November 10, 2017

Samson Genene

በአንድ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚኖር የማህበረስብ ስብጥር በሉዓላዊ ግዛት ውስጥ ኧንዲኖር ያደረገው ታሪካዊ ገፊ ምክንያቶች ኧንዳሉ ሆነው ማህበረሰቡ በአንድ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ አብሮ መኖሩን ተከትሎ በጋራ አብሮ ለመኖር ህግ  ኧና ህጉን የሚያስፈጥም አካል መኖር ኧንደሚገባ የስው ልጅ ያለፈባቸው ማህበረሰባዊ ኧድገቶች ማሳያ ናችው።

የህዝብ መጠንን፣ መልካአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ ማህበራዊ ኧና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብርን ወዘተ ማኧከል ባደረገ መልኩ በአንድ ሉአላዊ ሃገር የሚኖሩ ህዝቦችን በጋራ የሚያኖር ስርአትም ሆነ ስርአተ መንግስት በባህሪው ዲሞክራሲያዊም ሆነ አንባገነናዊ  ለመሆኑ በዋነኛነት መንስኤው ማህበራዊ ስርአቱም ሆነ ስርአተ መንግስቱ ባለው ህዝባዊ ውክልና ኧና ህዝባዊ ቅቡልነቱ ላይ የተንጠለጠለ ነው። ይህም ማለት በአንድ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦችን የሚያስተዳድረው ስርአተ መንግስት በሚያስተዳደራቸው ህዝቦች ላይ ሊያመጣ የሚችለው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ኧና ፓለቲካዊ መሻሻሎች ስርአተ መንግስቱ ከሚኖረው ህዝባዊ ቅቡልነት ጋር በዋነኝነት የተጋመደ ነው ኧንደማለት ነው።

በአንድ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚኖሩ ህዝቦችን ለማስተዳደር ህዝባዊ ውክልናን ማአከል ባደረገ መልኩ ተግባራዊ ከሚሆኑ መንግስታዊ ስርአቶች መሃል ፌደራላዊ መንግስታዊ ስርአት አንዱ ነው። አወቃቀሩንም ሆነ ለአከላለሉ መነሻ አድርጎ የተነሳበት ንድፈሀሳባዊም ሆነ ነባራዊ ምክንያቶቹ በውል የማይታወቀው የህወሃት-ኢህአዲግ የፌደራሊዝም ስርአት ላለፉት ሀያ አምስት አመታት ከሃገራችን ሰማይ ስር ከፈጠረው ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ኧና ፓለቲካዊ ቀውስ በተጨማሪ አሁን ላይ እራሱን የቻለ ሃገራዊ አደጋ የፈጠረበት ሰአት ላይ ደርሰናል።

እንደ እኔ እምነት አሁን ላይ ስርአቱ ከሀያ አምስት አመታት በፊት የፌደራሊዝም ስርአቱን ሲያዋቅር ህወሃታዊ ሚስጥር ያደረገውን ፓለቲካዊ ሴራ ኧና ፓለቲካዊ ውሳኔ  አሁን ላይ በሃገሪታ የተከሰተውን ህዝባዊ አመጽ ኧና ተቃውሞ መነሳቱን ተከትሎ በህወሃት የሚዘወረው ኢህአዴግ የወሰደው ኧና ኧየወሰደው ያለው ፓለቲካዊ ውሳኔ ኧና ፓለቲካዊ ሴራ ግልጥ ያደረገው ይመስለኛል። ሃገራችንን በዘጠኝ ክልሎች ኧና በሁለት የከተማ አስተዳድሮች ሸንሽኖ የሃገራችንን ህዝቦች ኧያስተዳደረ የሚገኘው ህወሃት-ኢህአዴግ ፣ አንድ የፌደራሊዝም ስርአት መንግስት ሊያስገኘው የሚችለውን ቱርፋት ለሃገራችን ህዝቦች ከማጎናጠፍ ይልቅ ከሃገራችን ሰማይ ስር ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በላይ  ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ኧና ፓለቲካዊ ተግዳሮቶች ኧንዲከሰቱ መንሳኤ ለመሆኑ እልፍ ማሳያዎችን በመጥቀስ መሞገት የሚቻል ይመስለኛል።

