ዛሬ ሓሙስ 04/12/09 ዓም የመቐለ ሚኒባስ ታክሲዎች ከ01:00 እስከ 06:30 ኣድማ መተው ውለዋል።

image_pdf

August 10, 2017 – 

ቆንጅት ስጦታው

የመቐለ ታክሲዎች ኣድማ  by Amdom G/S

ዛሬ ሓሙስ 04/12/09 ዓም የመቐለ ሚኒባስ ታክሲዎች ከ01:00 እስከ 06:30 ኣድማ መተው ውለዋል።

የኣድማው ምክንያት በመቐለ ከተማ መስተዳድር “በፌደራል መንገድ ትራንስፖርት በሃገራቀፍ ደረጃ ያወጣው ኣንድ ዓይነት የግዳጅ የግብር ክፍያ ነው” በማለት እስከ 3000 ብር የሚደርስ ብር “በግድ ክፈሉ” የሚል ኣስገዳጅ መመርያ በመውረዱ “ኣንከፍልም” በማለት ተቃውሞኣቸው ኣሰምተዋል።

ባለታክሲዎቹ የተሰጣቸው የግዜ ገደብ በማሳለፋቸው መስተዳድሩ ለማህበራት ማስፈራራት እያቀረበ የቆየ ሲሆን የማህበራቱ ኣመራሮች ባለታክሲዎቹና የመስተዳድሩ ሓላፊዎች ስራ በማቆም ግንባር ለግንባር እንዲነጋገሩ ኣድርገዋል።

ሓላፊዎቹ በግድ ትከፍሉዋታላቹ የሚል ማስፈራርያ ያቀረቡ ሲሆን ባለታክሲዎቹ ደግሞ ከኣቅማችን በላይ ግብር መክፈል ኣንገደድም በማለት ኣቋማቸው በመድረኩ ኣሳውቀዋል።

ሓላፊዎቹ በድንጋጤ የመለሱት መልስ

* ትርፍ ትጭናላቹ

እስከ 06:00 ሰዓት እያገላገላቹ ኣይደለም

በተፈቀደላቹ ስምሪት እየሰራቹ ኣይደለም

ኣደጋ እያደረሳቹ ናቹ ወዘተ ” የሚሉ የጎንዮሽ ማስፈራርያ በማቅረብ ጭቅጭቁ ተጨርሰዋል።

የመቐለ ባለታክሲዎች “ከኣቅማችን በላይ ግብር ኣንከፍልም” በሚል ኣቋሙ ፀንቶ ስብሰባ ተበትነዋል።

ከኣቅማችን በላይ ግብር እንድንከፍል እያስገደደን ነው የሚል ተቃውሞ ነው።

ካድሬዎቹ የመቐለ ህዝብ ያየው ሃቅ ለመካድ እየመኮሩ ነው።

No widget added yet.

← የኦፌኮ ከፍተኛ አመራር የሆኑት መምህር በቀለ ገርባ የዋስትና መብታቸውን ተከለከሉ ! ግርታ የተሰኘው ኢትዬጵያዊ አጭር ፊልም በአለም አቀፍ ደርጃ ሽልማትን አገኘ →

Leave A Reply

Comments are closed

Visit Us On TwitterVisit Us On FacebookVisit Us On YoutubeVisit Us On Linkedin