ከአያሌ ዘመናት የግፍ አገዛዝ በኋላ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ገዥዎቹን፤ ያለ ማንም ርዳታ በገዛ እጁ ከሥልጣን ያወረደበት ዘመን 1966 ዓም ነው ። ይኽንን ድል የተቀዳጀው ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ሁሉም ዜጋ ተባብሮ በአንድ ላይ በመቆሙ ነበር ። ይኽ የጋራ ሀገራዊ ድል የተገኘው፤በጎሣ፤ በቋንቋ ፤ በሃይማኖትና በርዕዮት ሳይከፋፈል፤በአንድ ልሳን በመጮኽ፤ በአንድ ልብ በማመንና፤ አንድ ራዕይ በማየት መሆኑ ማንም አይክደውም። በወቅቱ የነበሩት የማኅበራዊና የመንግሥታዊ ሠራተኞች ተቋማት ፤ ህዝባዊና ባኅላዊ ድርጅቶች ሳይቀሩ ፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ- ሀገራዊ አንድነትንና ዕምነትን ያነገቡ ነበሩ ። ከዚኽ ሃቅ በመነሳታቸው ለትግላቸው አንድነት ጽኑ መሠረት እንዲያገኙ አስችሏቸዋል ። በዚያን ጊዜ በነበረው ክስተት፤ የሕዝባዊው ዕመፅ የኃይል ሚዛንና አሰላለፉን ማስታወሱ ለዛሬው ትግል ከሞላ -ጎደል፤ ለግንዛቤ ግዙፍ ርዳታ ያደርጋል።

ዘገባውን ለማንበብ PDF⇓

https://ethiopanorama.comwp-content/uploads/2017/11/finotehatetanovember06_2017-a.pdf

http://assimba.org/