ኢትዮጵያ- ደራሲ ይታገሱ በፌስቡክ ገጹ ፤ ዛሬ በማለዳ አዲስ አበባ ሰቴዲየም በሚገኘው የፓውዛ መበራት በአንደኛው ላይ በጠዋቱ በፓውዛው አናት በመብራቱ ጫፍ ላይ አንድ ሰው [ የኮከብ ] አርማ የሌለውን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ባንዲራ ከላይ ሰቅሎ ፤ ከታች ዝቅ ብሎ ደግሞ (ለጊዜው እላዩላይ ምን እንዳረፈበት ያላወቅሁት) ሌላ ባንዲራ ሰቅሎ ጉብ ብሏል ይለናል ፡፡

አሁን የፖሊስ ኃይልና የእሳት አደጋ ሠራተኞች በቦታው ደርሰው ከሰውየው ጋር እያወሩ ይገኛሉ ፡፡ ሰውየውንም እንደምታዩት በእሳት አደጋው ዘመናዊ መኪና ቀርበው እያነጋገሩት ነው ይላል ደራሲ ይታገሱ ፡፡በመቀጠልም ይታገሱ ይኽ ነገር የአዲስ አበባ ሌላ ድምጿ ነው ወይስ ሌላ? በማለትም ይጠይቃል ።

እኔ ደግሞ አይ ይቴ [ የሰላማዊ ተቃውሞው የከፍታ ዘመን ] የሚጠቁም ይመስለኛል ። የዚህን ሰውዬ ተቃውሞ በሚኒልክ ቤተመንግሥት የሚገኙት እስረኛው ጠቅላያችንም ሆኑ ሁሉም ሹመኞች ካሉበት ሥፍራ ሆነው በደንብ ያዩታል ። በተለይ ረጅም ሰዓት የታክሲ ወረፋ የሚጠብቁት ፣ በየቀበሌው ለስኳርና ለዘይት የተሰለፉት አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችና [ ሰልፈኞች ] ልጁን በደንብ ያዩታል ነው የተባለው ። ምክንያቱም ባንዲራዋ ቀለሟ ጯኺ ነው ። ከየትም ይታያል ።

ጉዳዩን ለየት የሚያደርገው ደግሞ [ በሀገሪቱ ውስጥ በየትኛውም ስፍራ ምንም አይነት የሰላማዊ ተቃውሞ ማድረግ እንደማይቻል በተነገረ ማግስት መሆኑ ነው ። ይኸው አዲስ አበባም ከ 1997 ዓም በኋላ አንድ እንደ [ በላይ ዘለቀ ፣ አብዲሳ አጋና ፣ ዘርዓይደረስ አስገዶም ] የሚወራላትን ጀግናም አገኘች ብንልስ ። ሄሎ አዲስ አበባ የሚል የምስላል ሰውየው እዚህ ፓውዛ አናት ላይ ወጥቶ።

በነገራችን ላይ ይኽ ሰውዬ በፖሊስ ልመና ፣ በእሳት አደጋም ውኃ ከዚህ ከወጣበት ማማ ላይ አልወርድ ቢል ። የኢትዮጵያ መንግሥት ግለሰቡን ከዚህ ፓውዛ ላይ በምን ያወርደዋል ብዬ ስጨነቅ በመጨረሻም በስንት ልመናና ማግባባት የአዲስ አበባ ፖሊስና የፌደራል ፖሊስ ልጁን አግባብተው ከፓውዛው ላይ አውርደውታል ብሏል ይታገሱ ወንድሜ ።

ልጁም ልሙጡን የኢትዮጵያ ባንዲራ እንደለበሰ ከፖሊስ መኪና ላይ ተጭኖ ሔዷልም ብሏል ።

የእኔ ጥያቄ ይሔ ልጅ ጣቢያ ከደረሰ በኋላ ምን ይገጥመው ይሆን.? ማእከላዊስ ይወሰድ ይሆን.? የሚከሰስስ ከሆነ ምን አድርገሃል ተብሎ ይከሰስ ይሆን.? ትንሽ ሾጥ ሾጥ አድርገው ይገርፉትስ ይሆን.? ወይስ በትልቁ… ለማንኛውም ይቴ እንዳለው የለበስካት ሰንደቅ ዓለማ የኢትዮጵያ አምላክ ይከተልህ ። እስቲ ጣቢያ አከባቢ ያላችሁ ፖሊሶች ደግሞ የዚህን ልጅ መጨረሻ አሳውቁን ።

ሳተናው