September 7, 2017
EMF

በሙስና ወንጀል ውስጥ እጃቸው አለበት እየተባለ የሚነገረው አቶ አባይ ጸሃዬ ልጆቻቸውን በሙሉ ወደ ውጭ እንዲሸሹ ማድረጋቸውን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።

የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት የአባይ ልጆች በአሁን ሰዓት በአሜሪካን ሃገር ውስጥ እንደሚገኙ የተጠቆመ ሲሆን ከሚኖሩበት ስፍራ ሰው በቀላሉ እንዳያጘኛቸው ማህበራዊ ገጾቻቸውን እና ስልኮቻቸውን አጥፍተዋል።

የአስራ ሁለት ልጆች አባት የሆኑት አቶ አባይ ጸሃዬ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 77  ቢሊየን ብር በማባከን የሚጠቀሱ ሙሰኛ ቢሆኑም እስካሁን ተይዘው ሊጠየቁ ግን አልተቻለም።

አቶ አባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በፌደራል ጉዳዮች እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በሃላፊነት ሲሰሩ የዘረፉትን የሀዝብ እና የሃገር ገንዘብ በልጆቻቸው እና በሚስታቸው ስም በህገወጥ ንግድ ላይ ማዋላቸውንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

አቶ አባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በፌደራል ጉዳዮች እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በሃላፊነት ሲሰሩ የዘረፉትን የሀዝብ እና የሃገር ገንዘብ በልጆቻቸው እና በሚስታቸው ስም በህገወጥ ንግድ ላይ ማዋላቸውንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ከአባይ ጸሃዬ ልጆች ውስጥ ትንሽዋ፣ ቤቢ የተባለችው ልጃቸው በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሕንጻዎች  ያላት ሲሆን፤ በዱባይ እና በአሜሪካም ትላልቅ ህንጻዎች እና የንግድ ተቋማት እንዳላት ምንጮቹ ገልጸዋል።  ጤፍ፣ በርበሬ፤ እንጀራ፣ ወዘተ  ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ የሚላኩ የእርሻ እና የባልትና ውጤቶች በሙሉ የተያዙት በአባይ ጸሃይ ልጆች መሆኑንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።

ባለቤታቸው ሳሌም ከበደ ከወር በፊት በሙስና ተጠርጥራ መታሰርዋ  የሚታወስ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ባለሀብቶችም ከአባይ ጸሃዬ ጋር ስላላችሁ የዝርፍያ ግንኙነት ለፖሊስ እና ፍርድ ቤቶች እየተናገሩ ይገኛሉ።

የኦሮሞን ሕዝብ እንደመሥሳአለን እያሉ ሲዝቱ የነበሩት እኚህ ሰው ባለበታቸው በታሰሩ ግዜ የተለያዩ ጀኔራሎች ዘንድ በመደወል “አድኑኝ” እያሉ ሲማጸኑ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት በህወሃት አመራር መካከል በተፈጠረው የከረረ ክፍፍል እና ያለመግባባት ሳብያ ስጋት ውስጥ የገቡት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘረፈውን የሃገርን ሃብት እና ልጆቻቸውን በሙሉ ከሃገር ማሸሹን እንደአማራጭ መውሰዳቸው የሳቸው ቡድን ህልውና አስጊ ሁኔታ ላይ መድረሱን ያሳያል።

ከአቶ አባይ ጸሃዬ ውጪ ጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ አቦይ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል፣ እና ባለ ማእረግ የህወሃት ወታደሮች  በቢሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ እና ዘመድ አዝማዳቸውን በማሸሽ ላይ እንደሚገኙም የተጠቆመ ሲሆን አቶ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ከምኒስትር ድኤታ ወርደው የቻይና አምባሳደር እንዲሆኑ የተደረገው ለባለስልጣናቱ የመጨረሻ የማምለጫ አማራጭ ለማበጀት መሆኑን የፖለቲካ ታዛቢዎች ይናገራሉ።

በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ ያሉት እነዚህ ጥቂት ሰዎች፣ ሃገሪቱን ለማስተዳደር ያልቻሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አለም አቀፍ ሜዲያም እየተናገሩ ይገኛል። የህወሃት ሰዎች በሁለት ጎራ ተከፍለው አሁን የማይወጡበት ችግር ውስጥ ስለገቡ ያላቸው አማራጭ ሃብት እና ዘመዶቻቸውን ማሸሽ በመሆኑ ይህንን ተያይዘውታል። በስሙ ሲነግዱበት የነበረውን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ እንዲጫረስ አድርገው እነሱ እግሬ አውጭኝ ማለታቸውን የትግራይ ሕዝብ ከወዲሁ ሊያወግዘው እንደሚገባ በርካታ ሃገር ወዳዶች ሃሳብ እየሰጡበት ነው።

EMF