ከ አራት ሚሊዮን በላይ ብዛት ያለውን የሲዳማ ብሄር ከሃምሳ በላይ ከሚሆኑ በደቡቡ የሃገራችን ክፍል ከሚገኙ ብሄረሰቦች ጋር አጣምሮ በአንድ ክልል ስር እያኖረ፣ ክስላሳ ሺህ በላይ ለማይሆነው የሃረሪ ብሄር ታሪካዊታን እና የብዙ ብሄር መኖሪያ የሆነችውን ሃረርን እንዲያስተዳድር የሰጠው የህወሃት-ኢህአዴጉ የፌደራሊዝም ስርአት ውጤቱ በነቢር ሲታይ  የብዙሃኑን ህዝብ በተለይም የወጣቱን ትውልድ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቀሶ የመስራት፣ ሃብት የማፍራት፣ ኧንዲሁም በሃገሪታ በየተኛውም ግዛት ተንቀሳቅሶ ፓለቲካዊ ሃላፊነቱን ኧንዳይወጣ ማነቆ የሆነ ስርአት ነው።

በፌደራል መንግስት ውስጥ የህወሃትን የፓለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ የበላይነትን ማስጠበቅን ባሰላሰለ መልኩ የተጎነጎነው የየህወሃት-ኢህአዴግ የፌደራሊዝም ስርአት የህዝቦችን በተለይም የግለሰቦችን በነጣነት ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራትን መብት የገደበ፣ በህዝቦች መሀል የነበረን ታሪካዊ እና ደማዊ ትሥስር  ለሃገራዊ ልማት ከማዋል ይልቅ በሃገር ግንባታ ወቅት በታሪክ አጋጣሚ የተከሰቱ ግጭቶችን በማጉላት ኧና የህዝቦች ለዩነትን በሚያጎላ መልኩ የተሰላሰል ማህበራዊ አካሄድ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የሃገራችን ፓለቲካዊ ምህዳር በህወሃት የበላይነት  እንዲዘወር የህወሃት-ኢህአዴግ የፌደራሊዝም ስርአት ከፍተኛውን ሚና ተጫውታል።

የህወሃት ኢህአዴግ የፌደራሊዝም ስርአት የህወሃትን ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ የበላይነትን ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት እያስጠበቀ ቢጋዝም ፣ አሁን ላይ ስርአቱ ከጥቂቶች በቀር ለብዙሃኑ እንዳልጠቀመ፣  ብዙሃኑ የሃገሪቱ ህዝብ በተለይም የነገ የሃገሪቱ ተረካቢ የሆነው ወጣቱ ትውልድ በመረዳቱ  ሃገሪታን ከዳር እስከ ዳር ባካለለ መልኩ ሞት ለወያኔ፣ ወያኔ ሌባ፣      Down Down Weyane የሚሉ ድምጦችን በማሰማት ስርአቱ ስልጣን እንዲለቅ እየጠይቀ የሚገኝበት ሰአት ላይ ደርሰናል።  አሁን ላይ ሃገራችን በአንድ በኩል ብዙሃኑ ህዝብ በህወሃት አገዛዝ ከመማረሩ ባለፈ ህወሃት በበላይነት የሚዘውረው ኢህአዴግ ከስላጣን እንዲወርድ ድምጡን እያሰማ የሚገኝበት፣ በሌላ በኩል ህወሃት ኢህአዴግ ከስልጣን ላለመውረድ በህዝቦች እልቂት ኧና ደም ካርድ የሚጫወትበት አንገብጋቢ ጊዜ ላይ ደርሳለች።

የህወሃት ኢህአዴግ የፌደራሊዝም ስርአት ስራ አጥ፣ ነጣነት አልባ፣ የበይ ተመልካች ያደረገው ብዙህኑ ወጣት ከአገዛዙ ተላላኪ ቅጥረኛ ገዳዮች ጋር እየተጋፈጥ፣ እየወደቀ እየተነሳ እንዲሁም እየሞተ ለሀገሩም ሆነ ለራሱ ነጣነት ክቡር ህይወቱን እየሰጠ የሚገኝበት ወቅት እንደመሆኑ በእኔ እምነት እንደ ህዝብ ከልዩነት ይልቅ አንድንታችን ላይ ማተኮሩ የህወሃትን የበላይነት ከማረጋገጥ ውጪ ለብዙህኑ ሀዝብ ምንም ያልፈየደውን የህወሃት ኢህአዴጉን የፌደራሊዝም ስርአት ለመደርመስም ሆን የስርአቱን ሞት በማፋጠን ህዝባዊ መንግስትም ሆነ ህዝብ ያመነበት፣ሙሁራን፣ነጣ እና ገለልተኛ ተቃማት የመከሩበተ እውነተኛ የፌደራሊዝም ስርአት በሃገራችን ለመገንባት የሚያስችለን ይመስለኛል።