ሕወሐት በሰላም ድብቅ አጀንዳዋን በስራ ለማዋል እና የትግራይ/ትግሪኝ የመቶ አመት የቤት ስራ መክሸፍ ላይ ቢሆንም። በጥድፊያ የሚሰሩ ጸረ ኢትዮጵያ ተግባራትን እየከወነች መሆኑን ከሰሞኑ የተሻለ አንድም ሌላ ገላጭ ግዜ አልነበረም። ያኔ ሕወሐትን ለመግታት የያ ትውልድ ሰማእት መሪወች በፍኖተ ዴሞክራሲ ከጀግኖች ምድር ከቋራ ይተላለፍ በነበረው ራዲዮ ያለማቋረጥ ጥሪ አቅርበው ሰሚ ጆሮ ተነፍገው ብዙታጋዮችም ግንባራቸውን ሳያጥፉ ያለማንም ድጋፍ ታሪካዊ ሀላፊነትን በመወጣት መስዋእትነትን በጸጋ ተቀብለው አልፈዋል። ዛሬ በየምእራብ አደባባዩ እና ቤተመንግስት ደጃፋት የምናደርገውን እግዚዮታ ያኔ እሩቡን ለዚያ ታጋይ ትውልድ ቢሰጠው አገራችን እዚህ ላትደርስ እሙን ነበር። ዛሬም ከዚያ አፍዝ አደንግዝ ያልተላቀቀ እና የወገን ስራ እንደቅጥቃጤ አላስተኛ ያለው ብዙ በመሆኑ እየደረሰ ላለው የጥፋት ዘመቻ ተባብሮ እና ተጋግዞ ያቅምን ከማበርከት ይልቅ እርስ በእርስ ዝልፊያ እና ጥላቻ ማካሄዱ አገርን ከጠርዝ ካደረሳት የሕወሐት እና የትሮዩ ፈረሶች ያልተሻለ ሆኖ መገኘቱ ባያስወነጅል በታሪክ ማስጠየቁ አይቀሬ ነው።

የሕወሐት ድብቅ አጀንዳ በአደባባይ በምስራቅ የሀገራችን ክፍል እየተካሄደ ያለው ጸረ ሕዝብ የሕወሐት ዘርን የማጽዳት ዘመቻ ቀጥሏል። ሕወሐት ያው የተለመደ ድብቁን አጀንዳ በጥድፊያ ለመከወን ስትነሳ አይነታ የትግል ስልቷ ትናንት በበደኖ፣ አርባ ጉጉ በሌሎች ስም የተገበረችውን ዛሬ በሶማሌ ኢትዮጵያውያን ስም በኦሮሞ ወገኖቻችን በመካሄድ ላይ ያለውን የፍትህ ንቅናቄ በሁለት መልክ ልትፈታው ተነስታለች። ትቂት ሰወችን ያነሳሳ የሶማሌ ጎሳ ሽፋን በመልበስ በሕዝብ ላይ መዝመት አንዱ ሲሆን ለዚህ አባሪ እና ተባባሪ ደግሞ ያው በኦሮሚያ የጎሳ ሽፋን ያጠለቀው የትሮይ ፈረስ ኦፒዲዮን በማሰለፍ የፕሮፖጋንዳውን ሽፋን ትጋራለሽች።

ይህ በምስራቅ እየተካሄደ ያለ ፋሽስታዊ የሕወሐት ሴራ እና ዘርን የማጥፋት ተግባር ከሃያላኑ የተሰወረ አለመሆኑን ትናንት የተገለጸልን የአሜሪካንን ደህንነት ለቆ በወጣው ስወርድን የተጋለጠው የትብብር የጋራ ስራ መኖሩም ሌላው ግልጽ የሚያደርግ ተግባር እና አገራችን በነበረችበት እንዳትቀጥል፣ ልክ እደ ዮጎዝላቪያ ከምድር ከካርታ እንድትፋቅ እና ከ70 አመታት በፊት በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ እና የኤርትራ የአደራ መንግስት ታስቦ የነበረው በፈራረሰች ኢትዮጵያ አመድ ላይ ሰፊ የባህር በር ያላት የአፍሪካ ቀንድ ሀያል የሆነች የትግራይ ትግሪኝ መንግስት የመመስረት ዝግጅት መሆኑን መገመቱ ተገቢ ነው። ሰፊ ግዜ ተወስዶለት እና ብዙ ባጀት ፈሶለት የተከወነ መሆኑ ሌላው ከባዱ ስራም ይመስለኛል። ማህከላዊ እና ኢትዮጵያዊ መንግስት በሌለበት የተወሰኑ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦችን ፊስካ ነፍቶ እና አሰባስቦ የተሰራው የዘር ሕገመንግስትም ሊያመቻች የሚችለው ይህኑ አገርን ያለምንም ብዙ ችግር የማስረከብ ስውር አላማ አስፈጻሚነትን ነው። ሕወሐት አተኩራ ከታሪካዊ ጠላቶች ባገኘችው ትብብር እና ስነጠበብት ድጋፍ የሰራችው ኢትዮጵያን የጠበቁትን አማራን እና ኦሮሞን እርስ በእርስ ማናከስ ብሎም የመጥፊያ የመጨረሻ ፈጻሜን ማሸራሸት ነበር። ይህ አንድም ቀን ሳይታክቱ የተሰራበት ስራ ዛሬ ነገር መበላሸቱ እና ሕወሐት እንደመንግስት ቀጣይነቷ አስተማማኝ አልመሆኑ እየጎላ በመጣበት ሰአት የተዘየዱ አገር የማጥፋት እቅዶች በሩጫ እየተገበሩ መሆናቸው ሁሉም የሚረዳው ሊሆን የገባል።

