September 24, 2017 08:39

የድረሱልን ጥሪ! ቪዲዮ ይዘናል!
የደብረታቦር ህዝብ ላይ የጭካኔ እርምጃ!
መስከረም 14 2010
ተወዳጁንና የሰላም አባት የሆኑትን ባህታዊ አባ ብርሃን ወያኔ ለሁለተኛ ጊዜ አፍኖ በመውሰዱ የደብረታቦር ህዝብ በሃይማኖታችን ጣልቃ አትግቡ ቢልም ወያኔ የጭካኔ በትሩን እየሰነዘረ ነው። ህዝቡም ጩኸቱን እያሰማ ለሃይማኖታችን እንሞታለን ወገን ድረሱልን እያለ ነው። ይህ የወያኔ አማራንና ኦርቶዶክስ የማፍፋት ተልእኮ ነው። ለደብረታቦር ህዝብ እንድረስለት…በስንቱ….

 

https://youtu.be/y7otTSf016M

ሙሉቀን ተስፋው

ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2010 ዓም ፖሊስ ከደብረ ታቦር ኢየሱስ ተራራ ወደ ከተማ በመውረድ ላይ ባለው ሕዝብ ላይ በከፈተው ተኩስ ቢያንስ ሁለት መስቀል ተሸክመው የነበሩ ዲያቆናት መቁሰላቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ከታቦር ተራራ ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ መተከል አለበት የተባለውን ሳትላይት በመቃወማቸው በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል፤ ከነዚህም መካከል ባሕታዊ አባ ብርሃኑ ለበርካታ ጊዜያት ሲታሰሩና ሲፈቱ ቆይተው ሰሞኑን እንደገና በመታፈናቸው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ለማስቀደስ የሔደው ሕዝብ ለማስፈታት በአንድ ላይ በመሆን በመውረድ በነበረበት ጊዜ ነው ተኩስ የተከፈተው፡፡ ይህን ተከትሎም ፖሊስ ሕዝቡን ለመበተን በከፈተው ተኩስ ነው የሃይማኖት አባቶች የቆሰሉት፡፡

ይህ ሪፖርት በሚዘጋጅበት ጊዜ ከተማው ውጥረት ውስጥ መሆኑንም ለማወቅ ችለናል፡፡

አሳዛኝ ሰበር ዜና

ዛሬ በአሁኑ ሰዓት በደብረታቦር ከተማ ባለፈው ኃሙስ ቀን የታሰሩበትን አባት እንዲፈቱላቸው ከኢየሱስ ቤተክርስትያን ወደ ስላሴ ሲያመሩ በነበሩት የክርስቲያን ምዕመናን ላይ ተኩስ በመክፈቱ ምክንያት በከተማዋ ውስጥ ዳግም አመፅ ተቀስቅሷል ። ወደፊት ዞርዝር መረጃዎች እንደደረሱን የበለጠ እናብራራለን ።
Enat Ethiopia

https://youtu.be/6jR4zZdAmp0