(በሃያሬ ተንለሱ)

1. አማራና ኢትዮጵያዊነት

አማራነት የኢትዮጵያ መሠረት ሆነው ኢትዮጵያን ላቆሙ፣ በፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ አውሮፓውያንን ካሰማሩዋቸው የውጭና ሃገር በቀል ባንዳዎችን ድል በመምታት ሃፍረትን ያከናነቡ፣ ለጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌ ለሆኑ፣ ከባርነት ስሜትና የአይምሮ አጎብዳጅነት ነፃ የሆኑ ህዝቦች መለያ በመሆን በኢትዮጵያዊነታቸው ለሚኮሩ ለጀግኖቹ የኢትዮጵያ ብርቅዬ ልጆች ሁሉ የተሠጠ የክብር ስም ነው። አማራነት የጀግኖቹ እምዬ ሚኒሊክ፣ ጣይቱ ቡጡል፣ ንጉስ ተክለሃይማኖት፣ ባልቻ አባ ነብሶ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ፣ ራስ መኮንን፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዩርጊስ፣ ሃይለማርያም ማሞ፣ አብድትሣ አጋ፣ ራስ አሉላና የሌሎች እልፍ አእላፍ ኢትዮጵያዊ ጀግኖች የጋራ ስም ነው።

አማራነትን ከነዚህ ጀግኖች፤ ጀግኖቹንም ከአማራነት ውስጥ ለይቶ ማውጣት የማይቻል በጊዜ፣ በቦታና በወቅታዊ ሁኔታ የተሣሰረ የደም፣ የማንነት የክብርና የታሪክ ቅንብርም ነው። ኢትዮጵያ ሃገሬ ህዝቧ በስነልቦና፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ ድንበር ዘለል ባህላዊ መወራረስና የሚሊዮኖች የጋብቻ መጠላለፍ ምክንያት ህብረ- ብሄራዊ መርከብ በመሆን ዜጎቿ የሚቀዝፏት ልዮ ሃገርም ናት። አንዱ ሌላውን:ሌላውም አንዱን የሚመስልበት ከሚለያዩበት የሚመሣሰሉበት የጋራ እሴቶች ያላቸው በልዩነታቸው ውስጥ አንድነታቸው የጎላ ህዝብን ያቀፈች ሃገርም ኢትዮጵያ ናት።

በያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ዜግነት፤ በሁሉም ኢትዮጵያዊ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ክብር አለ። በአማራ ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያዊነት እየተጠቀምን በኢትዮጵያዊነት ውስጥ ያለውን አማራነት እያዳፈንን ኢትዮጵያዊነትን ማለም አንችልም። አማራነትን ለፖለቲካ ፍጆታ/Political consumption/ እና ፖለቲካዊ ትክክለኛነት/Political correctness/ አገልግሎት እየተጠቀምንና በተንሸዋረረ ዓይን እያየን ስለኢትዮዽያዊነት ማሠቡና መነዛነዙ ቀልድም ነው።

አማርኛ ተናጋሪ ሁሉ አማራ መሆን ይችላል። አማራ የሚለውም ኢትዮጵያዊ ስሙ ተነጥቆና ተንኳሶ አማራ ነው ስምህ ተብሎ ዛሬ በኮሪደር ተገድቦ የሚንገላታውን የህዝብ ስብስብ ነው። ለነፃነቱ በከፈለው ዋጋና ሃገሩ ኢትዮጵያን በማቆሙና ክብሩን ያለመደራደሩ ወንጀል ሆኖ ዛሬ በባንዳዎችና ከሃዲ ውላጆች የሚቀጣ ህዝብ ነው።

በዘመነ ትግሬ ወያኔ የአማራ ታዳጊ ህጻናት ትምህርት ቤት

 

