አከአለ ያገሬ ሰው፣ ከሰሞኑ አጃኢብያሰኘውን የአዜብ መስፍን ወሬ ሲሰማ። አዜብ ልምድ ያላት ውሸታም እን ጂ ልምድ ያላት ኮሜዲ አትመስልም ነበር። ከሚሚ ስብሃቱ ጋር በያዝነው ሳምንት የተወኑት ድራማ ግን ጦሽ አርጎ ያስ ቃል። መቼም ጥርስ እንጂ ልብ አይስቅ። ፈንድሻምኮ ልቧ እየተቃጠለ ነው ፊትዋ ሚፈካው።

ሴትየዋ አይኗን ሳይሆን ቅንድቧን በጨው አጥባ ምንም የለኝም ግን ይወረስነው የምትለው። መለስ የባንክ ደብተር ይቅርና መንጃ ፈቃድ እንኳ የለውም ስትል የቀለደችበት ወቅት ሩቅ አይደለም። እርግጥ ነው አዜብ በራስዋ ስም እንኳን ሕንጻ፣ ሲም ካርድም ሊኖራት አይችልም። ጥሩ ጋዜጠኛ አልገጠማትም እንጂ፣ ቢገጥማት፣ እመኑኝ ልጃገረድ ነኝ!” ብላ እያለቀሰችም ቢሆን ለማሳመን ትሞክር ነበር። ልጆቼን እየተበደርኩ ነው የማስተምረው ብላ በተናገረች ሰሞን ኤ..ሲ ኢንተርናሽናል የተባለው የማድሪድ ጋዜጣ ወ/ሮ አዜብ መስፍን በአንድ ቀን የግል ግብይት ብቻ 1.5 ሚሊዮን ዶላር እንዳወጣች ዘግቦ ነበር።

የወዲ ስብሃቱ ልጅ አላማ የሙስናዋን ንግስትነጻ ለማውጣት መሞከር ባይሆን ኖሮ ፣ በነካ እጅዋ ሰሞኑን በወደቀ ሂሳብ እየተቸበቸቡ ስላሉ የአዲስ አበባ ሕንጻዎች ጉዳይ ታነሳ ነበር።

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ጠቅልሎ የያዘው ኤፈርት አናት ላይ ቁጭ ብላ ምንም የለኝምየሚል ነጠላ ቀልድ የለቀቀችው አዜብ 30 ሚሊዮን ብር ከኪስዋ መዝዛ ለመቀሌ ስፖርት ክለብ መለገስዋን እንኳ ረስታዋለች። ግብር የማይከፍልና የኦዲት ቁጥጥር የማይነካው ደጀና የተባለው የማፍያ ኩባንያ ከኤፈርት ጋር ተጣምሮ የሃገሪቱን ኢኮኖሚ እኩሌታ ይዟል። ካፒታሉ አፍሪካ አንደኛ የሆነው የዚህ ጥምር CEO ነኝ ብላናለች አዜብ። ሰማይ አይታረስ፣ ንጉስ አይከሰስ፣ ደሞዝ አይነገር.. ደሞዝአይጠየቅ! በዛሚ!

ዛሚ ኤፍ.ኤም ተብሎ በሚጠራው የነሚሚ ስብሀቱ ራዲዮ ጣቢያ ከዚህ ቀደም የሞራል ቀውስ ውስጥ ገብተው የሚዋኙ ትናንሾችን እያቀረበ፣ በደረቀ ፕሮፓጋንዳ ብቻ ብዙ መጓዝ ባለመቻሉ፣ የፕሮግራም ለውጥ ያደረገ ይመስላል። እንደ አዜብ መስፍን አይነቱን ጥያቄና መልስ እያስጠና ተከታታይ ድራማ ማቅረብ ጀምረዋል። የመጀመርያው ሾው በቴዲ አፍሮ ተጀመረ ። ገድለው ሃውልት መስራት ለነሱ አዲስ ነገር አይደለምና ጸሃይ የሞቀውን እርምጃው ፍትሃዊ አይደለምእንቶፈንቶደጋገመችው። የቴዲ አፍሮን የአልበም ምረቃ ያገደውን ስውር እጅ አደባብሳ አለፈችው። ስለማታውቀው ፍትህ እና መብት መለፈፍዋ ግን ብዙዎችን ሳያስደምም አልቀረም።