ጎንደርን ለማጥፋት ትልቁ ሴራ የክፉ ቀን ከለላው የጎንደር ሕዝብ በሕወሐት አይን የገባው ዛሬ አይደለም። ወልቃይት ጸገዴን፣ ጸለምትን፣ ከኢሕአሠ ማስለቀቅ በዋና ስራ ተይዞ ሕወሐት የሻብያን ትብብር ተችሯት በከባድ ተጋድሎ ከኢሕአፓ ከነጠቀች ግዜ ጀምሮ ጎንደርን የማጥፋቱ እና ትግራይ የማድረጉ እረጅሙ ስራ የተጀመረው 1971 ዓም ነበር። በተመሳሳይ አመት ዛሬ ለሕወሐት የትሮይ ፈረስ ሆኖ የሚያገለግላት ከሀዲ ስብስብ ኢሕአፓ ከዝህች ዘረኛ ቡድን ጋር በጦር ሜዳ በሚፈተንበት ሰአት የከዱ የእንግዴህ ልጆች ግዜውን ተጠቅመው የራሳቸውን ከሀዲ ቡድን መስርተው ኢሕዴን እንዲሉት ተደርጎ ከእናት ድርጅታቸው የተቀላቀሉበትም አመትም ነበር።

ሕወሐት አርባ አመት ያስቆጠረ ጎንደርን የማፍረሱን የመጨረሻ መጀመሪያ ለማድረግ ይህን ሳምንት አሁንም ዳግም በከዱ የሕዝብ ጠላቶች ሕዝበ ውሳኔ ይሰጥ ብላም ተነስታለች። ይህን ሕዝበ ውሳኔ ጠያቂም ደጋፊም የሆነ አማራ እና ንጹህ ቅማንት ላለመኖሩ ደግሞ ግልጽ ነው። ለጥርጥር የሚያስገባንም አይደለም። እነ ጉዱ (ገዱ) አንዳርጋቸው ፈጻሚም አስፈጻሚም ሆነው የተሰየሙበት የጎንደርን ሕዝብ እርስ በእርስ ለማባላት ብሎም የሕወሐት ቋሚ ጠላት የሆነውን የአማራ ሕዝብ ልክ እንደኦቶማን ቱርኮች የኢትዮጵያ ኩርድስታን የማድረግ ተግባር ለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። በእርግጥም ወጣት ኢትዮጵያውያን የአንድነት ኃይሉን በጥያቄ ቢያስቀምጡት ለምን የሚያሰኝ አለማሆኑን አሁን ካንዣበበው አደጋ አንጻር ተመልክቶ አስቸኳይ መፍትሄ የሚሻ ቢሆንም። ሕወሐት እና የትሮይ ፈረሷ በአዴናውያኑ ስራቸውን ከጥይት በቀደመ ፍጥነት ከውነው የጎንደርን የአማራ እና የቅማንት ትርምስ ለማይተ ዝግጁ በሆኑበት ሰአት። ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ እንዲሉ ትግሉ እና ስልቱ የጠፋበቱ የኢትዮጳያ ተቃዋሚ ዛሬ እጅግ ለአገሪቱ ሕልውና ፈታኝ የሆነው እና ለመኖርም ሆነ ላለመኖር ወሳኙ ግዜላይ ቆመን የተቃዋሚ ተብየው ቅዝምዝም ከፍየሏ የሰሜን እና የደቡብ ጫፍን ያክል የተራራቀ ሆኖ መገኘቱ ተጨባጭ ሁኔታን አንቦ ለመፍትሄ ከመሄድ ይልቅ ጠላትን በወረቀት በመስደብ፣ ወይንም ከሩቅ አገራት አለያም ከሌላ safe haven ሆኖ ማስፈራራት የሚሰራ የመሰላቸው እና ድል በድል ብለው የሚቆጥሩልንም ዝናር በቅፌወች አላጣንም።

