November 20, 2017

የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች

የፍኖተ ዴሞክራሲ ራድዮ ፍካሬ ዜና ህዳር 10 ቀን 2010 ዓ.ም

#ወያኔ የእርስ በእርስ ግጭቶችን በመቆስቆስ ግጭቶችን እያራገበ መሆኑ ተጋለጠ

▪ በሐረር የተከሰተው ግጭትን ተከትሎ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ወያኔ-ህወሀት ሆን ብሎ ውስጥ ውስጡን ባሰለጠናቸው ካድሬዎች ግጭት እያቀጣጠለ ሲሆን በሕዝቡ አርቆ አስተዋይነት እየከሸፉ መሆናቸው እየታየ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በዝዋይ ኦሮሞዎችንና ወላይታዎችን በማጋጭት በግምት ከአስር በላይ የሚሆኑ ንፁሀን ዜጎች በግጭቱ መገደላቸው እና በርካቶች መጽኑ መቁሰላቸው ከስፍራው ከደረሰን መረዳት ተችሏል፡፡ ከአምስት መቶ በላይ የሚደርሱ የወላይታ ተወላጆች አደጋ ስለተደቀነባቸውና ቤቶቻቸውና መደብሮቻቸው ስለወደሙባቸው ተፈናቅለው ወላይታ ሶዶ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ ከዚህ በተያያዘ ይህን ግጭት ተከትሎ፣ ግጭቱን በማረጋጋት ስም የአጋዚ ጣር ዝዋይ ላይ መዝመቱ ይህን ደባ ያሳያል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ይህን የወያኔ ሴራ በንቃት የሚከታተሉ ፖለቲካ አዋቂዎች እንደሚሉት ወያኔ የኦሮሞ ሕዝብን ከተለያዩ ብሔረሰቦች ጋር በማጋጨት እየተቀጣጠለ በመሄድ ያለውን የኦሮሞ ሕዝብ ብሔራዊ ስሜትን ቅስም ለመስበር እንዲያስችለው መሆኑን ያስረዳሉ፡፡

#ወያኔ-ህወሀት ስንጥቁ እየሰፋ መሄዱ ተሰማ

▪ ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው በምህጻረ ቃል ወያኔ-ህወሀት የሚባለው ጠባብ ዘረኛ ቡድን በየጊዜው እየተከፋፈለና ከመስራቾቹም ብዙዎቹ እየከዱት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህ ቡድን ከተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል እየዘረፈ ትግራይን እንደ ታይዋን የማድረግ ቅዠት እንዳለው ቢለፍፍም የተዘረፈውን ገንዘብ እየተከፋፈሉት ያሉት አዜብ መስፍን፣ ስብሀት ነጋ፣ ዐባይ ወልዱ፣ ደብረ-ጽዮን፣ አርከበ፣ ዐባይ ፀሀይ፣ በአጠቃላይ ቁንጮ ወያኔዎችና ውላጆቻቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ በየጊዜው ተሀድሶ፣ ጥልቅ ተሀድሶ፣ አርቲ ቡርቲ የፖለቲካ ችርቻሮ የሚያወጣው ይኸው ቡድን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ምንም ዐይነት የተሀድሶ ጭላንጭል አለመታየቱ የዚህን ዘረኛ ቡድን ዐይን አውጣ ተራ ቁጭ በሉነት የሚሳይ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ በዚህ ሳምንት የመቀሌውን ስብሰባ ሌባዋ አዜብ መስፍንና ኢቢሲ የተባለው የወያኔ ቱልቱላ የዜና ተቋም ሥራ አስኪያጅ የሆነው በርሀነ ኪዳነ ማርያም የቀረበባቸውን ነቀፌታ በመቃወም ስብሰባ እረግጠው መውጣታቸው ታውቋል፡፡ በደረሰን መረጃ መሰረት ወያኔ በሦስት ጎራ እንደተከፈለና የቁንጮ ወያኔዎች መጻኢ እጣ የሕዝባዊ አመጽን ፍርድ መከናነብ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡

#የገበያ ግሽበት ዘርፈ ብዙ ጦስ እያስከተለ መሆኑ ታወቀ

▪ የውጪ ምንዛሪ ጭማሪን ተከትሎ የዋጋ መናር በስፋት እየቀጠለ ባለበት ከሠላሳ ከመቶ በላይ ሊንር እንደሚችል ስጋት መደቀኑ ታወቀ፡፡ ይህ ሁኔታ በከተሞችና በገጠር መንደሮች የሚኖረው ሕዝብን ለከፍተኛ የርሀብ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል አመላካች ሁኔታዎች እየታዩ መሆናቸውን በርካቶች ያስረዳሉ፡፡ በገጠር እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ካለው ድርቅ ጋር በተያያዘ የርሀብተኞች ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እንደሚጨምር የሚጠበቅ እንደሆነ የታመነ ነው ተብሏል፡፡ በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባዎች፣ በተለይም ደጋማ አካባዎች ያልተጠበቀ ውርጭ በመከሰቱ የደረሰው እህል በአመዳ ሊጠቃ እንደሚችል እየተነገረ መሆኑ ታውቋል፡፡ የከተማ ኗሪው ህዝብም በየጊዜው እየናረ የሚሄደውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም እንደማይችል ጥርጣሬ የለም፡፡ ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ሕዝቡ ያለው አማራጭ አንድ ነው፡፡ ይኸውም ወያኔ በፈጠረው ርሀብ ከመማቀቅ በህብረት ተነስቶ፤በአንድነት አምጾ የወያኔን ቀንበር ከትከሻው አሽቀንጥሮ መጣል ነው ተብሏል፡፡

