ባህር ዳር ውጥረቱ ተባብሷል

image_pdf

August 11, 2017

 

 

ወደ ባህር ዳር የሚገባሆም ሆነ የሚወጣ ይፈተሻል።

ኢትዮጵያ ነገ አማርኛ ዜና፦ ባህርዳር ከተማ ውጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል። ወደ ከተማዋ የሚገባን ሆነ የሚወጣ ይፈተሻል። ነጋዴዎችንና የከተመዋን ወጥቶች በገፍ ማሰሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ሱቆችም እየታሸጉ ነው። ከተመዋ በመንግስት ደህንነትና በልዩ ሀይል ፖሊስ ተጨናንቃለች።

ገበያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን ለመክፈት ቡሞክሩም ሰሞኑን “ለአድማ” ስለዘጋችሁ ዛሬም አትከፍቱም ተብለው በፖሊስ ተባረዋል።ትናንት ቀበሌ 6 (መናኸሪያ አካባቢ) ያሉ ሱቆች በሙሉ ታሽገዋል። መንገድ ላይ አሮጌ ልብስ የሚሰፉ፤በኮንቲነር ትናንሽ የሸቀጥ እቃ የሚሸጡ ሳይቀር እስከ 30000 የስራ ግብር ተጥሎባቸዋል።የከተማው ግብር ሰብሳቢ ቡድን “የግብሩን መጠን” ለሁሉም ነጋዴዎች አላሳወቀም።”ይህም ነጋዴው አንድ ላይ ሆኖ መብቱን እንዳይጠይቅ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው።ይሁን እንጂ ህዝቡን የሚለያይ አጀንዳ ከእንግዲህ አይኖርም።” በማለት መረጃውን ከባህር ዳር ያደረሰን ምንጫችን ገልፆልናል።

ባህር ዳር እና ደብረታቦር በአጋዚ ወታደሮች ቁጥጥር ስር ወድቀዋል፣ ወጣቶችም እየታፈሱ ነው፣ የንግድ ተቋማትም እየታሸጉ ነው። በጎንደር፣ በወልደያ፣ በምስራቅ ጎጃም ደምበጫ እና አማኑኢል የሥራ ማቆም አድማ እየተደረገ ነው።

http://ethioforum.org

No widget added yet.

← “አዲስ አበባ የኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ናት፤ አራት ነጥብ።” – ዶ/ር አብርሃም ዓለሙ – ውውይት High Profile Corruption Case Boils Down on Properties of 210 People →

Leave A Reply

Comments are closed

Visit Us On TwitterVisit Us On FacebookVisit Us On YoutubeVisit Us On Linkedin