሉ።

     ሕዝባዊ አመኔታ የሚገኘው ከተግባር መሆኑን ያምናሉ ። ሕብን ማታለልና መቅጠፍ ፀረሕዝብነት ነው ይላሉ። ‘እውነተን ተናግሮ በመሸበት ማደር’ን ይመርጣሉ። መርሻና ድርጅታቸው ይህንን መተክል (principle) ስለሚከተሉ ነው ከአርባ ዓመታት በላይ ትግል ላይ የቆዩት። ለምዕራብውያን መንግሥታት እና ለአረብ አገሮች መንግሥታት ቅጥረኛ ቢሆኑ ኖሮ ከሃያና ከሰላሳ ዓመታት በፊት የኢትዮጵያ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሥልጣን ይጨብጡ ነበር ። ምንግዜም ፣በየትኛውም ማኅበርሰብ ታሪክ ለሃቅ መጋፈጥ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ የኖረ፣ያለ እና የሚኖር ነው ። 

    ኢሕአፓዎች ለሃቅ ስለሚጋፈጡ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድም ቀን በመጥፎ ፣በቅጥፈት፣በውሸት ወዘተ..
    ሲከሳቸው አልተደመጠም ። በርግጥ ኢህአፓ በፀረ ሕዝቦች፣ ፀረኢትዮጵያ አቋም ባላቸው በሄርተኞች ፣ፀረ– ኢትዮጵያ አቋም ባላቸው የባዕዳን መንግሥታት እና በተፎካክሪዮቹ የፖለቲካ ድርጅቶች ክፉኛ ይጠላል ።

     ገጽ 5 አንቀጽ 1፦ ያ ትውልድ አነሳሱ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ብዙ አልሞና ሰንቆ የተነሳ ነበር ። የምሁሩን፣ የወታደሩን፣ የወጣቱን፣ የአርሶ አደሩን ቀልብ ሰቦ የነበረ ድርጅት ነው ። ወጣቶች የማርክሲዝም ፍልስፍና የሚከተለውን ኢአፓ በጠባብ ህወሃቶችና ሻቢያዎች የሚሽከረከር መሆኑን ሳያውቁ ሕይወታቸውን ገበሩ። እዚህ ጋ ፍሬ ሃሳቡን ቀንጭቤ ስለውስድኩ ትምህርተ ጥቅስ አላስፈለገኝም 

    አጭር መልስ ፦ኢህአፓ የወያኔና የሻቢያ አጃቢ/ታዛዥ ከነበረና ከሆነ ለምን ቀንደኛ ጣላታቸው አድርገው ሊያጠፉት ሞከሩ? ለምንስ ነው ሁለትም ተጋግዘው ከትግራይ ከፍለ ሃገር ያስወጡት? ለምንስ ነው እንድ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣የደቡብ ሕዝብ ድርጅቶች ሥልጣን ያላካፈሉት? ምንም አመክኖት (logic) የለዎትምን?

ገጽ 5 አንቀጽ 2፦ አቶ መርሻ ድርጅታቸው ኢአፓ የወያኔና የሻቢያ መጠቀሚያ መሳሪያ ነበር ብለው እስካልተቀበሉ ፤ በድፍኑ ለ 21 ኛው ክ/ዘመን ወጣት ኢትዮጵያ ውያን ከእኛ ስህተት ተማሩ ብሎ ማለፍ በቂ አይደልም። 

ፈሬ ሃሳቡ የተቀነጨበ መልስ ፦ ምን ዓይነት መልስ እንደሚፈልጉ አልገባኝም። ጭብጥ ሃቁን ከላይ ደጋግሜ መልስ ሰጥቼበታለሁ ። አቶ መርሻ የዚያ ሃቀኛ ትውልድ ስህተቶች ምን ምን እንደሆኑም በጽሁፋቸው የጦቆሙበትን ገጽና አንቀጽ እንዲያነቡ አመላክቼሎታለሁ ፤ እርሶ የሚሉት አቶ መርሻ አዎን ኢሕአፓ የወያኔም የሻቢያም መጠቀሜያ መሳሬያ ነበር እስካላሉ የሰጡት ምክር ቢቂ አይደለም ነው ። ኢህ አፓም ሆነ አቶ መርሻ እንደ ግንቦት 7 የውሸት ተረተረት አያወሩም፤ላሞች ባልዋሉበት ኩበት ለቀምን አይሉይም፤ ሌባ የሚያምኖ ሌቦችን እንጂ እውነተኞችን አይደለም፡፡

ገጽ 5 አንቀጽ 5 ፦ “ከኑዛዜ በፊት ኢትዮጵያ፣ዕውነት…ቢቀድም ፀሐፊውን ይበልጥ ባስከራኳቸው ነበር። 

.ለማንኛውም ሕይወት የማያቋርጥ ትምህርት ቤት ናትና አሁንም አልመሸም ። ………………..ለወደፊቱም እውነቱን ለመናገር እንዲችሉ እግዛብሄር ድፍረቱን እና ተመክሮ ይስጥዎት።” 

መልስ ፦ ከኑዛዜ በፊት፣አሁንም አልመሸም፣ ለወደፊቱም እውነቱን ለመናገር…ድፍረቱን…ይስጥዎት’ አይቃረኑምን??

ኑዛዜ በእኛ በኢትዮጵያውያን ባህል ለሞት አፋፍ ላይ ሲደረስ ለቤተሰብ የሚነገር ቃል/መልዕክት ይመስለኛል ። እንዳልመሸባቸውና ዛሬ ያላጋሩኑን/ያልነገሩንን ተመክሯቸውን ወደፊት ሊነግሩን እንድሚችሉ ካመኑ ይህንን ጽሁፋቸውለምን የኑዛዜያቸው ጽሁፍ ሊሆን ይችላል

አንቺው አምጪው አንቺው መልሺው አይሆንምን