#የኤርትራውያን በአዲስ አበባ ሰለፍ አነጋጋሪ ነው ተባለ

▪ ወያኔ እራሱ ያዘጋጀው ሰልፍ ካልሆነ በስተቀር ሕዝባዊ ትዕይተ-ሕዝብና ስብሰባ በወያኔ የተከለከሉ መሆናቸው የሚታወቅ ነው፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የኤርትራው አምባ-ገነን ቡድን በኤርትራ ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በማንሳት የአፍሪካ ሕብረት ተገቢ የሆነ አቋም መያዝ እንደሚገባው ለማሳሳብ በህብረቱ ደጃፍ መሰለፋቸው የተነገረላቸው የኤርትራ ስደተኞች ሰልፋ ወይስ ሌላ የሚል ጥያቄ መጫሩን መታዘብ ተችሏል፡፡ ባገር ውስጥ የሚካሄዱ ሰልፎችን ካለመፍቀድ ግድያ እስከማካሄድ በሚድርስ እርምጃ የሚያስተናግደው ወያኔ ጥቂት ኤርትራውያንና ትግሬዎችን አሰልፎ የራሱን የፖለቲካ አቋም ለማንጸባረቅና የሚፈልገውን ተጽእኖ ለማሳደር እንዲሁም የህዝብን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ ለማዞር ነው የሚሉ በርካቶች መሆናቸውን ተገንዝበናል፡፡

#የወያኔ የፍትህ ስርዐት ብልሹ መሆኑ ተጋለጠ

▪ በዛሬዪቱ ኢትዮጵያ በፍትህ ሙያ ከመቶው አብላጫ ቁጥር ያላቸው ቀድሞውኑ የወያኔ ካድሬዎች የሆኑን በህግ ትምህርት ከተመረቁ በኋላም እንኳንስ የህግ መጻህፍቶችን አንብበው ሊረዱ የገዛ ስማቸውን እንኳ አጥርተው እንደማይጽፉ ከፍትህ ሥራ ጋር ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት ሁለት በግንቦት ሰባት አባልነት ተከሰው በወያኔ ከርቸሌዎች እየማቀቁ የሚገኙ የፖለቲካ እስረኞች ከወያኔ ፍርድ ቤት ፍትህ እንደማይገኝ በመናገራቸው ወያኔ ዳኛው የፍርድ ቤቱን ፖሊስ በጥይት እንዲመታቸው በኃይለ-ቃል መናገሩ የወያኔ ዳኞች ወታደራዊ ዳኞች፣ ለሕግ የማይገዙ፣ በዘረኛው ወያኔ ፖለቲካ የሚዘወሩ እቡዮች፣ ድንጋዮች፣ መሆናቸው በስፋት እየተነገረ ነው ተብሏል፡፡

#የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቁጥር እየተመናመነ መሆኑ ተነገረ

▪ ወየኔ እርስ በእርስ ሕዝብን ከሕዝብ፣ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ፣ ሀይማኖትን ከሀይማኖት፣ እያጋጨ ለመበጠስ እየነተበ ያለውን የዘረኛ አገዛዙን የእድሜ ገመድ ለማረዘም የጎነጎነው ሴራ ጦሱ በየዩኒቭርሲቲዎች መከሰቱ ታወቀ፡፡ ዘንድሮ በተለያዩ ዩኒቭርሲቲዎች ከተመደቡት ተማሪዎች ከግናሽ በላይ የሚሆኑት ምዝገባ አለመፈጸማቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ በተረፈ የትግራይ ተማሪዎች ከትግራይ ውጪ በሚገኙ ዩኒቭርሲቲዎች ለመማር ተጨባጭነት ባለው ሁኔታ ስጋት ውስጥ በመግባታቸው እዛው ትግራይ እንዲመደቡ አለበለዚያ ትምህርታቸውን ለማቋረጥ እንደሚገደዱ መናገራቸው ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የተጠናቀረው መረጃ ያስረዳል፡፡ከመቱ የኒቭርሲቲ የትግራይና የኦጋዴን ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው የኒቭርሲቲውን ለቀው መውጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ሁኔታ በቅርብ ጊዜያት በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሊስፋፋ እንደሚችል በርካቶች ግምታቸውን