November 20, 2017 07:28

ከህወሃት ባለስልጣናት እንደ አቦይ ስብሃት የሚገርመኝ ሰው የለም፡፡ ሰውዬው ፊት-ለፊት ስለሚናገሩ ግልፅነታቸው ይመቸኛል፡፡ ነገር ግን፣ በግልፅነታቸው ውስጥ ቅጥ-ያጣው የህወሃት ግብዝነት ስለሚንፀባረቅ ንግግራቸው ያበሳጨኛል፡፡

ለምሳሌ ትላንት በጎንደር በተካሄደው ስብሰባ ላይ “…ከኦሮሞ ጋር ለምን ግንኙነት መሰረታችሁ? አላማው ምን ነበር? ምንስ ታስቦ ነው? አሁንም ብታስረዱን…” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ይህን ማለታቸው የእሮማራ ጥምረት ለህዋህቶች ምን ያህል ስጋትና ፍርሃት እንደከተታቸው ያሳያል፡፡ አቦይ ስብሃት ይህን ፍርሃት በይፋ በማጋለጣቸው ይመቹኛል፡፡

ነገር ግን፣ የNational_Party መስራች እና አመራር ካልሆንክ በስተቀር የሁለት ህዝቦች ትብብርና ግንኙነት ስጋት ሊፈጥርብህ አይገባም፡፡ (National Party በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓትን የመሠረተው ፓርቲ ነው) ልኬ እንደ ደቡብ አፍሪካ በኢትዮጲያ የአፓርታይድ ስርዓትን የዘረጋው ህወሃት መስራች የሆኑት አብይ ስብሃት በኦሮማራ ጥምረት ፍርሃትኒ ስጋት ቢያድርባቸው አይፈረድባቸውም፡፡

ያም ሆነ ይህ፣ አቦይ ስብሃት “ከኦሮሞ ጋር ለምን ግንኙነት መሰረታችሁ? አላማው ምን ነበር?” በማለት ላነሱት ጥያቄ መልሱ በአጭሩ “የህወሃትን የብሄር አፓርታይድ ለማስወገድ ነው!!” የሚል ነው፡፡