October 10, 2017 11:55

ኢት-ኢኮኖሚ     ET-ECONOMY

‹‹የሀብት ዝውውርን በተመለከተ ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ የሚሆን ተሞክሮ ይገኛል፡፡ ፕራይቬታይዜሽን የሚለው ቃሉን ራሱን የፈጠሩት ማርጋሬት ታቸር መሆናቸው ይነገርላቸዋል፡፡ የእንግሊዞ ጠ/ሚ/ር ማርጋሬት ታቸር የሀገራቸውን ሃድሮ ፓወር ማመንጫ ጣቢያ ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች ነበር በአክሲዮን የሸጡላቸው ይህንን ልምድ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የፕራይቬታይዜሽን ትግበራ ለማዋል እንዴት አልተቻለም?፡፡››1  የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥታዊ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ግል ዘርፍ ኃብትና ንብረት የማዘዋወር፣ነቀላና ተከላ በኢትዮጵ ምድር አልሰመረም፡፡

በኢትዬጵያ የመንግስታዊ ሃብት ዘርፍ አፈጣጠር ታሪካዊ ሁኔታ ስንዳስስ (nationalized: state-owned/ publicly owned) በ1967 ዓም የኢትዬጵያ ወታደራዊ መንግስት፣ በሃገሪቱ ውስጥ የሚገኙ በግል ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ፣ ባንኮችና ኢንሹራንሰ ኩባንያዋችን፣ ፋብሪካዎች፣ እርሻዎች፣ የገጠር መሬት፣ የከተማ ትርፍ ቤቶች፣ ወዘተ በአዋጅ ቁጥር 20/1974 ወደ መንግስት ሃብትነት አዘዋወረ:: በሶሻሊዝም  ርዕዬተ-ዓለም ፍልስፍና ሃገር ለማዝመን ተወጠነ፡፡ የሃገሪቱ የኢኮኖሚ የግብርና፣ የኢንዱስትሪና ስርቪስ ዘርፎች አንጡራ ኃብቶች በብሄራዊ ሃብትና እድገት ሚኒስትር (Ministry of National Resource Development) ስር የተወረሱትን ንብረቶች እንዲያስተዳድር ስልጣንና ሃላፊነት በአዋጅ ተሰጠው፡፡ የኢትዬጵያ ወታደራዊ መንግስት የፖለቲካና ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች በሶሻሊስት የዕቅድ ኢኮኖሚ  በማስፋፋት በአንድ ማዕከላዊ ዕዝ የሚመራ መንግሥታዊ ዘርፍ በአገሪቱ ውስጥ ለ17 ዓመታት አስፈነ፡፡

የህወኃት/ኢህአዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥትም፤ የደርግን መንግሥታዊ ካፒታሊዝምን ውርስ ማለትም  ፋብሪካዎች፣ ባንኮችና ኢንሹራንሰ፣ የከተማ ትርፍ ቤቶችን፣ የገጠር መሬትን፣ የመንግሥት እርሻዎችን ወደ ግል ዘርፍ በስመ ፕራይቬታይዜሽን፣ የወያኔ መንግሥት ወደ እራሱ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ  ኃብትና ንብረትነት በማዘዋወር  ምጣኔ ኃብቱን ተቆጣጠረ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥት የመሬት ፖሊሲ ከደርግ የቀጠለ ሲሆን የደርግ መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ኢህአዴግ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በህወኃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ ኃብትና ንብረትነት ተዘዋወሩ፡፡  ባንኮችና ኢንሹራንሰ፣ የከተማ ትርፍ ቤቶችን፣ የገጠር መሬትን፣ፋብሪካዎች፣ የመንግሥት እርሻዎች በእነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎችና በቢዝነስ አጋሮች ኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ እንዲሁም ጥቂት ባለኃብቶች ሚድሮክ ወዘተ በጋራ የህዝብ ኃብትና ንበረት ተቀራምተው የያዙበት አንባገነን ስርዓት መስረቱ፡፡

ከመንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ግላዊ ዘርፍ የተደረገው የኢኮኖሚ ነቀላና ተከላ ያልተሳካው ለዚህ ነው፡፡  የደርግ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላ በወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ተከላ ተጠናቀቀ፡፡ የህወኃት/ኢህአዴግ የፖለቲካ ፓርቲዎች በ‹‹ልማታዊ መንግሥት›› ስም የኢትዮጵያን ህዝብ አርባና ሃምሳ ዓመታት ለመግዛት እንዲችሉ ኢኮኖሚውን በሙሉ ተቆጣጥረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመለስ ዜናዊ ውርስና ቅርስ የሆነው የሙስና ፋብሪካ ምርት አምራች የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዴሬክተር ጀነራል አሰፋ አብርሃና  ዴሬክተር ጀነራል በየነ ገብረመስቀል  የደርግን መንግሥታዊ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዲግ የፓርቲዎች መንግስታዊ ዘርፍነት በማዘዋወር ‹‹በልማታዊ መንግሥት ስም›› ህዝብን ያጭበረበሩበት የወያኔ መንግሥታዊ ዘርፍ ነቀላና ተከላ ጥናታዊ ዘገባ ሚስጢር እንደሚከተለው ቀርቦል፡፡

‹‹የፕራይቬታይዜሽን››፣ የፋብሪካዎች ሚሊየነሮች!!!