አዜብ በተከታዩ ክፍል ብቅ ብላ፣ የምተዳደረው በዶሞዝ ነው። መለስም፣ እኔም፣ ልጆቼም ሃፍት የላቸውም።አለችን። ውልና ማስረጃ የሌለው ሃፍት ካላኝ ቦታውን ያሳዩኝ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ልመልሰውየሚለው ሕጻን ልጅን እንኳ የማያሳምን አባባልዋ ትንሽ ያስቃል። ሕዝብ በደቦ ወጥቶ የአዜብና ዘመዶችዋን የልተመዘገበ ንብረት እንዲያፈላልግላት መጠየቅዋ ነስ ወይንስ የእሷም ህንጻዎች እንደ ኮንዶሚኒየሙ ጠፍተዋልብለው ነገሯት? ከሠበታ የወሰደችው 1200 ሄክታር መሬት የቀብርዋ ስፍራ መሆኑ ነው። ይህ ደግሞ በነሱ ቋንቋ ሙስና አይባልም። ሙስናም ቢሆን ለከባባድ

ሚዛን የህወሃትአባላት የአገልግሎት ስጦታ ነው። አቶ አያሌው መንገሻ፣ የቀድሞው የደህነት መ/ቤት ሹም ህብር ሬዲዮራላይ ቀርበው በሰጡት ቃለ ምልልስ በሕወሃት ሙስና ወንጀል አይደለምብለውናል።

ኮሜዲያን ወደ ውጭ ሲሰደዱ፣ ፖለቲከኞቹ ቦታቸውን ይዘዋል ልበል? ከሰሞኑ የህወሃት ካድሬዎች እንደጉድ መቀለድጀምረዋል። አዜብ እና ከሚሚ ተደራጅተው የሰሩት ይህ እየሳቁማንባት ተውኔት ግን ከኮሜዲ መስመር ወጣ ይላል።

ቃለምልልሱ የተጠና ላለማስመሰል እንኳ አለመሞከራቸው፣ ለአድማጭ ያላቸውን ንቀት ያሳያል።መኖርያ ቤት ሰርተሻል?” የሚለው የመጀመርያ ጥያቄ ሲቀርብላት ነበር ፣ አዜብ ከሌላው ጋር አብሬ ልመልሰውስትል ተካታዩን ጥያቄምእንዳምታውቀው ያስፎገረችው። መዋሸት አንድ ነገር ነው። ውሸት ለማስመሰል መቻል ደግሞ ማወቅን ይጠይቃል። ይህንን እንኳን ማድረግ አልቻሉም።

የዛሚዋ ካድሬ ሚሚ ስብሃቱ አዜብን ለማንጻት ብዙ የታከከች ይመስላል ለዛሬ ባይሳካም።አዜብ እውቀት ነጻ ትሁን እንጂ፣ በጣም ደፋር ናት። የእንግሊዝን መንግስትንም ሆነ የአውሮፓ ህብረትን ብትጠይቁ

ምንም የሌለኝ ድሃ መሆኔን ይነግሯችኋል ትለናለች። አዜብ ሃብታም ግን የምትሆነው ህወሃት ወይንም ኤፈርትሲለቅቃት ብቻ ነው። ድርጅቴ ሲለቅቀኝ በግሌ ከጉልት ንግድ በመጀመር ሃብታም ሆናለሁስትል አስቃናለች።

ይህንን ያድርግልሽ ብለናል!

https://www.youtube.com/watch?v=CZgU-08PjWU