ከኢትዮጵያዊነቱ ውስጥ አማራነቱ፤ ከአማራነቱም ውስጥ ኢትዮጵያዊነቱ ተዘርፎ ወራሪን ባርበደበትና ድል በነሳበት በሃገሩ ኢትዮጵያ መሬት ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ በባንዳዎችና በሹምባሾች አዎን ዛሬ ይሸማቀቃል። አዎን ኢትዮጵያዊ ነኝ ያለ ሁሉ አማራ ተብሎ ከተፈረጀ ከ26 ዓመት በላይ ሆነ። በተለይ አማርኛ ብቻ ተናጋሪ አማራ ተለይቶ አማርኛን በደባልነት በመናገራቸው አማራ ሆነውና አማራ-ኢትዮጵያዊ መስለውና የአማራ ለምድ ተላብሰው ወያኔ ሠራሹን አሻንጉሊት “የአማራ ድርጅት-ብአዴን” የተሠኘ ስም ጭነው ከከሃዲው ወያኔ ጋር በመሆን ጀግናውን የኢትዮጵያ ልጅ በአማራ ስም ሲገፉት፣ ሲያስሩት፣ ሲገድሉት፣ ሲያስገድሉትና ከቀዔው ሲያፈናቅሉት ይስተዋላል። እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች አማራውን በመግደል ኢትዮጵያዊነትን የሚሽሩና ኢትዮጵያን የሚንዱ እየመሰላቸው ጥፋታቸውን ተያይዘውታል።

ኢትዮጵያዊነትን ያለ አማራ ማሠብ ውሃን ያለ ሃይድሮጅን ውሁድነት በኦክሲጅን ብቻ ለማምጣት መመኘት ነው። አማራን ማጥፋት ማለት የኢትዮጵያን ህዝብ ማጥፋት ነው። ይህ ህልም ብቻ ሣይሆን የቀን ቅዠት/daydreaming/ ነው። ኢትዮጵያዊነት አማራነት፤ አማራነትም ኢትዮጵያዊነት ነው። ምክንያቱም ሁሉም ኢትዮጵያዊ አማራ፤ ሁሉም አማራ ኢትዮጵያዊ ነው። ኢትዮጵያዊነት አንድነት በፍቅር ተሳስቦና ተፋቅሮ መኖር ነው።

በዘመነ ትግሬ ወያኔ የአማራ ሕዝብ ኑሮ

ኢትዮጵያ የህዝቧ እንጂ የገዢዎቿ ንብረት አይደለችም። ግፈኛ ገዢዎቿ በጊዜ ይወገዳሉ። ኢትዮጵያ ግን ትቀጥላለች።ቀጥላለችም። ኢትዮጵያ ያለ ግፈኛ መሪዎቿ ኖራለች።ትኖራለችም። ነገር ግን ግፈኛ መሪዎቿም ሆኑ የግፍ ሠለባ የሆኑ ልጆቿ ያለ ኢትዮጵያ የሉም። ለዚህ ነው ፖለቲካዊ ስርዐትና ሃገር አይደበላለቁ የምንለው። ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከአማራ፤ አማራም ከሁሉም ኢትዮጵያውያን ከደምና አጥንት ተሰርቷል። ጥንት በጣሊያንና ሌሎች ወራሪዎች ይሁን ዛሬም በወያኔ ከሃዲና ባንዳዎች ስሌትም ኢትዮጵያዊነትን መዘከር አማራነት ነው በሚል እሣቤ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት አማራን ማጥፋት የስትራቴጃቸው ዋነኛ ቀመር ነው።

አማራን ማጥፋትም ኢትዮጵያን ማክሠም/cease to exist/ነው። ኢትዮጵያዊነት እነርሱ አማራ ብለው የፈረጁት ህዝብ ብቻ አይደለም። የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ንብረት እንጂ። ዛሬም የህወሃት ወራሪዎች ከሃዲና ባንዳዎች ልክ እንደ ጥንቱ ጣሊያንና ሌሎች ወራሪዎች ኢትዮጵያን በመዳፋቸው አድርገው የልጆቿብ ደም በዋግምት ለመመጥመጥ በግንባር ቀደም ጠላትነት ፈርጀው የመጡት አማራ ኢትዮጵያዊውን ነው። አማራም ብለው የሣሉት ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሠውንና ለአንድነቷና ክብሯ የቆመውን ኢትዮጵያዊን ነው።

ህወሃቶች እንድ አንበጣ መንጋ የወረሩት መላው ኢትዮጵያን ረግጠው የሚገዙትም ሁሉን ኢትዮጵያዊ ነው። ለዚህ ነው ኢትዮጵያዊነታቸውን የሚመክቱትን ኢትዮጵያውያን ሁሉ ጠላቶቻችን በአማራነት የሚፈረጁት። ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊነት አማራነት፤ አማራነትም ኢትዮጵያዊነት ነው የምንለው።

