November 17, 2017 19:14


ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ህውሃት ስልጣኑን አስጠብቆ ለመቆየት ከሰራው የድራማ ብዛት አንጸር፣ በኦህዲድ አካባቢ ያየነውን የለውጥ እንቅስቃሴ ህውሃት ከጅርባ ሆኖ የዘውረው ነው ብሎ መጠርጠሩ መሰርት ቢስ ባይሆንም፤ በቅርቡ በኦሮሚያ እና ኣማራ ክልል ቴሌቪዥኖች የተላለፉ ፕሮግራሞች፤ በተለይ በባህርዳር ኮንፍርንስ ላይ የተስተጋቡ ድምጽች ከለመደው የህውሃት የጭንቅ ግዜ መውጫ ተሃድሶ በይዘትም በድምጸትም ያላቸውን የሰማይ እና የምድር ያህል እርቀት፤ እየተንጽባረቁ ያሉት ሃሳቦች ከህውሃት መሰረታዊ ፖለቲካ ፍልስፍ ጋር ፍጽም የተፋቱ መሆናቸው፤ ነገሩን ያው የተለመደ የህውሃት ማዘናጊያ ነው ብሎ በደፈናው ማለፍ የሚያስችል አይደለም።

ህውሃት በብሄር ብሄረሰቦች ፈቃደኝነት ላይ መሰረትኩአት የሚላት አትዮጵያ ህዝቦችዋን የሚያስተሳስራቸው ቃልኪዳን ከአክሲውን ማህበር ውል ያልጠበቀ፤ ላልተስማማው ድርሽውን ተካፍሎ የመውጣት “መብት” የሚያረጋግጥ ነው። በህውሃት እሳቤ፣ የአትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችን አግባብቶ በአንድ ሃገር እንዲቀጥሉ የሚያስችላቸው ብቸኝ ዋስትና ህገ መንግስቱ “ያጎናጽፋቸው” ያልፈለጉ ቀን ሃገሪቱን በትነዋት የመለይይት መብት ነው። ዛሬ ከኦህዲድ ሰውች በግልጽ እየሰማነው ያለው ግን፤ ኢትዮጵያዊያን አንድነታችን ላይፈታ የተገመደ፤ ብቸኛ እጣ ፈንታችን ውይ ተደጋግፎ መነሳት ወይ ተያይዘዞ መውድቅ የሆነ ህዝቦች መሆናችንን ነው።

በህውሃት ትረካ መሰረት የቅድመ ህውሃት ኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ናት። ህዝቦችዋም ከጭቁአኝ ተጭቁአኝ ግንኙነት ያለፈ ትስስር ያላቸው አልነበሩም። ህውሃት የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ምስረታም ሆነ ግንባታ ያለውን ታሪክ፤ በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ያሳረፈውን አሻራ ደምሰሶ ነው የሚነሳው። በቅርቦ ግን የህን የህውሃት ትርክት የመቀልበስ፣ የተካደውን የኦሮሞ ህዝብ ተሳተፍ መለሶ የማጽናት(ሪክሌም የማድረግ) አካሄዶች አስተውለናል።

ህውሃት በየተኛውም ታድስኩ ታረምኩ ባለበት ውቅት፤ ችግር ብሎ የሚለው የአፈጻጸም ችግር፣ የግለሰቦች ምግባር ብሉሽነት፣ ትምክተኝነት፣ ጠባብነት እና ወዘተረፈ እንጅ ከዛ አልፎ መሰረታዊ የሆነ የርእዮት አለም ችግር አለብኝ ብሎ አያውቅም። የብስ ብሎ የተሃድሶውቹ መቆኣጫ ከመስመር ውጥተናል ወደ መሰራታዊ ባህሪያችን እንመለስ አይነት ነው። አሁን ኢትዮጵያ የገባችበት ቀውስ መንስኤ፤ ባለፉት አመታት የተራመደው በተነሽዋረረ የታሪክ ኣረዳድ ላይ የተመሰረተ የልዮነት ፖለቲካ እንደሆነ ሲነገር የተሰማው ለመጅመርያ ግዜ አሁን ነው። የህን የልዮነት ፖለቲካ በስልጣን ለመቆየት ሆነ ብሎ ያራመደው አካል እንዳለም በውስጠ ውይራም ቢሆን ሲገለጽ ተሰምቶአል። እንደ እኔ የኦህዲድን ለውጥ ከተለመደው የህውሃት ተሃድሶ በጉልህ የሚነጥለው ይሄ ነው።

