November 15, 2017 10:58

ብአድን “እንታደሳለን እየታደስን እንሰራለን” የሚል ፉከራ ሲያደርግ ነበር። ሆኖም ቢያንስ ራሱን ከጥገኝነት አውጥቶ ለህዝብ የሚረባና የሚጠቅም ሥራ ሊሰራ ይችላል ብለን ስናስበው የነበረው ብአዴን ሕዝቡን ለበለጠ መከራ እየዳረገው ነው።

– እነ አቶ ለማ መገርሳ የኦፌኮ አመራሮች እንዲፈቱ ግፊት ሲያደርጉ፣ ብአዴን ግን ለነ ኮሎኔል ደመቀ፣ ለነ ንግስት ይርጋ ሲሟገት አይሰማም።

– በተቀረው የአገሪቷ ክፍል አማራ በሚባለው ማህበረሰብ ላይ ጉዳት ሲደርስ፣ መሰረታዊ ፣መፍትሄ ከመጠየቅ ጉዳቱን ማሳነስና ማደብባበስ ነው የሚቀናው።

– ሕዝቡ ወልቃይት ጠገዴ ወደ ጎንደር መመለስ አለበት ሲል ብአዴን መቀሌ ድረስ በመሄድ ወልቃይትን ለሕወሃት ለመስጠት የተፈራረም ነው።

– የሕዝቡን አንድነትና መያያዝ ከማጠናከር ይልቅ፣ ቅማንት ምናምን እያለ የሕወሃትን ፕሮጀክት በጎንደር የተገበረ፣ የሕዝቡን ጥቅም የሚጎዳ እንጂ የሚጠቅም ሥራ የማይሰራ ድርጅት ነው።

አንዳንዶቻችን በብአዴን ውስጥ ተስፋ ሰጪ ድምጾችን ስንሰማ፣ ምን አልባት ከኦህዴድ ጋር በመሆን አንድን አይንት ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ ብለን ትንሽ ተስፋ አድድርገን ነበር። አሁን ግን ብአዴንን ሰርዤዋለሁ። ሕወሃት ሲስተማቲክ በሆነ መንገድ በብአዴን ውስጥ የተነሱ የልውጥ ጥያቄዎችን ሙሉ ለሙሉ የጨፈለቃቸው ነው የሚመስለው። እንደዉም ህወኃት ከማናቸዉም ጊዜ በተለየ ህዝቡን እንዲያማልሉለት ብአዴኖች ስትራቴጂክክ በሆነ መንገድ እየተጠቀመባቸው ነው።

በልማት ረገድ ጥሩ እየሰራን ነው የሚል ሙግት ሊያቀርቡ ይችላሉ። የዉሸት ጋጋታ። የትኛው ልማት ? እስቲ አንድ ምሳሌ ላስቀምጥ። ፍኖተ ሰላም ጎጃም ውስጥ ያለች አንዱ ትላቋ ከተማ ናት። የአባይን ምንጭ ዉሃ ጠማው እንደሚባለው፣በፍኖተ ሰላም ጎጃም፣ የዉሃ አገልግሎት ከመዳከሙ የተነሳ፣ ዉሃ በፈረቃ ነበር የሚመጣው።

አሁን ጭራሽ ብሶ፣ በፈረቃ የነበረ ውኃ፣ ድራሹኑ ጠፍቶ ለዉሃ ወደ ወንዝ እየተወረደ ነው። እንግዲህ በብአዴን፤ የፍኖተ ሰላም ህዝብ በዚህ መልኩ ነው “የንፁህ የውኃ መጠጥ” እየተስፋፋለት ያለው።