October 12, 20

መቸም ወያኔ የማህበራዊ ሚዲያውን የፖለቲካ ትግል በማህበራዊ ሚዲያው በመመከት የመልስ ምት እና ስልታዊ የሆነ አዳዲስ አጀንዳ በራሱ ሰዎች እና ተቋማት በመልቀቅ የማህበራዊ ሚዲያውን የጦር ሰራዊት ስራ ያበዛበት ይመስለኛል፡፡

ወያኔ በርግጥ ሃሳብን ለመግለጽና የድርጅቱን ፖለቲካዊ ኪሳራ ለማሳየት የሚጻፉ ጽሁፎች እና ጸሃፊያን ጋር ያለው ጠላትነት የተጠበቀ ቢሆንም ነገር ግን ይህ የወያኔን በየጊዜው አጀንዳ የመፍጠር የፖለቲካ ስልት ሊታወቅበት ይገባል፡፡ ይህንን ያልኩበት ምክንያት ሰሞነኛ የወያኔ የአባዱላ(ምናሴ)ተረት ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባ ነገር የተከዜ ማዶ የጫካ ሰዎች ከተማ ሲገቡ በሁሉም ክልሎች ላይ የመሰረቱት የፖለቲካ ድርጅቶች በወያኔ ዘገምተኞች እጅ ተጠፍጥፈው የተሰሩ ሰዎች እና የራሳቸው በሆኑ ሰዎች የተመሰረቱ ናቸው፡፡ የዚህ ሃሳብ ብቸኛ ማሳያ በክልሎች ውስጥ የሚፈጠረው አፈና ግድያ እና ችግር በወያኔ ነፍሰ በላ አጋዚ ሲፈጸም ህዝቡን እንወክልሃለን የሚሉት የክልሎች መንግስታት አፈናውን ከማገዝ ውጭ እንወክለዋለን የሚሉትን ህዝብ ከሞት አላዳኑትም ምክንያቱም ሁሉም የክልሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የህውኅት የግሉ ትእዛዝ ተቀባይ ማሽኖች ናቸውና፡፡ 

አባዱላ ገመዳም የዚህ ትእዛዝ ተቀባይ ማሽን ዋናው ዘዋሪ ነው፡፡ አባዱላ ገመዳ ትክክለኛ ስሙ ምናሴ ወልደጊዪርጊስ ሲሆን የኦሮሞን ህዝብ የማይወክል የተከዜ ማዶ ሰዎች ማፌያ ቡድን አባል ነው፡፡ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት በነበረበት ዘመንም ብዙ የኦሮሞ ህዝብን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚታገሉ ሰዎችን አሳልፎ በመስጠት እንዲገደሉ አድርጓል፡፡ አባዱላ(ምናሴ)ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ የወያኔ የስልጣን እርከኖች የሰሩ ሲሆን ከነዚህም

*የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ኦፕሬሽን መምሪያ ሀላፊ

*የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የምድር ጦር አዛዥ

*የመከላከያ ሚንስቴር ምኒስትር እና የጦር ጀኔራል

*የደህንነት ቢሮ ሀላፊ

*የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት

እነዚህ ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ በነዚህ ተቋማትም በተለይ ኦዲት በማይደረገው የመከላከያ ተቋም ውስጥ ከቱባ የህውሓት ሰዎች ጋር በቂ የሚባል የሃገሪቱን ሃብት የዘረፉ ሲሆን ከዚህ በፊትም መቸም ሌባ ሲሰርቅ ሳይሆን ሲካፈል እንደሚጣላው ሲካፈሉ በመጣላታቸው አለቆቹ የተከዜ ማዶ ፍሽስቶች የእስር ማዘዣ ሲቆርጡባቸው የሚያምረውንና በውድ ዋጋ የተሰራውን መኖሪያ ቤታቸውን ተሽጦ ለኢሃዴግ እንዲሰጥ ሲወስኑ የእስር ትእዛዙ ተቀይሮ የአሁኑ ስልጣን የተሰጣቸው ሲሆን የወያኔ ፈረሱ አባዱላ ለአሁኑ መልቀቂያ ዋናው ምክንያት አንዱ የማህበራዊ ሚዲያውን ቀይ ካርድ ለመምዘዝ ሲሆን ከዚህ ውጭ ምናልባትም ሁለት አንድምታ አለው፡፡

1.ይህ ወቅት የታምራት ላይኔን ግዜ ያስታውሳል ምናልባት ከወያኔ ጋር የዘረፉትን ሃብት ሲከፋፈሉ ባለመስማማታቸው ምክንያት ባለቆቹ ታዞ መልቀቂያውን እንዲያስገባ ያ ካልሆነም ተቋርጦ የነበረው ክስ የሚቀጥልበት ይመስላል፡፡

2.ሌላኛው መንገድ ደግሞ አባ ዱላን የህዝብ ወገንተኝነት ያለው በማስመሰል ሰሞኑን በኦሮምያና ሶማሊ ክልሎች ላይ በተነሳው የድንበር ግጭት ልዩነት ያለው በማስመሰል በአዲስ ስታንዳርድና በሌሎች የመንግስት ሚዲያዎች እንዲነገር ማድረጋቸው ያው አባ ዱላን ሌላ ማሊያ በማልበስ ወደ ኦሮሚያ ክልል በመሾም ሌላ ግድያ እና እልቂት እንዲፈጸም ሃሪፍ ተዋናይ ለማድረግ ከማሰብ ውጭ አባ ዱላ ከተከዜ ማዶ አለቆቹ ትዕዛዝ ውጭ ወጥቶ ለመቃወም የሚያስችል አቅምም ሆነ ብቃቱ የለውም ምክንያቱም እሱም ልክ እንደ ሌሎች ባለስልጣኖች አፉን ሞልቶ ለህዝብ ከቆመ የሚመዘዙ የአፍ ማዘጊያ የሙስና ፍይሎች ስላሉ መዘዝ ማድረግ ብቻ ነው፡፡

እናም አባዱላ እንዲህ ብለዋል በግብጹ ናይል ቲቪ

«one said love is never die.so,if their is a love,a trust b/n us never die.»         

እናም ምናልባት ይሄ አነጋጋሪው የአባዱላ መተማመን ወይስ ፍቅር ይሆን ያለቀው?

ሰሎሞን ይመኑ

https://www.youtube.com/watch?time_continue=1&v=VTfEozXWqEs