የመንግስት ፋብሪካዎች ከ1994/95 እስከ 2003 ፕራይቬታይዝ የተደረጉ (List of Privatized Stat Owned Factories from 1994/95 up to March 2003)

{1} የኮካኮላ ሁለት ፋብሪካዎች ለኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ፣ የተሸጠበት ዋጋ 64,030,000   ሚሊዩን ብር በ5/15/95 ዓ/ም፡፡

{2} የፔፕሲኮላ ሦስት ፋብሪካዎች ለሞሃ ሶፍት ድሪንክ የተሸጠበት ዋጋ 105,356,891.1ሚሊዩን ብር በ5/15/95 ዓ/ም፡፡

{3} ቅዱስ ጊዩርጊስ ቢራ ፋብሪካ ለቢጂአይ ኢንተርናሽናል፣ የተሸጠበት ዋጋ 74248086.81 ሚሊዩን ብር በ11/5/98 ዓ/ም፡፡

{4} አድዋ ዱቄት ፋብሪካ ለቢሃኒ ባቡላይ ሙዲ የተሸጠበት ዋጋ 20,629,102.43 ሚሊዩን ብር በ7/17/95 ዓ/ም፡፡

{5} ድል የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለአቶ ከበደ ወሰን፣ የተሸጠበት ዋጋ 2,637,564.70 ሚሊዩን ብር በ2/18/99 ዓ/ም፡፡

{6} ዕድገት የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለአቶ ዘውዴ ልየው የተሸጠበት ዋጋ 1,611,899.97 ሚሊዩን ብር በ12/22/99 ዓ/ም፡፡

{7} አዋሳ ድቄት ፋብሪካ ለአበባ ግደይ፣ የተሸጠበት ዋጋ 18,509,250.00 ሚሊዩን ብር በ7/3/00 ዓ/ም፡፡ አዋሳ ድቄት ፋብሪካ  ባንክ ውስጥ 20 ሚሊዩን ብር ተቀማጭ ነበረው፣ለሀወኃት ኢፈርት አበባ ግደይ በነፃ የተሸጠ ድርጅት ነው፡፡

{8} አንበሳ ዱቄት ፋብሪካ ለኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ የተሸጠበት ዋጋ 12,335,082.69 ሚሊዩን ብር በ10/5/95 ዓ/ም፡፡

{9} ድሬዳዎ ምግብ ዘይት ፋብሪካ ለያኒል ጆርዳኒ ኤንድ ጌት፣ የተሸጠበት ዋጋ 1,849,012.44 ሚሊዩን ብር በ7/28/00 ዓ/ም፡፡

{10} ትግራይ ምግብ ዘይት ፋብሪካ ለኢፈርት ለመስፍን ኢንጅነሪንግ የተሸጠበት ዋጋ 334,004.00 ሽህ ብር በ10/16/96 ዓ/ም፡፡

{11} ተራማጅ ምግብ ዘይት ፋብሪካ ለአቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የተሸጠበት ዋጋ 6,945,265.00 ሚሊዩን ብር በ9/25/95 ዓ/ም፡፡

{12} ደብረዘይት ዱቄት ፋብሪካ ለሆራየር ብህንሰን ኤንድ ሰንስ የተሸጠበት ዋጋ 8,000,000.00 ሚሊዩን ብር በ7/17/95 ዓ/ም፡፡

{13} አቃቂ ምግብ ዘይት ፋብሪካ ለብራሌ አግሪካልቸራል ዲቨሎፕመንት፣ የተሸጠበት ዋጋ 2,051,800.00 ሚሊዩን ብር በ2/8/96 ዓ/ም፡፡

{14} ጥቁር አባይ ፈርኒቸር ፋብሪካ ለሰለሃዲን ኢብራሂምና መሃመድ ሃጂ የተሸጠበት ዋጋ 9,359,500 ሚሊዩን ብር በ5/20/98 ዓ/ም፡፡

{15} ፍንፍኔ ሃውስሆልድ ፍርኒቸር ፋብሪካ ለእንዳለ ይርጋ፣ የተሸጠበት ዋጋ 7,110,000.00 ሚሊዩን ብር በ2/7/96 ዓ/ም፡፡

{16} አቫሎ ፕሌይውድ ፋብሪካ ለባላንባራስ መኮንን የተሸጠበት ዋጋ 177,507.69 ሽህ ብር በ9/10/99 ዓ/ም፡፡

{17} ዋንዛ ውድወርክ ሦስት ፋብሪካዎች  ለስታር ቴክኒካል፣ የተሸጠበት ዋጋ 31,980,000.00 ሚሊዩን ብር በ4/25/96 ዓ/ም፡፡

