የኬንያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ሮቤሊን አኪም

August 16, 2017 05:47

የኬንያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽነር ሮቤሊን አኪም ወደ አሜሪካ ለመጉዋዝ የሚያስፈልገውን ቅድመ ሁኔታ አሟልተው የበረራ ሰዓት በሚጠባበቁበት ወቅት በመንግስት ባለስልጣናት መጉዋዝ እንደማይችሉ ተነግሮዋቸው ከአውሮፕላን እንዲወርዱ እና በረራቸው እንዲሰረዝ መደረጉን ቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ዘግቧል፡፡እንደ ቢዝነስ ዴይሊ አፍሪካ ዘገባ የኬንያ ምርጫ ቦርድ ስለኮሚሽነርዋ ጉዞ እገዳ በሰጠው ማስተባበያ በድርጊቱ የተሳተፉ የመንግስት ባለስልጣናት ይቅርታ ጠይቋል ብለዋል፡፡ኬንያ ባለፈው ማክሰኞ ኦገስት 8 ሀገራዊ ምርጫን ብታደርግም የዋናው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነው ናሳ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለውና ምርጫ ቦርድ ለመንግስት ያደላ ነው ማለቱ አይዘነጋም፡፡

By ሳተናው