November 12, 2017 15:28

በአዋጁ ላይ የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ፀሃፍ የመከላከያ ሚንስትሩ ሳይሆኑ የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅፈት ቤት ኃላፍው ናቸው – ደረጀ ገረፋ ቱሉ

 

November 12, 2017 15:28

የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት የማቋቋሚያ አዋጅ በአንድ ወዳጄ ተልኮልኛል።በቅድሚያ ወዳጄን አመሰግናለሁ።

1. በአዋጁ ላይ ግልፅ ሆኖ ባይቀመጥም ምክር ቤቱ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ይመስላል።ጠቅላይ ሚንስትሩ እና እሳቸው የሚመሩት የሚንስትሮች ምክር ቤት ደግሞ ተጠሪነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

2.  የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ተግባር ተብሎ። ከተዘረዘረው ውስጥ የብሄራዊ ምክር ቤቱ ተግባራት በአብዛኛው የመወሰን ስልጣን ሳይሆን የማማከር ነው።ምክር ቤቱ በደህንነት ጉዳይ ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩን እንደሚያማክር እና የውሳኔ ሃሳብ እንደሚያቀርብ በግልፅ ተቀምጧል።ከዚህ የምንረዳው የደህንነት ምክር ቤቱ ሃሳብ ላይ የሚንስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ሊሰጥበት ይገባል ማለት ነው።በተለይ ሰሞኑን የታወጀው ዓይነት ትላልቅ ውሳኔዎች ላይ የምንስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አስፈላጊ መሆኑ ጥያቄ የለውም።በአዋጅ ላይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ እንደሚያስፈፅም ተገልፃል።አሁን ጥያቄው የሚንስትሮች ምክር ቤት ሰሞኑን የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ በወጣው አዋጅ ላይ መክሯል? ወይስ ስልጣኑን እሱም ለብሄራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ አሳልፎ ሰጥቷል?

3. በአዋጁ ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ሰቢሳብ ጠቅላይ ሚንስትሩ ሲሆን ምክትል ሰብሳቢው ደግሞ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ነው።ፀሃፍው ደግሞ የጠቅላይ ሚንስትሩ ፅፈት ቤት ኃላፍ ነው።

ከዚያ ውጭ የመከላከያ ሚንስትሩ አባል ብቻ ነው።ስለዚህ የመከላከያ ሚንስትሩ በምን መለኪያ ነው የብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤቱ ፀሃፍ የሆኑት?

ይህስ ግልፅ የሆነ የስልጣን ነጠቃ አይሆንም?