September 24, 2017


File Photo

ሙሉቀን ተስፋው

ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2010 ዓም ፖሊስ ከደብረ ታቦር ኢየሱስ ተራራ ወደ ከተማ በመውረድ ላይ ባለው ሕዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ ሁለት መስቀል ተሸክመው የነበሩ ዲያቆናት መቁሰላቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ከታቦር ተራራ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ መተከል አለበት የተባለውን ሳትላይት በመቃወማቸው በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፤ ከነዚህም መካከል ባሕታዊ አባ ብርሃኑ ለበርካታ ጊዜያት ሲታሰሩና ሲፈቱ ቆይተው ሰሞኑን እንደገና በመታፈናቸው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ የሔደው ሕዝብ ለማስፈታት በአንድ ላይ በመሆን በመውረድ በነበረበት ጊዜ ነው ተኩስ የተከፈተው፡፡ ይህን ተከትሎም ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን በከፈተው ተኩስ ነው የሃይማኖት አባቶች የቆሰሉት፡፡

ይህ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ጊዜ ከተማው ውጥረት ውስጥ መሆኑንም ለማወቅ ችለናል፡፡