{18} ዋርካ ሃውስሆልድ ፈርኒቸር ፋብሪካ ለአቶ ፍቃዱ አንባዬ የተሸጠበት ዋጋ 8,000,000.00 ሚሊዩን ብር በ8/3/95 ዓ/ም፡፡

{19} ድሬዳዋ ሜታል ፋብሪካ ለሚድሮክ፣ የተሸጠበት ዋጋ 47,035,330.94 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{20} ኮንቦልቻ ሜታል ፋብሪካ ለሚድሮክ የተሸጠበት ዋጋ 15,456,009.85 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{21} መልጋ ወንዶ ስጋና አትክልት ፋብሪካ ለሚድሮክ የተሸጠበት ዋጋ 65,250,738.58 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{22} ኢትዮጵያ ሥጋ ፋብሪካና ኮንሰንትሬትድ ፋክተሪ ለሚድሮክ የተሸጠበት ዋጋ 36,705,044.45 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{23} ጎንደር ሥጋ ፋብሪካ ለሚድሮክ የተሸጠበት ዋጋ 17,211,410.09 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{24} አቃቂ ምግብ ማደራጃ ፋብሪካ ለአቶ ፋሲል ፀጋዬ የተሸጠበት ዋጋ 3,200,000.00 ሚሊዩን ብር ቀንና ዓ/ም አልተጠቀሰም፡፡

{25} ናዝሬት ዱቄት ፋብሪካ ለአቶ ሙዘይን ተ. የተሸጠበት ዋጋ 6,427,681.29 ሚሊዩን ብር ቀንና ዓ/ም አልተጠቀሰም፡፡

{26} አዋሽ ታነሪ ፋብሪካ ለሚድሮክ ኤሊኮ  የተሸጠበት ዋጋ 127,781,850.00 ሚሊዩን ብር በ1/8/98 ዓ/ም፡፡

{27} ዩኒቨርሳል ሌዘር ፕሮዳክት ፋብሪካ ለሚድሮክ ኤሊኮ የተሸጠበት ዋጋ 16,205,000.00 ሚሊዩን ብር በ6/20/97 ዓ/ም፡፡

{28} ድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ለሚስተር አቲላ ይልድሪም የተሸጠበት ዋጋ 111,248,000.00 ሚሊዩን ብር በ12/14/99 ዓ/ም፡፡

{29} አዲስ ሲሜንታል ፕሮዳክት ፋብሪካ ለመሃመድ ይመንና ልጆቹ የተሸጠበት ዋጋ 15,527,000.30 ሚሊዩን ብር በ3/20/96 ዓ/ም፡፡

{30} ፓይል ፋውንዴሽንና ወተር ዌል ድሪሊንግ ኮንስት. ለዋት ኢንተርናሽናል የተሸጠበት ዋጋ 6,201,703ሚሊዩን ብር በ7/2/98 ዓ/ም፡፡

{31} አዲስ ጋዝ ኤንድ ፕላስቲክ  ለስታር ቴክኒካል የተሸጠበት ዋጋ 22,441,000.00 ሚሊዩን ብር በ4/25/96 ዓ/ም፡፡

{32} ጉለሌ ሶፕ ለአቶ ፍፁም ዘአብ አስግዶም የተሸጠበት ዋጋ 22,370,000.00 ሚሊዩን ብር በ12/23/96 ዓ/ም፡፡

{33} አዲስ ካር ባትሪ ለአቶ ሙራድ ሁሴን እና ሌሎች የተሸጠበት ዋጋ 2,906,289.69 ሚሊዩን ብር በ10/19/99 ዓ/ም፡፡

{34} ድል ቀለም ለኢኮቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ የተሸጠበት ዋጋ 35,000,000 ሚሊዩን ብር በ3/28/96 ዓ/ም፡፡

{35} ጎንደር ጂነሪ ለአቶ መሃመድ ኡመር የተሸጠበት ዋጋ 6,790,599.99 ሚሊዩን ብር በ11/5/98 ዓ/ም፡፡

{36}ናሽናል ቶባኮና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ለሼባ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የተሸጠበትዋጋ 285,955,707 ሚሊዩን ብር በ12/23/98 ዓ/ም፡፡

{37} ሃረር ፕሪንቲንግ  ኢንተርፕራይዝ  ለአቶ ፍፁም ዘአብ አስግዶም የተሸጠበት ዋጋ 1,164,000.00 ሚሊዩን ብር በ11/5/98 ዓ/ም፡፡

