10 ኖቬምበር 2017

ልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን እና ኢማኑኤል ማክሮን ሃሙስ በሪያድ ተገናኝተዋል

አጭር የምስል መግለጫልዑል አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሰልማን እና ኢማኑኤል ማክሮን ሃሙስ በሪያድ ተገናኝተዋል

የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሳዑዲ ያልተጠበቀ ጉብኘት በጀመሩበት ወቅት የሊባኖስ መረጋጋት አስፈላጊ ስለሆነ በጉዳዩ ላይ ትኩረት እሰጣለው ሲሉ ተድምጠዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳድ ሃሪሪ ሪያድ ሆነው ለሕይወቴ ሰግቻለው በማለት በፍቃዳቸው ሥራ መልቀቃቸው ይታወሳል።

እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጫና ሳያሳድሩባቸው አልቀረም ተብሏል።

ማክሮን በየመን ስላለው ቀውስ ከሳውዲ ባለስልጣናት ጋር እወያያለሁም ብለዋል።

የሳውዲ መራሹ ጥምር ኃይል በየመን የመጓጓዣ ዘዴዎችን ከዘጋ በኋላ የእርዳታ ቁሶችን ወደ የመን ማስገባት እንዳልቻለ የተባበሩት መንግሥታት ማስታወቁ አይዘነጋም።

ባለፈው ሰኞ የየመን ሁቲ አማጺያን ወደ ሳዑዲ ሚሳዬል ከተኮሱ በኋላ ነበር ጥምር ኃይሉ ወደ የመን የሚደረጉ የአየር፣ የየብስ እና የምድር መጓጓዣ ዘዴዎችን በሙሉ ዝግ ያደረገው።

ሳዑዲ ለጥቃቱ በኢራን የሚደገፈውን የሊባኖስ ሚሊሻ ቡድን ሄዝቦላህን ተጠያቂ ታደርጋለች።

የመንየዓለማችን አስከፊው ረሃብተጋርጦባታል

ትናትን ሳዑድ አረቢያ በለሊባኖስ የሚገኙ ዜጎቿ በአስቸኳይ ሃገሪቱን ጥለው እንዲወጡ አሳስባለች።

ማክሮን ወደ ሳዑዲ ከማቅናታቸው በፊት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ባደረጉት ንግግር ከሳዑዲው አልጋ ወራሽ ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተው እንደሚወያዩ ተናግረዋል።

”በሊባኖስ መረጋጋት እና አንድነት” ዙሪያ ትኩረት ሰጥተው እንደሚወያዩ አሳውቀዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዝዳነት ከቀድሞ የሊባኖሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሪሪ ጋር መነጋገራቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

አጭር የምስል መግለጫየሃሪሪ ስልጣን መልቀቀ በሌባኖስ የለመረጋጋትን ፈጥሯል

የሃሪሪ ስልጣን መልቀቀ በሌባኖስ የለመረጋጋትን ፈጥሯል

ሃሪሪ ሳዑዲ ሆነው በሰጡት መግለጫ በፍቃዴ ስልጣን መልቀቅ የፈለኩት በስልጣን መቆየቴ ለሕይወቴ አስጊ ስለሆነ ነው ብለዋል።

በሰጡት መግለጫ በሊባኖስ ጠንካራ ወታደራዊ አቋም ያለውን ሄዝቦላህን ኮንነዋል።

እአአ በ2005 የሃሪሪ አባት እና የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ራፊክ ሂዝቦላህ አጥምዶታል በተባለ ቦንብ ተገድለዋል።

በሌላ በኩል ሄዝቦላህ ሃሪሪ ከስልጣናቸው የለቀቁት በሳዑዲ አረቢያ ግፊት ነው ይላል።