በዘመነ ትግሬ ወያኔ የአማራ ህዝብ የጤና ሁኔታና እየአናትቶች ኑሮ

አማራነት ለሁሉም ኢትዮጵያዊ፤ ኢትዮጵያዊነትም የአማራ ክብር ነው። ኢትዮጵያውያንም ለሃገራቸው ኢትዮጵያ ማገርና ምሰሶም ናቸው። የጨቋኝ ስርዐት ግፍና በደል ሠለባነት እንጂ የኢትዮጵያ ዜግነት አድልዎና ችግር የለባቸውም። ትግላችንም ኢትዮጵያን የአማራ ወይም ያንዱ ጎሣ ለማድረግ ሣይሆን ኢትዮጵያን የኢትዮጵያውያን ሁሉ ለማድረግ ብቻ ነው። ለዚህ ማረጋገጫው ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩበት: ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚኖርበት፤ የእምነት ነፃነት የሰፈነበት፤ የግለሰቦች ያልተገደበ መብትና ነፃነት የሚፀናበት፤ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የነገሠበትና ሠዎች ለሕግ እንጂ ሕግ ለሠዎች የማይገዙበት ዲሞክራሲያዊ ስርዐት ምስረታ ብቻ ነው።

2. አማሮች ለምንና በማን ይገደላሉ?

በያዝነውም ዘመን ልክ እንደ ጣሊያን ወራሪዎች ኢትዮጵያዊነት እንዲያከትም ኢትዮጵያም እንድትበተን ዋነኛው የኢትዮጵያ ጋሻ አማራ ነውና ይህን አማራ ማጥፋት የሚል መርሃ ግብር ከሽኖ የሚንቀሣቀሰው በዋናነት ወያኔ ነው። ወያኔም ለዓላማው መሣካት ከሻዕቢያ ጥንት የወረሠውንና በጊዜ የማይለወጠውን ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ ትርክት አንግቦ ይህንንም የፈጠራ ትርክት ለአክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች አሸክሞና እነርሱንም እየነዳ በአማራ ላይ ታሪክ የመዘገበው ጅምላ ጭፍጨፋ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ተግብሯል። እየተገበረም ነው።

የጣሊያኖችና ወያኔዎች ትርክት ሰለባዎችን አደራጅቶ በበደኖ: በአርባጉጉ:በጉራፈርዳ በቅርቡም በኢሊባቡርና በቤኒሻንጉል ንፁሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ አሣርዷል። ግድያውን የሚተገብረው በአካባቢው ጎሣዎች ሣይሆን ከጎሣው ውስጥ በመለመላቸው ቅጥረኞችና ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰቦችን በመጠቀም ነው። ይህም ግድያ ጎሣዎችን እርስ በርስ ለማጋጨትና ኢትዮጵያዊነትን ለማዳከም ሆን ተብሎ በተጠና መንገድ የሚከናወን የዘር ፍጅት/genocide/ ጥንስስም ነው። አማራ ለሃገሩ ኢትዮጵያ እንጂ ለራሱ ኖሮም ሞቶም አያውቅም። ዛሬም የሚገደለው እጥብቆ ለያዘው ኢትዮጵያዊነት ማህተሙና ማተቡ ብቻ ነው። ዛሬም እንደትላንቱ የሚገፉትና የሚገድሉት ባንዳዎችና ሹምባሾቻቸው ናቸው። ዛሬም የሚገደለውና የሚሠደደው በጎሣ ፌደራሊዝም ስም ነው። ዛሬም የሚሞተው ለኢትዮጵያዊነቱ ነው።

ልክ ፈጣሪ ታማኝነቱንና ትዕዛዙን መፈፀሙን ለማረጋገጥ አብርሃምን ልጁን ይስሃቅን ለመስዋትነት እንዲያቀርብ አዘዘው። አብርሃምም የፈጣረውን ትዕዛዝ በማክበር ልጁ ይስሃቅን ለመስዋትነት አቀረበው። የትዕዛዙን መከበር ያረጋገጠው ፈጣሪም የይስሃቅን መስዋዕት በበግ ተክቶት የይስሃቅን ህይወት ታደገው። በአንፃሩም ፋሺስቱ ወያኔም ለይስሙላ የጎሣ ፌዴሬሽኑ ጠላት አድርጎ የፈረጀውን አማራ በየአቅጣጫው ለጭዳነት አቀረበው። ልቡ የተደፈነ አረመኔም ነውና መስዋዕቱን በበግ መተካት ይቅርና እራሱን አማራን አረደው። ዛሬም እያረደውና በትዕዛዙ እያሣረደው ነው። ፈጣሪ ወያኔ አይደለም። አማራም ከእንግዲህ ልጆቹን ለመስዋዕትነት እንደ አብርሀም አያቀርብም። የመስዋዕት በግም አይደለም።