{38} ኢትዮጵያ ፒክሊንግ ሚድሮክ ኢሊኮ የተሸጠበት ዋጋ 35,500,000 ሚሊዩን ብር በ6/20/97 ዓ/ም፡፡

{39} ህብረት ሜታል ወርክ  ለዛፍ ኢንተርፕራይዝ የተሸጠበት ዋጋ 3,100,000 ሚሊዩን ብር በ12/6/96 ዓ/ም፡፡

{40} ቃሊቲ ስፒኒንግና ሶክ ኒቲንግ  ፋብሪካ ለሸዋ ኮተን ጂኒንግ ፒኤሲ የተሸጠበት ዋጋ 20,646,323 ሚሊዩን ብር በ3/20/00 ዓ/ም፡፡

{41} አቃቂ ብርድ ልብስ ፋብሪካ ለኬኬ ፒኤልሲ የተሸጠበት ዋጋ 10,173,844.43 ሚሊዩን ብር በ3/18/00 ዓ/ም፡፡

{42} አደይ አበባ ድርና ማግ ፋብሪካ ለሚስተር አቲላ ይልድሪም የተሸጠበት ዋጋ 29,040,000.00 ሚሊዩን ብር በ10/2/99 ዓ/ም፡፡

 

{1} በፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ለቀድሞ የፋብሪካ ባለቤቶቻቸው የተመለሱ ፋብሪካዎች ውስጥ፡- ድል የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለአቶ ከበደ ወሰን፣ እድገት የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለአቶ ዘውዴ ልየው፣ ድሬዳዋ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለያኒል ጆርዳኒ ኤንድ ጌት፣ አቫሎ ፕሌይ ውድ ለባላንባራስ መኮንን፣ አዲስ ካር ባትሪ ለአቶ ሙራድ ሁሴንና ሌሎች ንብረታቸው ተመልሶል፡፡

{2} ሜድሮክ ኢትዩጵያ  Midroc Ethiopia ባለቤት ሽህ መሃመድ አላሙዲን ከህወኃት የመንግሥት ፋብሪካዎች ሽያጭ፣ በፕራይቬታይዤሽን ስም ከተቀራመቱት የፋብሪካዎች፣ሶስት የፔፕሲ ኮላ ፋክተሪዎች፣ በሞሃ ሶፍት ድሪንክስ ስም በ(105,356,891.1) ሚሊዮን  ብር፣ በሚድሮክ ስም አምስት  የስጋ ፋብሪካዎች እነሱም  መልጋ ወንዶ ሚት ኤንድ ቬጅቴብል ፋክተሪ (65,250,738.58) ሚሊዮን  ብር፣ ኢትዮጵያን ሚት ኮንሰንትሬትድ ፋክተሪ (36,705,044.45) ሚሊዮን  ብር፣ ጎንደር ሚት ፋክተሪ (17,211,410.09) ሚሊዮን  ብር በርካሽ ዋጋ የተቸበቸበው የህዝብ ንብረት ይጠቀሳሉ፡፡ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፋብሪካዎች በሚድሮክ ኤሊኮ የተገዙ ፋብሪካዎች አዋሽ ታነሪ (127,781,850) ሚሊዮን  ብር፣ ዮኒቨርሳል ሌዘር ፕሮዳክት (16,205,000) ሚሊዮን  ብር፣ ኢትዮጵያ ፒክሊንግ (35,500,000) ሚሊዮን  ብር ገዝተዋል፡፡ ሚድሮክ ሁለት የብረት ፋብሪካዎች ማለትም  ድሬዳዋ ሜታል ፋክተሪ በ(47,035,330.94) ሚሊዮን  ብር፣እና ኮንቦልቻ ሜታል ፋብሪካ (15,456,009.85) ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ በተጨማሪም ስታር ቴክኒካል  Star Technical ባለቤት የሽህ መሃመድ አላሙዲን ዋንዛ ውድ ወርክ ሦስት ፋብሪካዎችን በ31,980,000 ሚሊዮን  ብር፣ እንዲሁም አዲስ ጋዝ ኤንድ ፕላስቲክ በ22,441,000 ሚሊዮን  ብር ገዝተዋል፡፡ በተመሳሳይ ሚድሮ ድል ቀለም ለኢኮቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ስም 35,000,000 ሚሊዩን ብር ገዝቶል፡፡  የሚድሮክ ጠቅላላ የመንግሥት ፋብሪካዎች ግዥ፣ 555,923,275.01 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

{3} ኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ፣East African Bottling፣ሁለት ኮካኮላ ፋክተሪስ በ64,030,000 ሚሊዮን ብርና አንበሳ ዱቄት ፋብሪካ በ12,335,082.69 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡

{4} የመንግሥት ፓርቲዎች ንብረት Government Party property ከመንግሥት ፋብሪካዎች ሽያጭ፣ህወኃት/ ኢፈርት ድርጅቶች ከገዙት ውስጥ የአዋሳ ዱቄት ፋብሪካ በአበባ ግደይ በ18,509,250 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ትግራይ የምግብ ዘይት ፋብሪካ ለመስፍን ኢንጅነሪንግ በ334,004 ሽህ ብር ገዝተዋል፡፡

