August 8, 2017

ነሐሴ 07, 2017

(ጽዮን ግርማ)

የሕፃናቱን ወላጆች አነጋግረናል ቤተሰቦቹ እንደሚሉት የመደፈር አደጋው የደረሰባቸው የአንድ መንደር ወንድ ሕፃናቱ ሰባት እንደነበሩና ፖሊስ ወደ ፍርድ ቤት ጉዳያቸውን የወሰደው ሕፃናት ቁጥር አምስት መሆኑን ነው።

ዋሽንግተን ዲሲ — በአዲስ አበባ ከተማ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አባዲና እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በአንድ መንደር ውስጥ የሚኖሩ ከሰባት በላይ የአዳጊ ወንድ ልጆች ወላጆች “የመደፈር አደጋ ለደረሰባቸው ልጆቻችን የሕክምናና የሥነ ልቦና አገልግሎት የሚሰጠን አጣን ልጆቻችንንም የምናደርስበት ግራ ገባን” ሲሉ ተናገሩ። በልብስ አጠባና በጽዳት ሥራ የተሰማሩና እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ መሆኑን የተናገሩት እናቶች “በዚህ ኑሮ ላይ ይህ ሁኔታ እንዴት እንደምንቋቋም ግራ ተጋብተናል” ብለዋል። ሕፃንቱን በመድፈር የተጠረጠረው ወጣት በእስር ላይ እንደሚገኝና መዝገቡ ውሳኔ ሳያገኝ አንድ ዓመት መቆጠሩን ገልፀዋል። በወረዳው በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚሰሩ ወጣቶች ሕፃናቱ በደረሰባቸው አደጋ መጎዳታቸውን ማየታቸውን ገልፀው አምስት ሕፃናት መደፈራቸውን የሚያረጋግጥ የሕክምና ማስረጃ አይተናል እሱም ለፍርድ ቤት ተያይዟል ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ቤተሰብ፣ የሕፃናትና ወጣቶች ባለሞያ፣ ፖሊስ፣ የሕክምናና የሥነ ልቦና ባለሞያ አነገጋግረናል።

ሁኔታውን በስፋት የሚዳስሰውን ዘገባ ያዳምጡ።⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/08/4cf78698-e7bb-4901-b66e-114d9f66816d_48k.mp3