በርግጥ ህውሃት ከዚህ በፊት አስፈላጊ ሆኖ ባገኝው ወቅት አንድንትን እንደሚያቀነቅን አሳይቶኣል። ያን ሲያድርግ ግን መሰረታዊ ፖሊቲካውን በማያደፈርስ ሁኔታ በጥንቃቄ፤ በተቻለ መጠን እነሱ አቀናናት በሚሎት የ 27 አመቶ ኢትዮጵያ ዙሪያ አትኩረት በማድረግ ነው። ህውሃት መሰረታዊ የርእዮት አለም አብዮት በራሱ ላይ ማካሂድ ከውስነም፤ እራሱ በፊት አውራሪነት ያቀንቀንቅዋል እንጅ፣ ክሪዲቱን ለኦህዲድ አሳልፎ የሚሰጥበት ምክንያት አይታየኝም። በዛላይ የኦህዴድ ወደ መሃል መምጣት ህውሃት አማራ እና ኦሮሞ መካከል እጫውተዋልሁ የሚለውን የገላጋይነት ሚና ያሳጣዋል።

ባጠቃላይ እያየነው ያለው፤ የህውሃትን ስልጣን ለማትረፍ ደፋ ቀና የሚል ኦህዲድን ሳይሆን፤ የህውሃት መዳከም የፈጠረውን አጋጣሚ በምጠቀም፤ በኦሮምያም በብሄራዊ ደረጃም ተጽኖ ፈጣሪነቱን ለማሳደግ አለሞ በተውሰነ ደረጃም ቢሆን በራሱ የፖለቲካ መስመር መንቀሳቀስ የጀመረን ኦህዲድን ነው። ይህ ደግሞ በይሁንታ ልንቅበለው የሚገባ ዜና ነው። ኦህዲድን ሰውች፣ ህውሃት ሲያራግበው ከኖረው ‘እኛ የለለን ቀን ኢትዮጵያ ትበተናለች’ ሞርት በተቃራኒ፣ በህውሃቶች ውድቀት ዋዜማ ከተለጠፈባቸው የጠባብነት አጥር ወጥተው ብሄራዊነት መላበሳችው ሃገር ከማረጋጋት አንጽር ያለው ተጽኖ ቀላል አይሆንም።

የህውሃትን ዙፋን ከምንም በላይ የተሸከመው፤ ለአመታት በረቀቀ ዘዴ በኢትዮጵያዊያን መካከል ያሰረጹት የፍርሃት፣ የጥርጥር እና የመለያየት መንፈስ ነው። የድህረ ህውሃት ኢትዮጵያ የተረጋጋች እንድትሆን፤ የህ መንፈስ በመግባባት እና በአንድነት መንፈስ መተካት አለበት። የኦህዲድ የወቅቱ አካሄድ የምንመኝውን የአንድነት ስሜት ከማጠናከር አኮያ ሜናው ትልቅ ነው። የኦህዲድን ሰውች፣ በጀመሩት መስመር የመቀጠል አቅም እና ቁርጠኘነት እስከየት ነው የሚለውን ግዜ የፈታዋል። አያያዛቸው ግን የበል የሚያሰኝ ነው። ተፈራርቶ የነበረን ህዝብ የሚያቀራርብ፤ ብሄራዊ መገባባትን የሚያጠናክሩ ሃሳቦች ከየትም ውገን ቢነሱ፤ ሃሳቡ ሃቅ ያለው እና የተቃና እስከሆነ ድረስ፤ ካንገት ነው ካንጀት ነው እያሉ ከመነታረክ ይልቅ፤ ተቀብለን ልናስተጋባው ነው የሚገባ።

የሃገራችን ችግር በጣም ውስብስብ ነው። ከአንድ አካባቢ የሚመጣ ለውጥ የሚፈታው አይደለም። ዋናው ነገር፣ የህውሃት አገዛዝ ተገርስሶ፤ ለሁላችንም ሰላም የምትሰጥ ኢትዮጵያን ለመመስረት ትግል የሚያደርግ ሁሉ ሳይዘናጋ ትግሉን መግፋቱ ላይ ነው። በዚህ ሂደት ውስጥ ግን በያቅጣጫው የሚፈጠሩትን መልካም እድሎች እያስተሳሰሩ መራመድ ያስፈልጋል።
ከፍቅርተ ገላው