{5} አቶ ፍፁም ዘአብ አስግዶም የጉለሌ ሳሙና ፋብሪካን በ22,370,000 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም ሃረር ፕሪንቲንግ ፋክተሪ በ1,164,000 ሚሊዮን ብር፣ገዝተዋል፡፡

{6} ሚስተር አቲላ ይልድሪም የድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ በ111,248,000 ሚሊዮን ብር እንዲሁም አደይ አበባ ሱፍ ክር ፋብሪካ በ29,040,000 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ1994/95 እስከ 2003 ፕራይቬታይዝ የተደረጉ 42 የመንግስት ፋብሪካዎች ውስጥ ግማሾቹ ለጥቂት ቢሊየነሮችና ሚሊዮነሮች እንደተሸጡ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ ከ42 ፋብሪካዎች ውስጥ ለሽህ አላሙዲን ሚድሮክና ኤሊኮ (የኢትዮጵያ ሌዘር ካንፓኒ) 12 ፍብሪካዎች ተሸጠዋል፡፡ ለኢስት አፍሪካን ቦትሊንግ፣ ስታር ቴክኒካል  ኩባንያአቶ መሸሻ ቤተማርያም፣ አቶ ፍፁም ዘአብ አስግዶም ከፋብሪካዎች ቅርጫ ሁለት ሁለት መደብ አግኝተዋል፡፡ የእንግሊዞ ጠ/ሚ/ር ማርጋሬት ታቸር የሀገራቸውን ሃድሮ ፓወር ማመንጫ ጣቢያ ለአንድ ሚሊዮን ዜጎች ነበር በአክሲዮን የሸጡላቸው ይህንን ልምድ ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው የፕራይቬታይዜሽን ትግበራ ለማዋል እንዴት አልተቻለም?፡፡››

በኢትዬጵያ ኢህአዲግ ዘመን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ መንግስታዊ ድርጅቶች ወደ ግል ዘርፍ የማዘዋወር ድክመት ዋነኛዎቹ አብይ ምክንያቶች፡- የፕራይቬታይዜሽን መመሪያና የአፈፃፀም ዕቅድ ከኢትዬጵያ ምልዓተ-ህዝብ ለውይይት ያልቀረበ፣በተቃዋሚ ፓርቲዎችም እይታ ያልተዳሰሰ፣በምሁራኖች ጥናት አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያላካተተ ለምሳሌ ፕራይቬታዝ የሚደረጉ ንብረቶችን ህዝቡና ባለሃብቶችን  በመደራጀት በአክሲዮን ባለቤትነት እንዲገዞቸው ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት  የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ በተዘጋው የሴራ በር በስተጀርባ የፕራይቬታይዜሽን ዕቅድና አፈፃፀም ተከናወነ፡፡ በዚህም ምክንያት የህወኃት ፖለቲከኞችና ካድሬዎች የፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲው ግልፅነት በሌለው መልኩ፣ በአድሎና፣ በሙስና ወዘተ ለፖለቲካ ፓርቲዎችና ቢዝነስ አጋሮች ለኢፈርት፣ጥረት፣ዲንሾና ወንዶ እንዲሁም ጥቂት ባለኃብቶች ሚድሮክ ወዘተ የህዝብ ኃብትና ንብረት ቅርምት በሽያጭ ስም አደረጉ፡፡

‹‹አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች›› (SMALL RETAIL SHOPS AND BUSINESS)

{1} ጣና ገበያና 7 መጋዘኖች ለናሽናል ትሬዲንግ ፕራይቬት በቀለ ሞላ ልጆች፣ የተሸጠበት ዋጋ 68,010,020 ሚሊዮን ብር በ10/16/1995 ዓ/ም ተሸጠ፡፡ ሜድሮክ ኢትዩጵያ፣ባለቤት ሽህ መሃመድ አላሙዲን ጣና ገበያና 7 መጋዘኖች ከባንክ ገዝተዋል፡፡

{2}አዲስ ፋና (Addis Fana) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች (SMALL RETAIL SHOPS AND BUSINESS) ውስጥ 41ዱን ማለትም 45 በመቶውን ድርሻ 45,027,408.75 ሚሊዮን ብር የገዛ የህወሃት/ኢህአደግ የፖለቲካ ፓርቲ የንግድ ድርጅት ነው፡፡ ሱቆች ውስጥ ፓኪንግ ስቶርና ሱቅ፣ ስፔር ፓርት መሸጫ፣  አንዋር፣ ሜክሲኮ፣ ሸገር፣ ንፋስ ስልክ፣ ማጨው፣ ጎላ፣ አፋር፣ ባሮ፣ አዲስ ከተማ፣ አምስት ዌር ሃውሶች፣ ስድስት ሱቆች አድዋ ማርኬት፣ ስታዲየም ስቶር፣ መስከረም፣ እድገት፣   አንበሳ፣ አቃቂ፣ ናዝሬት፣  አዳማ፣ አዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ ጎንደር፣ ጂማ፣ ድሬዳዋ፣ ባህር ዳር፣ ኢትፍ ባህር ዳር ቅርንጫፍ፣ ባሮ፣ ነቀምት፣ ደሴ፣ አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ለማኔጀሮችና ሠራተኞች የተላለፉ ይገኙበታል፡፡

