የወያኔ መንግስት ሁለገብ በሆኑ  መንግስታዊ  የጥንካሬ መመዘኛ መስፈርቶች ሲገመገም ያለ-ጥርጥር መሰረቱ ተናግቶ ኣገርን መምራት ከማይችልበት ደረጀ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ በጅምላ እብደት ውስጥ የሚባክነው የወያኔ ኣመራር የኢትዮጵያ ህዝብ በ-27 ኣመት ረጅም ጎሳዊ ኣገዛዝ ተንገሽግሾ ለውጥ ሲጠይቅ፣ የለውጡን ጥያቄ በኣግባቡ ከመረዳት ይልቅ በመደናበር ይባስ ብሎ የለውጡን-ፍኖት በፀረ ትግሬነት  በመፈረጅ በንዴት ጥርሱን እየቃጨ በገልፍተኝነት ለመበቀል እየተሯሯጠ ነው፡፡ ይህ እርምጃ ደግሞ የትግርይን ህዝብ ህልውና ኣደጋ ላይ የሚጥል ሀላፊነት የጎደለው የቀብጸ-ተስፋ እርማጃ ነው፡፡

 

የወያኔው መሰሪ-ቡድን ሁሉንም ካርዶቹን  መዞ ጨርሷል፡፡ ቡድኑ እንደመፍትሄ በ-2 ስትራተጂዎች ላይ ብቻ ኣተኩሮ ስልጣን ላይ ተንጠልጥሎ የመጨረሻዋን ኣስከፊ ጽዋ ለመጋት እና ብሎም ኣገሪቱ  ወደ ከፋ ጎሳዊ ጦርነት ለመዘፈቅ መወሰኑ ታውቁል፡፡

 

የወያኔ 2-ቱ ስትራተጂዎች፡ (1) በኣንድ ጎሳ በተገነባ ሰራዊት አና ጸጥታ-ሀይል መተማመን (2) በብኣዴን እና ኦፒዲኦ ውስጥ የሚገኙ የወያኔን የበላይነትን መጋፋት የጀመሩ ኣባላትን በተሀድሶ ሰበብ ማባረር ካልተቻለም በራሱ ጎሳ ባደራጀው ሰራዊት ሀይል ተጠቅሞ    በማስወገድ ለቡድኑ ታማኝ በሆኑ ሆድ-ኣደር ግብዞች በመተካት ክልሎችን እንደገና መቆጣጠር :: ሲጠቃለል ግን ተጨመረ ተቀነሰ ይህ ስትራተጂ  መሰረታዊ ለውጥ ኣምጥቶ የወያኔን መንግስት ወደ ታሪክ ትቢያ ከመውረድ ኣይታደገውም፡፡

 

ታሪክ ምስክር ከሆነ፣  2-ቱ የተጠቀሱት የወያኔ  ስትራተጂዎች የመጨረሻ ውጤታቸው ሀገርን ከማጥፋት ውጭ የሚፈይዱት ነገር የለም ፡፡በተለይ ደግሞ በኣንድ ጎሳ የሚመራ ሰራዊት እና የጸጥታ ሀይልን ተጠቅሞ የብዙሀንን ፍልጎት ጨፍልቆ ስልጣን ላይ ለመቆየት መጣር ታሪክ ይቅር የማይለው የጥፋቶች ሁሉ ጥፋት እና የለየለት የጅምላ እብደት ነው፡፡

 

ወያኔ ምንም እንኽዋ ህዝቡ ከዳር-እስከ-ዳር ኣንቅሮ እንደተፋው የተገነዘበ ቢሆንም ግን ለኣንድ ሰከንድም ቢሆን በሰላም ስልጣንን ለህዝብ ማስረከብ እንደመፍትሄ  በኣማራጭነት ኣይቶ  ኣያውቅም፡፡ ወያኔው ገፋ ሲል ኣንዳድ ኣባላቶቹን በተሀድሶ ስም ከመለዋወጥ ውጭ ሌላ መሰረታዊ ለሀገር የሚበጅ ህልም የለውም፡፡ ለዚህ ለወያኔ ዜጋዊ-ሀላፊነት መጙደል ምክኒያቶች ብዙ ቢሆኑም በዋናነት ግን “ ኣመራሩ በጅምላ እብደት/ Tplf Collective Madness”  ኣዙሪት ውስጥ የሚዋዥቅ  የመንድር ስብስብ በመሆኑ ነው፡፡

 

የወያኔው ኣመራር በሚያሳየው የኣመራር ጸባይ (Leadership Behavior)  በጥልቅ ሲገመገም PTSD – Post Traumatic Disorder በሚባለው  የቀውስ በሽታ የተጠቃ ይመስላል፡፡  ይህ በሽታ የሚያጠቃው በጦርነት ውስጥ ባለፉ እና ኣሰቃቂ ድርጊቶችን በሌሎች ገለሰቦች እና ቡድኖች ላይ በፈጸሙ ሰዎች ላይ ነው፡፡

 

