የኢህአዴግ አገዛዝ በተለያዩ ሀገሮች ሰላም የማሰከበር ሥራ እየሠራሁ ያለሁት የዓለም የሰላም አስከባሪ ኃይል ነኝ እያለ ብዙ ቢያወራም ባለፉት 26 የአገዛዙ ዓመታት ሕዝባችንን ከፋፍሎ የሚገዛበት ስልቱን እየቀየሰና እየተገበረ ብሔሮችና ብሔረሰቦች እንደዚሁም አጎራባች ክልሎች እርሰበርስ የሚጋጩበትን ሁኔታ ፈጥሮ በመቆየቱ የሀገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነትን እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ጥሎት ይገኛል፡፡ ግዛታቸውን የማስፋፋት አባዜ የተጠናወታቸው የአገዛዙ የክልል ባለሥልጣናቶችና ካድሬዎቹ በክልሎችና ብሔር ብሔረሰቦች መካካል የሚፈጥሩት ግጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በአሁኑ ወቅት በብዙ አከባቢዎች የበርካታ ሰላማዊ ዜጎቻችንን ሕይወት በመቅጠፍና ንብረት በማውደም ላይ ይገኛል፡፡ በዚህም ክስተት የእራሱዋ እያረረባት የሰውን ታማስላለች እንዲሉ በብዙ ሀገሮች ሰላም እያስከበርኩ ነኝ የሚለው የኢህአዴግ አገዛዝ በሀገራችን ውስጥ የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት የማስከበር መንግሥታዊ ኃላፊነቱን በአግባቡ ለመወጣት እንኳን እንዳልቻለ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበለጠ ግልጽ እየሆነ ይገኛል፡፡

PDF ለማንበብ ይሕን ይጫኑት ⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/09/ESDP1.pdf