{3}ሜጋ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ (Mega Publishing Enterprise) ከተሸጡት 91 የቀድሞው ኩራዝ ፓብሊሽንግ ኢንተርፕራይዝ የነበረው አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 35ቱን ማለትም 38.5 በመቶውን ድርሻ 13,031,048.06 ሚሊዮን ብር የገዛ ህወኃት ኢፈርት ድርጅት ነው፡፡ የመጽሃፍት ሱቆችና ቢዝነሶች በመላ ኢትጵያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

{4}ቴክኒካል ስርቪስ ለኢትዮጵያ ቱሪስት ትሬድ የተሸጠበት ዋጋ 8,777,579.61ሚሊዮን ብር በ8/16/1995 ዓ/ም ተሸጠ፡፡

{5} ሴንትራል ፉድ ፕሮሰስ Central food process ለኢቲቲሲETTCየተሸጠበት ዋጋ 8,752,237.64 ሚሊዮን ብር በ1/17/1997 ዓ/ም፡፡

{6}አቶ ሰኢድ ኢብራሂም (Ato Sahed Ibrahim) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 5ቱን  7,857,209 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሱቆች ውስጥ ፓኪንግ ስቶር፣ ቴድሮስ ስቶር፣ አንድነት ሾፕ፣ዌር ሃውስ ቁጥር 84ና 88 ናቸው፡፡

{7} ኢትፍ ቃሊቲ ስቶር ለፍሪግቶርስ ካርጎ (Freigtors Cargo) የተሸጠበት ዋጋ 4,322,904.04 ሚሊዮን ብር በ4/4/1997 ዓ/ም፡፡

{8} ቴድሮስ ለሶላስት ትራቭል ኤጀንሲ የተሸጠበት ዋጋ 4,101,001 ሚሊዮን ብር በ4/2/1997 ዓ/ም፡፡

{9} ሾፕ ቁጥር አንድ ለጎተራ ካንፓኒ የተሸጠበት ዋጋ 3,502,000 ሚሊዮን ብር በ8/20/1996 ዓ/ም፡፡

{10} ቦሌ ማርኬት ለባለቤቱ የተመለስ፣ለአቶ መስፍን ዓርአያ የተሸጠበት ዋጋ 3,146,061 ሚሊዮን ብር በ12/2/1998 ዓ/ም፡፡

{11} ፈጣን ዌር ሃውስ ለአቶ ፍቃዱ አንባዬ የተሸጠበት ዋጋ 3,000,000 ሚሊዮን  ብር በ4/25/1996 ዓ/ም፡፡

{12} ስታር ፋርማሲዮቲካል ኤንድ ሜዲካል ስፕላይ ሼር ካንፓኒ (Star Pharmaceuticals & Medic. Supp S.C) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን 2,948,541 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሱቆች ውስጥ ሴንትራል ፋርማሲ እና ሂልሰን ፋርማሲ ይገኙበታል፡፡

{13} ሾፕ ቁጥር አራት ለወይዘሮ ስብለወንጌል አለማየሁ የተሸጠበት ዋጋ 2,513,219 ሚሊዮን ብር በ4/25/1996 ዓ/ም፡፡

{14} ኤች ሆል ሴል (H.wholesale) ለአቶ መርሃ ፂዎን ነጋ የተሸጠበት ዋጋ 2,501,000  ሚሊዮን  ብር በ4/2/1997 ዓ/ም፡፡

{15} ጉለሌ ስቶር ለአቶ መሠረት ሰርጉዓለም የተሸጠበት ዋጋ 2,156,000 ሚሊዮን  ብር በ4/4/1997 ዓ/ም፡፡

{16}ወይዘሮ ሃድያ ጎንጂ (W/ro Hadya Gonji) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን ድርሻ 1,787,700 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሱቆች ውስጥ ታጠቅ ሱፕር ማርኬት፣ እና ቁጥር 5 ሱቅ ይገኙበታል፡፡

{17}ድሬ ኢንዱስትሪ (Dire Industry) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን  1,181,988.19 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ ኢትሆፍ አዋሳ ቅርንጫፍ፣ ጂማ፣ ዴዴሳ፣ እና ደሴ ይገኙበታል፡፡

{18} ሾፕ ቁጥር አምስት ለአቶ መሃመድ ሃጂ ዱሪ የተሸጠበት ዋጋ 1,156,502.10 ሚሊዮን  ብር በ12/19/1995 ዓ/ም፡፡

{19}ኦሜዳድ ፕራይቬት ሊሚትድ (Omedad Private Ltd.) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን   1,156,101.00 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሱቆች ውስጥ ኢትዮፍ ጅማ ቅርንጫፍና ኢትዮፍ ናዝሬት ቅርንጫፍ ይገኙበታል፡፡