እንደሚታወቀው የወያኔ ኣመራር ከሞላ ጎደል ሁሉም  በጦርነት ውስጥ ያለፉ ሲሆን እነሱን በሚቃወሙ ቡድኖች አና ግለሰቦች ላይ የሚዘገንን ኣሰቃቂ እርምጃዎች ፈጽመዋል፡፡  (1) ለምሳሌ ፊታውራሪ ኪሮስ በተባሉ ዜጋ ላይ ኣድዋ ውስጥ ከነ-ህይወታቸው ገደል ሰደዋል (2) ኣቶ ገዛኢ የተባሉ ሽሬ ከተማ  የቡና ቤት ባለቤት ኣስረው ጉድጙድ ውስጥ በእሳት ለብለበዋል፡፡ የኣምልኮት ቦታዎችን ኣርክሰዋል፡፡ በመላ ሀግሪቱ  ውስጥ በዜጎች ላይ የፈጸሙትን ኢ-ሰብኣዊ ድርጊት ቤቱ ይቅጠረው፡፡ ….ወዘተ፡፡ ሁሉም እርምጃዎች ተደምረው ሲታዩ ኣመራሩ የፈጸማቸው እና በመውሰድ ላይ ያሉ እርምጃዎች  PTSD ውጤቶች ናቸው፡፡

 

ወያኔውች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ካላቸው ብርቱ ኣላማ በዋናነት የጎሳን ፖለቲካ ፍጹም የማይቀየር ሌላ ኣማራጭ የሌለው ፣ ከመጽሀፍ ቅዱስ እና ቅዱስ ቁርኣን በላይ እንደቅዱስ ቆጥረው እንደ-ብቸኛ  መፍቲሄ በመውሰድ ኣገሪቱን በጎሳ ጦርነት ውስጥ ዘፈቅዋል፡፡ ከወያኔው ኣመራር ውስጥ ኣንድም ቢሆን የሰከነ ድምጽ ኣይሰማም፡፡የወያኔ የጅምላ የእብደት የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

 

ለምሳሌ ከዚህ በታች ለኣብነት ያክል የተዘረዘሩት የወያኔ ፖሊሲዎች በጥልቀት ሲመረመሩ ከመልካም ምኞት እና ከሀገር ፍቅር የመነጩ ኣይደሉም፡፡ እንዳውም ሆን ተብሎ ኣገርን ኣደጋ ላይ ለመጣል ታቅዶ የተቀረጹ ናቸው፡-

  • የጎሳ ፖለቲካን በፍጹማዊነት ማምለክ
  • የትግራይን ህዝብ ከመላው ኢትዮጵያዊ ጋር ኣጋጭቶ ህልውናውን ኣደጋ ላይ መጣል
  • ከታሪክ ውጭ የትግራይን ግዛት ማስፋፍት
  • የሀገሪቱን ትላልቅ ጎሳዎች በጠላትነት መፈረጅ
  • ደርግ በራሱ ክብደት እና በህዝብ እምቢተኝነት ቢወገድም ወያኔ በብቸኝነት ደርግን ጥለናል ብሎ መኩራራት
  • ደርግን እና የኢትዮጵያን ህዝብ በኣንድ ላይ እንዳሸነፉ ኣድርጎ መቁጠር
  • ኢትዮጵያዊነትን ኣዳክሞ የጎሳ ብሄርተኝነት ማበልጸግ
  • የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት ከወያኔ ጥቅም ኣንጻር ብቻ መመልከት
  • የሀገሪቱን መከላከያ ሰራዊትን እና የጸጥታ መዋቅር የህወሀት የግል ተቕዋም ማድረግ
  • የህወሀት ድርጅታዊ ጥቅም ከሀገሪቱ ጥቅም በላይ ኣድርጎ ማየት
  • የፈደራል መዋቅሮችን በብቸኝነት መቆጣጠር
  • የሀገሪቱን ቁልፍ ኢኮኖሚን መቆጣጠር
  • ያለገደብ ስልጣን ላይ  ለዘመናት በብቸኝነት ለመምራት ሁኔታዎችን ማመቻቸት….ወዘተ

ወያኔውች ሰሞኑን ደግሞ  በኦሮሞ እና ኦጋዴን ኢትዮጵያውያን ዜጎች መሀከል ኣስቀያሚ እና እጥፊ ጦርነቶች ቀስቅሰው የጦር ሀይል  ኣዛዥቸውን ፕሮፌሰር ዶክተር ጀኔራል ሳሞራ የኑስን ወደ ሱዳን በመላክ ከሳምንት በላይ ቆይቶ ከሱዳን መንግስት ሽልማት እንዲያገኝ ኣድርገዋል፡፡ ይህ ድርጊት ወያኔዎች ምን ያህል እንደዘቀጡ እና ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ደንታ እንደሌላቸው ብርቱ ምስክር ነው፡፡

 

ወያኔዎች በየቦታው የቀሰቀሱትን የጎሳ ግጭቶች መስማት ከጀመርን ቆይተናል፡፡  ኣስደንቃጋጭነቱን  ኣልፈን እየተለማምድናቸው መጥተናል፡፡ ኣሳዛኝ ክሰት፡፡ ከወዲሁ ተባብረን መፍቴሄ ካልገኘን ሀገራችን ወያኔ ወደ ደገሰላት ቀውስ እየተዘፈቀች ነው፡፡ ይህ ኣስፈሪ ቀውስ ብዙ ሳንቆይ በቅርብ የምናየው ይሆናል፡፡ በኣንድ ኢትዮጵያዊነት ስር ተሰባስቦ ኢትዮጵያን መታደግ ነገ ሳይሆን ዛሬ ነው፡፡

ጦብያን ኣምላክ ይጠብቅ !!