3. የጥሪ ደወል

ይህ ደወል የሚጮህና ከሩቅ የሚይስተጋባ ደወል ነው። የዘር ፍጅትንና የዘር እልቂትን ለማስቆም የሚሠማ የመከላከል ወይም ለመከላከል-ማጥቃትን ጠቋሚና ተግባራዊ ድምፅ ነው። ደወሉ በዚህ በቦስተን-ምሳቹሴት የሆሎኮስት ሰለባዎች መታሰቢያ ላይ የሰፈረው የሬቨረንድ ማርቲን አባባል ውስጥ እንዲህ ይስተጋባል :-

“ናዚዎች በመጀመሪያ ሶሻሊስቶችን ለመግደል መጡ። ሶሻሊስትም አልነበርኩምና እኔም የተቃውሞ ድምፅ አላሠማሁም። በመለጠቅም የሠራተኛ ማህበር መሪዎችን ለመጨፍጨፍ ሲመጡ የማህበሩ አባል ባለመሆኔ ትንፍሽ አላልኩም። አሁንም አይሁዶችን ለመግደል መጡ። አይሁድም አልነበርኩምና ዝምታዬን ቀጠልኩበት።
ናዚዎቹ በስተመጨረሻ ወደ እኔ መጡ። ከነርሱ ግድያ የተረፈ ማንም ስላልነበር ለኔ የሚናገር ጠፋ”

4. ምን መደረግ አለበት?

የህወሃት ወያኔ ሽፍታዎች ለማጥፋት የተነሱት ኢትዮጵያዊነትን የሚያወድሠውንና ለአንድነቷና ክብሯ የቆመውን ኢትዮጵያዊን ነው። ይህን ስብስብ አማራ በሚል ስያሜ ስር አነጣጥረውበታል። እየተኮሱበትም ነው። ከእንግዲህ ሞትን ወደ ገዳዮች መንደር መውሰድ እንጂብቆመን አንጠብቀውም። ከእንግዲህ ሞትን ሞተን አንጠብቅም። የሚነደውን የሚመጣውን እሳት ለማጥፋት ያልተቀጣጠለውን መለኮስ እሳትን በእሳት ማጥፋት የሚያስችል ብልህነት:ጥበብና ብቸኛ ምርጫም ነው። ለዚህም የአማራ-ኢትዮጵያዊ መደራጀት የወቅቱ አንገብጋቢ ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያ ሃገራችን በደም ከመዋዠቅ የሚያድናት መፍትሄም ነው። አማራነት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ያቀፈ የመከላከል ሃይል ነው። የሁሉም ኢትዮጵያዊ ትንሣኤ ጎህ ቀዳጅ ነው።

የአማራው መደራጀት የወያኔን ‘ዳሞክራሲያዊ ብሄረተኝነትን’ በታኝ ሃሳባዊ ቅዠት የሚጋራ ሣይሆን ይልቁንም የሚያመክንና/debunking/ለኢትዮጵያ ምፅዓትና ልዕልና መኖር ዋስትና ነው። ህብረ-ብሄራዊነትን ለማጠናከር ምድር ላይ ያለውን አደረጃጀት ‘የወያኔን ሠርዶ ባገሩ በሬ’ ለማክሰም እንደ አንድ ግብዓት የሚታይ እንዲሁም ህብረ-ብሄራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን ሲባል ‘ጎባጣን ለመምሰል ጎብጦ መሄድ’ ዓይነት በሣልና ወቅታዊውን እውነታ ጋር የተጋባ አማራጭ የሊለውም ፖለቲካዊ ስልት ነው። አማራው በኢትዮጵይዊነቱ ውስጥ ያለውን አማራነት ይምዘዝና ለኢትዮጵያ ትንሣኤ ሳንጃውን ይወድር ማለት ነው። አማራው ተደራጅቶና ሌሎች ኢትዮጵያውይንን አደራጅቶና አካቶ ልክ የጣሊያን ወራሪን ድል እንደነሣ ባንዳ ወያኔዎችን ወደ ትቢያ ያሽቀንጥር ማለት ነው።