{20} ድሬዳዋ መደብር  ለኤቲማስ ፒኤልሲ (ITMAS PLC) የተሸጠበት ዋጋ 1,148,342.75 ሚሊዮን  ብር በ1/24/1996 ዓ/ም፡፡

{21} መስከረም አደባባይ ፍንፍኔ ሾፕ ለአቶ አብርሃም ደምሴ የተሸጠበት ዋጋ 1,050,000 ሚሊዮን  ብር በ12/19/1995 ዓ/ም ፡፡

{22} ተክለ ኃይማኖት ሾፕ ለአቶ ማርቆስ ገብረማሪያም የተሸጠበት ዋጋ 1,026,065.10 ሚሊዮን ብር በ12/19/1995 ዓ/ም፡፡

{23} ሲኒማ ራስ (Sinima Ras w.h) ለአቶ አህመድ ኢብራሂም የተሸጠበት ዋጋ 1,007,165.95 ሚሊዮን  ብር በ7/5/1995 ዓ/ም ፡፡

{24} አክሱም ፋርማሲ ለአቶ ሠለሞን የተሸጠበት ዋጋ 1,005,000 ሚሊዮን  ብር በ5/9/1999 ዓ/ም፡፡

{25} ሾፕ ቁጥር አስር ለየኤታ ትሬዲንግ የተሸጠበት ዋጋ 816,544.50 ሽህ  ብር በ12/19/1995 ዓ/ም፡፡

{26} ሾፕ ቁጥር አራት ለወይዘሮ ምፅህላል ገብረእግዚአብሄር የተሸጠበት ዋጋ 783,341.95 ሽህ  ብር በ12/19/1995 ዓ/ም ተሸጠ፡፡

{27}አቶ ከሊፋ አባጆርጋ (Ato Kelifa Abajorga ) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን  739,595.86 ሽህ ብር ገዝተዋል፡፡ ሱቆች ውስጥ ሻሸመኔ እና ዌር ሃውስ ቁጥር ሁለት  ይገኙበታል፡፡

{28} ኢትሆፍ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ለግርማ ወልዴ የተሸጠበት ዋጋ 650,000 ሽህ ብር በ4/4/1997 ዓ/ም፡፡

{29}አዲስ ጎማ ሼር ካንፐኒ (Addis Tyre S.c) ከተሸጡት 91 አነስተኛ የችርቻሮ ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን 643,361.85 ሽህ  ብር ገዝተዋል፡፡

{30} ምስራቅ ሱፕር ማርኬት ለባለቤቱ፣ ለቻራላም ቦስኤም-ቲዚማስ የተመለሰ ዋጋ 586,497.56 ሽህ ብር በ12/1/1998 ዓ/ም፡፡

{31} ቁጥር 1 የህዝብ ፋርማሲ ለአቶ ሲሳይ እንዳለ፣የተሸጠበት ዋጋ 303,690.19 ሽህ ብር በ5/9/1999 ዓ/ም፡፡

{32} መሻለኪያ ሱቅ ለአቶ ዘመረ ጀማነህ፣ የተሸጠበት ዋጋ 255,477 ሽህ ብር በ12/19/1995 ዓ/ም፡፡

{33} አፍንጮ በር ሾፕ ለአቶ መኮንን፣ የተሸጠበት ዋጋ 242,000 ሽህ ብር በ7/2/1998 ዓ/ም፡፡

{34} ሃረር ሱቅ ለአቶ ሙክታር መሃመድ፣ የተሸጠበት ዋጋ 208,499 ሽህ ብር በ4/4/1997 ዓ/ም፡፡

{35} ባህር ዳር ሱቅ ለአቶ ሙኒር ዓሊ፣ የተሸጠበት ዋጋ 87,400 ሽህ ብር በ8/20/1996 ዓ/ም፡፡

{36} ጎባ ሱቅ ለአቶ አህመድ መሃመድ፣ የተሸጠበት ዋጋ 58,000 ሽህ ብር በ4/4/1997 ዓ/ም፡፡

{37} ሾፕ ቁጥር 8 ለወይዘሮ ሊና ሰሚር፣ የተሸጠበት ዋጋ 56,000 ሽህ ብር በ4/25/1996 ዓ/ም፡፡
The relatively very few purchases by either endowment funds or endowment-owned companies of SOEs under the privatisation process are also remarkable: Kuraz publishing (bought by Mega for ETB13million) two pharmacies and one or two hotels seem to be almost the only exceptions.2 (Sarah Vaughan and Mesefin Gebremichael, Aug. 2011)

