አሳዛኝ ዜና በመቱ – የክልሉ መንግስት የሁሉም መንግስት መሆን አለበት –  …. – ግርማ_ካሳ

image_pdf

November 13, 2017 13:36

በጣም የሚያስዝን ነው። ዜጎች በአገራቸው ሲሸማቀቁና ሲፈሩ ማየት። አገራችን ሕወሃትና ኦነግ ባመጡት የዘር ፖለቲካ ትንሽ ነገር በቀላሉ ወደ ለየተለት ብጥብጥ የማምራት አቅም አላት። ሁሉም ዘሩንና ጎሳዉን እያሰበ፣ ትንሽ ነገር በተፈጠረ ቁጥር ሌላዉን ለማጥቃት ይፈጥናል። አገሪቱ በዘር ተሸንሽናለች። ይሄ መሬት የትግሬ፣ ያ መሬት የኦሮሞ፣ እዛ ጋር የአማራ እየተባለ።

የትግሪኛ ተናጋሪዎች በአገራችው፣ ፈርተው የመቱ ዩኒቨርሲቲን ለቀው ሄደዋል። ዛሬ ደግሞ ሌሎች ከግቢው በመውጣት ሸሽተው በየቤተክርስቲያናትና መስኪዶች የተደበቁበት ሁኔታ ነው ነበረው።

ደረጄ ገረፋ Dereje Gerefa Tullu “ የሃይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች ፣ የአከባቢው አመራሮች፣ የክልል እና የፌደራል አመራሮች በጋር በደረጉት ጥረት አሁን አብዛኛው ተማሪ ወደ ጊቢ ተመልሰዋል። ለተማሪዎቹ ደህንነት ዋስትና ተሰጥቶአቸዋል ። ጥብቀውን የፌደራል ፖሊስ እና የኦሮሚያ ፖሊስ በጋራ ለመጠበቅ ከስምምነት ላይ ተደርሷል” ሲል ጦምሯል። ዘገባው ምን ያህል ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ አልተቻለም። ከኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ መረጃዎች ካሉ በሚል ወደ ፌስቡክክ ገጻቸው ስሄድ መቱ እየሆነ ባለው ነገር ላይ ምንም አይነት መረጃ ለማግኘት አልቻልኩም።

ሆኖም የደረጄ ዘግባን በመቃረን ጋዜጠኛ ሙሉቀን “አሁን ከመሸ ሁሉም ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ዩንቨርሲቲውን ለቀው ወጥተዋል” ሲል ጸፉል።

ከሶስት ሳምንት በፊት በኢሊባቡር ታሪክ ዘግናኝ ድርግቲ ከተፈጸመ በኋላ (ብዙዎች መጤ ተብለው በገጀራ የተገደሉብት) የክልሉ መንግስት ቢያንስ በክልሉ ለሚኖሩ ሌሎች ማህበረሰብ አባላት “ጥበቃ ያደርጋል ፤ የመኖር ዋስትና ይሰጣል” የሚል እምነት ነበረኝ። ሆኖም ሁኔታው ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ውጭ የሆነ ይመስላል። ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ዉጭ የሆነ፣ የዘር ግጭት እንዲፈጠር ውስጥ ዉስጡን የሚሰራ፣ አክራሪ የኦነግ ክንፍ ያለ ይመስላል። ትንሽ ነገር በተፈጠረ ቁጥር በዚህ መልክ፣ በኦነግ አክራሪዎች በሌሎች ማህበረሰብ አባላት ላይ ጥቃት የሚፈጸም ከሆነ ወደፊት ነገሮች የበለጠ የከፋ ነው የሚሆነው። የክልሉ መንግስት ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ ፣ ከማባባል ፖለቲካ ወጥቶ፣ በክልሉ ያለምንም መሸራረፍ በክልሉ ያሉ የሌሎች ማሀብረሰባትን መብት ማረጋገጥ አለበት። የኦሮሞዎች መንግስት ሳይሆን ኦሮሞውን ጨመሮ በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ሁሉም ዜጎች መንግስት መሆኑ በቅርብ ማሳየት አለበት።

እዚህ በታች የምታዩት ፎቶ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ነው። ተማሪዎች አይመስሉም።፡ተቃዋሚዎች ናቸወ። ዱላ ይዘው።

No widget added yet.

← ማንም ኢትዮጵያን ሊነሳህም ሊመፀውትህም አይችልም!! (ሳምሶን ጌታቸው) ኢትዮጵያዊነት እና  ለማ መገርሣ፦ወደ ኀላ የለም፤ ወደኀላ ! ዳንኤል ሺበሺ →

Leave A Reply

Comments are closed