በዘመነ ትግሬ ወያኔ የአማራ ህዝብ ኑሮ

አማራው በኢትዮጵያዊነቱ ውስጥ ያለውን አማራነት መዞ ለኢትዮጵያ አንድነት እስካዋለው ድረስ በአማራነቱ ተደራጅቶ እንደ ጭዳ በግ በየሜዳው ከሚያርዱት ገዳዮቹ እራሱን መጠበቁና መታደጉና ኢትዮጵያን ከእፍራሾቿና ተላላኪ የውስጥ አርበኞች/fifth column/ መመከቱና መከላከሉ ችግሩ ምንድነው? ይህን አደረጃጀት መቃወምና ማብጠልጠል አያድን ጋሻ ቂጥ አስወጊነትም ነው። አማራ በአማራነቱ መደራጀቱ ኢትዮጵያን ለምንል ኢትዮጵያውያን መጨረሻው ከዘር አባዜ የፀዳ ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩበት: ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል የሚኖርበት፤ የእምነት ነፃነት የሰፈነበት፤ የግለሰቦች ያልተገደበ መብትና ነፃነት የሚፀናበት፤ የሕግ የበላይነትና ተጠያቂነት የነገሠበትና ሠዎች ለሕግ እንጂ ሕግ ለሠዎች የማይገዙበት ዲሞክራሲያዊ ስርዐት ምስረታ ዋስትና ነው።

አማራ በአማራነት ከተደራጀ የኢትዮጵያን አንድነት አደጋ ላይ ይጥላል የሚለው ምድር ላይ ካለው እውነታ በብዙ ሺ ኪሎሜትሮች ያፈነገጠ ግዙፍ ስህተት ነው። የገዳዮቹን የሞት ድግስ እንዲቀበልና የሞት ፅዋ በቁሙ እንዲቀበል መምከር ነው።ፖለቲካዊ እጥፍ ዘርጋ /Political flexibility/ አጭር ግቦችን ለማሳካት በጊዜያዊነት ቢያገለግልም በዘላቂነት ከያዙትና ከተጣበቁበት ያጭር ጊዜ ስልት መሆኑ ይቀርና የመጨረሻውን ግብ ለድርድርና ለክለሣ የሚያቀርብ አድርባይነት/opportunism/ ይሆናል።

ይህ ትርክትና የፖለቲካ ትክክለኛነት ስሌት ከትርፉ ይልቅ ኪሣራው ያመዘነ: ያልተገመተ ወይም ያልተጠበቀ መዘዝን/unintended consequences/ ያላገናዘበ ፖለቲካዊ ብዥታም ነው። ህዝባዊና ሃገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለ ህዝባዊ ይሁንታና ተወካይነትና ያለዲሞክራሲያዊ አግባብም በድርጅቶች መሃል የሚደረግ ማንኛውም ዓይነት ፖለቲካዊ ስምምነትና ፈቃድ/concession/ፖለቲካዊ ጥበብ ሣይሆን ፖለቲካዊ አሻጥር/Political intrigue/ ነው። በተፈጥሮውም ፀረ- ዲሞክራሲያዊ አካሄድም ነው።

ባጭሩ አማራዊ እና ህብረ-ብሄራዊ አደረጃጀት የሚጣረሡ ሳይሆን የሚደጋገፉና የሚመጋገቡ/symbiotic & obligatory/ ግባቸው አንድና ኢትዮጵያም ነው። ልብ እንበል። ጠላት እያሣደደ የሚያጠቃው አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው። አማራነት ልክ እንደ አይሁድነት የአንድነት ምልክት ነው።

አማራዊ አደረጃጀት የአማራን መጋዝና ሞትን ይታደጋል። የአማራ መደራጀት የኢትዮጵያን መኖር ያረጋግጣል።
አማራ ከእንግዲህ የአብርሃም በግ አይሆንም እራሱን ያደራጃል። አማራነት እራሱንና ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን ይታደጋል።
አማራነት ኢትዮጵያዊነት ነው። ኢትዮጵያዊ- አማራነት በድርጅታዊ ክህሎቱ የኢትዮጵያን ትንሣኤ ዛሬም እንደ ትላንቱ ያበስራል።

እሾክን በእሾክ ነውና አዎ አማራ ይደራጃል።