የዚምባብዌ የረጅም ጊዜ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ሥልጣናቸውን በፍጥነት እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ አልቀበልም ማለታቸው እየተዘገበ ነው።

REUTERS

የ93 ዓመቱ ሙጋቤ ባለፈው ረቡዕ በመከላከያ ኃይላቸው ቁጥጥር ሥር ከወደቁ በኋላ ተተኪያቸውን በተመለከተ የስልጣን ትግል ተፈጥሯል። እስካሁን ሙጋቤ ከአካባቢያዊ ልዑካኑና ከጦሩ አለቃ ጋር ያካሄዱት ውይይት ውጤቱ ምን እንደነበረ በይፋ አልተገለጸም። ሆኖም የመረጃ ምንጮች ስልጣናቸውን የማስረከብ ጥያቄውን አሻፈረኝ ማለታቸውን እየገለጹ ነው። የተቃዋሚው መሪ ሞርጋን ሻንጋራይ ሙጋቤ ‘የህዝባቸውን ፍላጎት ለማሟላት አሁኑኑ ከሥልጣናቸው መውረድ አለባቸው” ብለዋል። ጦሩ እርምጃውን የወሰደው ሙጋቤ ምክትላቸውን ኤመርሰን ምናንጋግዋን አባረው ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ የፓርቲያቸው ዛኑ-ፒኤፍና የፕሬዝዳንትነት መንበሩን ሊረከቡ እንደሚችሉ ፍንጭ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው። ”ሮበርት ሙጋቤ በቁጥጥር ስር ውለዋል፤ ደህንነታቸውም ይጠበቃል”

በዚምባብዌ የሚገኘው የቢቢሲው አንድሪው ሃርዲንግ እንደሚለው ሙጋቤ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ከተገደዱ ለወታደራዊ ጦሩን ጣልቃገብነት በሂደት ህጋዊ እውቅና ለመስጠት መንገድ ይከፍታሉ። በእርግጥ በዚምባብዌ ጎዳናዎች ሙጋቤ በሥልጣን እንዲቆዩ የሚፈልጉ ሰዎችን ማግኘት ይከብዳል ይላል አንድሪው። ሆኖም ከሥልጣናቸው የሚያርፉበትን ሁኔታዎች የማመቻቸቱና የሽግግር ስምምነቱን የማካሄዱ ሂደት ጊዜ መውሰዱ አይቀርም።

የወታደር መኪና

አሁን በሃራሬ ምን እየተካሄደ ነው?

እስካሁን ምንም ግልጽ አይደለም።

የዚምባብዌው ሄራልድ ጋዜጣ ሙጋቤ የጦሩን መሪ ጀነራል ኮንስታኒቲኖ ቺዌንጋንና የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ(ሳድክ) ተወካዮች ጋር በቤተመንግሥት ሲነጋግሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን አውጥቶ ነበር።

ከእነርሱ ጎን ደግሞ ከሙጋቤ ጋር ለዓመታት የሚተዋወቁት የሮማው ካቶሊክ ቄስ ፊደሊስ ሙኮኖሪ የድርድሩ አካል ሆነዋል። ለውይይቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እንደሚናገሩት የነጮችን የበላይነት ከረቱበት ከአውሮፓውያኑ 1980 ጀምሮ ዚምባብዌን የመሩት ሙጋቤ በቀጣዩ ዓመት ለማካሄድ ከታቀደው ምርጫ በፊት ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ አልተባበርም ብለዋል። ለጦሩ ቅርበት ያለቸው የመረጃ ምንጭ ለአጃንስ ፈራንስ ፕሬስ(ኤ ኤፍ ፒ) ሲገልጹ ” ጊዜ ለመውሰድ እየሞከሩ ይመስለኛል ” ብለዋል።

አንዳንድ ታዛቢዎችም ሙጋቤ ሥልጣን ለመልቀቅ የእርሳቸውና የቤተሰባቸው ደህንነት እንደሚጠበቅ ዋስትና እንዲሰጣቸው ለመጠየቅ ይሞክራሉ ይላሉ። የዛኑ-ፒ ኤፍ ባለሥልጣናት በመጪው ታህሳስ የፓርቲው ጉባኤ እስከሚካሄድ ድረስ ሙጋቤ የመሪነት ስማቸውን ይዘው መቆየት እንደሚችሉና ያኔ ግን ምናንጋግዋ በይፋ የፓርቲውና የሀገሪቱ መሪ እንደሚሆኑ ገልጾ ነበር። መጋቤ በቤተመንግሥት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር መክረዋልImage

አጭር የምስል መግለጫ

መጋቤ በቤተ መንግሥት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል

ZIMBABWE HERALD

መጋቤ በቤተ መንግሥት ከተለያዩ ኃላፊዎች ጋር መክረዋል

የዚምባብያውያን ሃሳብ ምንድን ነው?

