AUGUST 9, 2017

MANTEGAFTOT SILESHI BORN IN ADDIS ABEBA, SILESHI COMPLETED A MASTER’S DEGREE IN INTERNATIONAL MEDIA STUDIES (2009-2011) AT THE UNIVERSITY OF BONN, UNIVERSITY OF APLIED SCIENCE BONN-RHEIN-SIEG & DW-AKADEMY.

EMF – በማንተጋፍቶት ስለሺ ተሰርቶ ለእይታ የበቃው GERRETA ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ። ይህ ፊልም ሽልማቱን ያገኘው ጣልያን ላይ ተካሄዶ በነበረው THE 9 RIVER FILM FESTIVAL, PADOVA ሲሆን ፣ በያዝነው ወር አጋማሽ (17-26 AUGUST 2017) በአምስተርዳም የሚካሄደው የዓለምአቀፍ ሲኒማ ፌስቲቫል ላይም ይቀርባል።

ግርታ አጭር ፊልም በ2017 በዚፍ ZIFF (2017) የፊልም ፌስቲቫል ፣ በቡርኪና ፋሶ FESPACO (OUAGADOUGOU, BURKINA FASO 2017) እንዲሁም በርሊን ላይ ተደርጎ በነበረው 31ኛው አለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫሎች ላይ ተወዳድሮ የአሸናፊነት መታጨቱን የአለም ሲኒማ ድረገጽ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ፊልሙን የሰራው ማንተጋፍቶት ስለሺ በአሁን ሰዓት በጀርመን ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው አገልሎት ፕሮዲዩሰር ሲሆን ፣ በመጭው ሳምንት በአምስተርዳም ላይ በሚደረገው ዓለምአቀፍ ሲኒማ ቀን በመገኘት ለተመልካቾች ስለ ፊልሙ ይዘት ማብራርያ ይሰጣል።

ፊልሙ በአንድ በድህነት የተበሳጨ አባት ታሪክ ዙርያ ያጠነጥናል። ይህ አባት ለልጆቹ የሚበላ ፍለጋ ከቤቱ ይወጣል። እመንገዱ ላይ አንድ ሃብታም ቤተሰብ ያገጥመውና የሸክም አገልግሎት በትንሽ ክፍያ ይሰጣቸው ዘንድ ቢጠይቅ እምቢኝ ብለው ያመናጭቁታል። ግርግር ወደበዛበት ስፍራ የተጓዘው ይህ አባት፣ በማያውቀው የዳቦ ቤት ሌብነት ወንጀል እሱ ጦስ በመሆን “ሌባ” እየተባለ የአባሮሽ ሰለባ ሲሆን ያሳያል። በፊልሙ 35 ያህል ካራክተሮች የተካተቱ ሲሆን ቀረጻው በተለያዩ የአዲስ አባባ ክፍሎች መከናወኑን የፊልሙ ዲያሬክተር ገልጿል። ፊልሙ የተሰራው በአማርኛ ሲሆን የእንግሊዝኛ ሰብታይትል አለው።

በመጭው ሳምንት ፊልሙን በአምስተዳም ለማየት የሚሹ RIALTO ሲኒማ ብቅ በማለት አልያም በዚህ ሊንክ መጠቀም ይቻላሉ።

https://www.youtube.com/watch?v=vgao55J26oI