የህወኃት ኢፈርት የፖለቲካ ንግድ ድርጅት የሆነው ሜጋ ፓብሊሽንግ የኩራዝ ድርጅትን በ13 ሚሊዮን ብር፣ እንዲሁም 2 ፋርማሲዎች እና አንድ ወይም ሁለት ሆቴሎች ከመንግሥት ልማት ድርጅት ኤጀንሲ ገዝቶል፡፡ የኢፈርት፣ በስታር ፋርማሲዮቲካል ኤንድ ሜዲካል ስፕላይ ሼር ካንፓኒ (Star Pharmaceuticals & Medic. Supp S.C) ከተሸጡት 91 ሱቆችና ቢዝነሶች ውስጥ 2ቱን 2,948,541 ሚሊዮን ብር ገዝተዋል፡፡ ሁለቱ ፋርማሲዎቹ  ሴንትራል ፋርማሲ እና ሂልሰን ፋርማሲ ናቸው፡፡ በ1995ዓ/ም ስታር ፋርማሲዮቲካል  25 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያለውና በመቐለ ቢሮ እንዳለው ይታወቃል፡፡ ሚድሮክም ኢፋርም ፋርማሲዮቲካል ከመንግስት ልማት ድርጅቶች ገዝቶል፡፡ The largest of these are MIDROC’s Pharmacure, the SOE EPHARM established in 1972 (currently 50 products and 570 employees),

የህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥትና፣ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ለኢትዬጵያ ህዝብ፣አንደኛ፣ ምን ያህል የመንግስት ኮርፖሬሽኖችና  ንብረቶች እንደነበሩ፣ የስም ዝርዝራቸው፣ ብዛታቸውና ዘርፋቸው ማሳወቅ ግዴታቸው ነበር፡፡ ሁለተኛ፣ በፕራይቬታይዜሽን ወደ ግል ባለቤትነት  ለነማን ተሸጡ የደሃው ዜጋ መታወቂያ ላይ ብሄርህ የሚል እስካለ የገዥዎቹ ‹‹ብሄራቸውስ!!!››፣ በምን ያህል ዋጋ፣ የአፈፃፀሙ ሁኔታና ክትትሉ ሪፖርት መደረግ ነበረበት፡፡ ሦስተኛ፣ ቀሪዎቹ  የመንግስት ኮርፖሬሽኖችና  ንብረቶች የትኞቹ ናቸው፡፡ አራተኛ፣ መንግስት ከፕራይቬታይዜሽን ገቢዎች ምን ያህል ገንዘብ ወሰደ፣ ገንዘቡን በየትኛው የልማት ዘርፍ ላይ አዋለው፡፡ ወደ ግሉ ዘርፍ ንብረትነትና ባለቤትነትን የተዘዋወሩት ድርጅቶች የነበራቸው የሰው ሃይል ብዛት ወደ ግል ዘርፍ ከተዘዋወረ በኃላ ያለው የሰው ሃይል ቁጥር ለህዝብና ለጋዜጠኞች  በየግዜው መገለፅ ነበረበት፡፡ የፕራይቬታይዜሽን ዋና ዓላማዎች  ስራ ፈጠራ፣ ምርታማነትን መጨመርና የገቢ ምንጭ በማዳበር የሃገራችንን ልማት ማፋጠን ሲሆን አትራፊ የሆኑ ድርጅቶች መሸጥ አግባብነት አይኖረውም፡፡ ከዚህ አካያ በኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ወደ ብራይቬታይዜሽን መሸጋገሩ እሙን ሆኖል፡፡ የመሬት ሃብት ከኢህአዲግ መንግስት ንብረትነትና፣ ከመንግስት ዘርፍ ወደ ግሉ ዘርፍ የሚዘዋወረው መቼ ይሆን፡፡ በደርግ የተወረሱት መንግሥታዊ የኢኮኖሚ ዘርፍ ወደ ህወኃት/ኢህአዴግ መንግሥታዊ ዘርፍ መሸጋገራቸውን ጥናታዊ ማስረጃው ያሳያል፡፡ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን ተጨማሪ ጥናቶች በማድረግ ለህዝብ ማሳወቅ የዜግነት ግዴታና ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ምሁራኖች በሚያውቁትና ማበርከት በሚችሉት የእውቀት  ችሎታ (በምጣኔ ኃብት፣ በታሪክ፣ በስታትስቲክስ፣ በህክምና፣ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ ወዘተ) በጋራ ሆኖ በመሰባሰብ በጥናት ላይ የተደገፈ መረጃዎችን ለህዝብ የማቅረብ ባህል እንዲያዳብሩና በተለያዩ የሃገራችን ቆንቆዎች  ተተርጉመው በኢሳት፣በኦሮሞ ቴሌቪዝንና ሬዲዬ ጣቢያዎች ማቅረብ የግዜው አንገብጋቢ አጀንዳ መሆን ይኖርበታል፡፡

ምንጭ

{1} Michael P. Mclindon (1960, Privatization and capital market development:- strategies to promote economic growth) (የኢኮኖሚ ስነ-ምህዳር በውብሽት ጌታሁን 2002ዓ/ም ገፅ 64)

{2} Privatization and Public enterprises supervising agency, own competition and Amharic translation.

{3} Rethinking business and politics in Ethiopia,sarah Vaughan and Mesefin Gebremichael, August 2011.