በርካታ የዚምባብዌ ዜጎች ሙጋቤ በመኖሪያ ቤታቸው መወሰናቸውንና ጦሩም እርምጃ መውሰዱን ይደግፉታል። ” ጦሩ ጥሩ ነገር ነው ያደረገው” ይላል አንዱ መጽሃፍ ሻጭ ” የሽግግር መንግስት እንዲኖረን ያደርጋል”

እርሱ አሁን የሙጋቤ የ37 ዓመታት የመሪነት ጊዜ እንደተጠናቀቀ ያምናል። ሌሎችም ቢሆኑ የለውጥ ፍላጎት እንደነበረ በሚያሳይ መልኩ አሁን ሃሳባቸውን በግልጽ መናገር ጀምረዋል።

ስለ ሙጋቤ እና ዚምባብዌ ምን እየተባለ ነው?

ደቡብ አፍሪካም ሆነ አካባቢው ምንን ይፈልጋሉ?

ደቡብ አፍሪካ በአውሮፓውያኑ 2008 የዚምባብዌ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ከማሽቆልቆሉ ጋር ተያይዞ የተሰደዱ ሚሊዮን የዚምባብዌ ስደተኞችን ተቀብላለች። በዚህም ምክንያት መረጋጋት እንዲፈጠር ልዩ ፍላጎት አላት።

የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር ኖሲቪዌ ማፊሳ ንካኩላና እንዲሁም የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ሚኒስትር ቦንጋኒ ቦንጎ የ ደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብን (ሳድክ) ወክለው ከሙጋቤ ጋር በመነጋገር ላይ ናቸው።

በተጨማሪ ሳድክ በቦትስዋና ስብሰባ አድርጎ የነበረ ሲሆን ክልሉ ዚምባብዌ ላይ ያለውን ቀውስ አስመልክቶም ጉባዔ እንዲካሄድ ጠርቷል። ” ያለውን የፖለቲካ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ” ጥሪ ማቅረባቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አትቷል።

ሙጋቤ ከታጋይነት ወደ መሪ

የአፍሪካ ህብረት በበኩሉ ስልጣንን በወታደራዊ ኃይል መቆጣጠርን እንደሚቃወም ተናግሯል። የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ-መንበር የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴም በበኩላቸው ጦሩ ተመልሶ ወደ ሰፈራው እንዲመለሱና ሀገሪቱም ወደህገ-መንግሥታዊ ስርዓት እንድትመለስ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የዚምባብዌ ተቃዋሚስ?

የስርዓቱ ተቃዋሚ ፓርቲ ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ መሪ ሞርጋን ሻንጋራይ በበኩላቸው ሙጋቤ በአስቸኳይ ሥልጣን እንዲለቁና “ሁሉንም የሚያሳትፍና የሚስማሙበት የሽግግር መንግስት” የሚቋቋምበት መንገድ እንዲመቻች ጠይቀዋል። እነዚህም ማሻሻያዎች በነፃና ፍትሀዊ ምርጫ የሚመሩ መሆን እንዳለባቸው ጨምረው ተናግረዋል።

ግሬስ ሙጋቤ በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?

በቅርቡ የወጡ መረጃዎች የሚያሳዩት ግሬስ ሙጋቤ ወደ ናሚቢያ እንደሄዱ ነው ነገር ግን ምንጮች አሁን የሚሉት በግቢያቸው ውስጥ እንዳሉ ነው። የደገፏቸው የዛኑ ፒኤፍ ፓርቲ ወጣት ክንፍም አብረዋቸው አሉ።

በዚሁ ሳምንት ረቡዕ ዕለት ቁልፍ ደጋፊያቸው የሆኑት ኩድዛይ ቺፓንጋ የጦሩን መሪ ከተቹ በኋላ የቃል ጦርነቱ ተጋግሎ ጦሩ ሀገሪቷን እንዲቆጣጠሩ ማድረጉን በማስመልከት የተቀረፀ የይቅርታ መልዕክታቸውን በቴሌቪዥን አስተላልፈዋል። ምንም እንኳን ኩድዛይ ቺፓንጋ በጦሩ ቁጥጥር ስለሆኑ ይሆናል ይህንን መግለጫ የሰጡት የሚል አስተሳሰብ ቢኖርም በፍቃደኝነት የተሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል። የፓርቲው ወጣት ክንፍ ታላላቅ አባላትም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የወጡ ሪፖርቶች አሉ።

ሙጋቤና ባለቤታቸው ግሬስ ሙጋቤ

REUTERS

ጦሩ ሀገሪቷን እንዴት ተቆጣጠረ?

በዚህ ሳምንት ረቡዕ ጥዋት ላይ የዚምባብዌ ጦር የሀገሪቱን የቴሌቪዥን ጣቢያ (ዜድቢሲ)ን በመቆጣጠር “ሙጋቤ አካባቢ ያሉትን ወንጀለኞችን ዒላማ” እንዳደረገ መግለጫ ሰጥቷል። ሠራዊቱ እንዲሁም የጦሩ መኪኖች ፓርላማውን እንዲሁም ቁልፍ የሚባሉ ህንፃዎችን ከበው ነበር። ሰኞ ዕለት ጄኔራል ቺዋንጋ ለነፃነት የተደረገውን ትግል በመጥቀስ የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ አባላት ባለስልጣናቱን ማስወገዳቸውን ከቀጠሉ ጦሩ ጣልቃ እንደሚገባ ጠቅሰው ነበር። ኤመርሰን ምናንጋግዋ በአውሮፓውያኑ 1970ዎቹ ለነፃነት በተደረጉ ጦርነቶች ላይ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ታጋይ ናቸው።

BBC