በግልጽ አማርኛ ስንነጋገር ሕወሐት የተነሳችበትን ዋና አላማ አማራን ከምድር የማጥፋት ስራ ነገ የመጨርሻ ሕዝበ ውሳኔ ብላ በቧለተችው የካድሬ ስራዋ ልታሳይ ተነስታለች። በደቡብ እና ምስራቅ ሀገራችን የታላቁን የኦሮሞ ዜጋችንን ለአያሌ አመታት በአናሳ ብሄረሰብነት እራሱን ፈርጆ እንዲንቀሳቀስ ካደረገች በኋላ፤ የእርሷን ካድሬወች አሰልጥና ከሀጎስ ወደ ደመቅሳነት ቀይራም እስከ ሕዝባዊው አመጽ መነሳሳት ማግስት ሰርታለች። የአሉባልታ እና የጥላቻም ሀውልት እንዲሰራ በሕዝባዊው አመጽ ማግስት ሞክራለች። ሁሉም ሳይሆን ዛሬ የራሷን ጦር አሰልጥና የኦጋዴን ሕዝብ በኦሮሞ ሕዝባችን ዘመተ አለችን። ብዙም ደም ፈሰሰ። ብዙም ቤት ተቃጠለ። በአስር ሽሆች ቀያቸውን ለቀውም መዳረሻ አጥተው በመባዘን ላይ ናቸው። በዚህ መሀል በእርሀብ፣ በበሽታ፣ እና በሌላ አደጋ የሚያልቀው ዜጋ ቁጥር ቀላል አይደለም። ይህ ሲሆን አማራ ጠላቴ ነው (ሕዝብ ጠላቴ ነው) የሚሉት ባለሜንጫወች ክተት ሳይሆን ዝምታን እና የወረቀት ላይ ነብርነትን ከ safe haven ሆነው በመግለጫ ቀጥለዋል። ይህ ሲሆን ከዚህ ዘመን በፊት እንደነበረው እንደነ ሀብተጊወርጊስ ዲነግዴ፣ ባልቻ አባነፍሶ፣ ገረሱ ዱኪ፣ በቀለ ወያ፣ ጃገማ ኬሎ እና እንደነ ቤሻህ አቦየ አንድነት ተነስ አገርህን ከደመኛ ጠላታችን ከወያኔ ነጻ አውጣ፣ ከወንድምህ ፍዳውን እንዳንተው እየተቀበለ እንዳለው ከአማራው ጋር ተሰለፍ ተቆራኝ የሚል አንድም ቃል ያለመተንፈሳቸው በአደባባይ ባይተቃቀፉ እነርሱም የስውር የትሮይ ፈረስነታቸው ግን የአደባባይ ሚስጥር ለመሆኑ ለአፍታ የሚጠራጠር የለም።

ማጠቃለያ

ኢትዮጵያ ተመሳሳይ ከሆነ ዘመነ መሳፍንት ወጥታ የአውሮፓን የበርሊን ስብሰባ እቅድ እና አላማ አክሽፋለች። አማራን እና ኦሮሞን የማጋጨቱ የጠላቱ የጥሊያን ስራም ተወጥታ ለዚህኛው ዘመን ዘልቃ ነበር። ሕወህት ምኞት እንጅ እርሷ በሰፈረችው መሰፈሯ የማይቀር ዛሬ ቢደበዝዝ ጎልቶ የሚወጣ ታጋይ ትውልድ እንደቡቃያ ወጥቷል እና አገራችን ከታሰበላት የሴኦል መንገድ ወደ ብሩህ ሀዲድ ትገባለች። መለያየት፣ የግል ጉዞ ለጠላት አመች እና ጠላት በጥብቅ የሚሰራበት ነው። ዛሬ በማህበራዊ ሚዲያወች ሕወሐት ያሰለፈቻቸው ከአስር ሽህ የማያንስ ሰራዊቷ በተቃዋሚ ስም ሲያሽከረክር የሚውለው ስራ ኢዮጵያውያንን መለያየት፣ በአንድ እንዳይቆሙ ጠንክሮ መስራት ነው። የአገር የቁርጥ ልጆች ይህን መስበር እና መተባበር፣ በአንድ መቆም አንዱ እና ዋነኛው የድል ጥሪ መሆኑን ሊያውቁ ይገባል። እርስ በእርስ መጠላለፍን ትቶ የየግልን ድራሻ በአቅም ማበርከቱ ፋይዳ ይኖረዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!


ሞት ለሕወሐት እና ለትሮይ ፈረሶቿ!!!